Get Mystery Box with random crypto!

❤የጥበብ መድረክ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ poetry_timee — ❤የጥበብ መድረክ❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ poetry_timee — ❤የጥበብ መድረክ❤
የሰርጥ አድራሻ: @poetry_timee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 414
የሰርጥ መግለጫ

📜እነሆ ለጥበብ አፍቃሪዎች የተከፈተ ምርጥ ቻናል!
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
በቻናላችን
📚 ግጥም
📚 ወግ
📚 መነባንብ
📚 ቀልዶች
📚 ከሚገርም አቀራረብ ጋር በዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ።
👇👇👇
https://t.me/poetry_timee
Contact me : 𝑓𝑜𝑟 𝑐𝑟𝑜𝑠𝑠 𝑎𝑛𝑑 𝑎𝑑𝑚𝑖𝑛
@Leo_poet

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-18 18:33:34 #ማራናታ
( ጌታ ሆይ ቶሎ ና )
.
.
ነፍሴን ሳላሽራት ከሀጥያት ዕድፍ፣
በስምህ ሳልዳኘው የስጋዬን ጉድፍ።
እንደ ጷግሜ ዝናብ፤
እንደ ውሃ ደራሽ አልፎ የቀን ስንኩል፣
ስናፍቀው የነበር ከተስፋ ቃል እኩል።
ደርሶ ሳያበቃኝ ለሀገሬን ትንሳኤ፣
ሳልወጣ አደባባይ ሳልከርመው ሱባኤ።
ጌታ ሆይ አትምጣ ትንሽ ጊዜ ሰጠኝ፣
ነፍሴም ልተጣጠብ ፍቅርህ ይለውጠኝ።
እባክህ ጌታ ሆይ.......
እኔ ስልጡን ባርያ እኔ ብኩን ልጅህ፣
አፈር ትቢያ አካሌን አቁሜው ከደጅህ።
በተማፅኖ እንባ በኩርማን በዓቴ፣
እስክትምረኝ ድረስ ይህ ነበር ፀሎቴ።
"እባክህ አትምጣ!!!"
.
.
አሁን ግን አምላኬ አልልህም ማረኝ፣
መሰንበቴም ይፍረስ አልልም አኑረኝ።
እንዴት ነው መፀለይ?፤
እንዴት ነው መማፀን እንዴት ልለማመን።?
አምባ ነፍስያችን ቤተ እምነት ነደዱ፣
አፀደ እግዜር ማሳ ተርታ ሆኗል መስጂዱ።
እንዴት ነው መፀለይ ፤?
መሻገሪያው ድልድይ፤
መሪ ያልነው ሙሴ መንገድ ላይ ትቶናል፣
ማን ቀብቶት እንጃ ወርዶ አዋርዶናል።
ሚስኪን ሀገሬ እንኳን፤
ከአለም ተነጥላ ላመነችው ጌታ፣
"ኤሎሄ" እንዳለች እጆቿን ዘርግታ።
ለልጆቿ ታምና ታፍራ እንዳልተመካች፣
በአብራኳ ክፋይ በጥፊ ተመታች።
( የሚያሳዝን እውነት )
.
.
እንደምን ልማፀን ?፤
እንዴት ልለማመን።?
የስጋ ፍላጎት ሰው ከመሆን ነግሷል፣
በልባችን መንበር ሰይጣን ቤት ቀልሷል።
መፀለይ ምንድነው፤
መንበርከክ ምንድነው።?
በገረረ ብረት በጦር በጎራዴ፣
በሳንጃ በጩቤ በሻገተ ጓንዴ።
የፈጠርከውን "ሰው" እንደ በግ አርደናል፣
እንደ እንጨት ረብርበን ፍጡር አንድደናል።
.
.
እናም ጌታችን ሆይ.....
እየደጋገምን ዝንት ብንበድልም፤
እፁብ ቤተ መቅደስ እልፍ ሰው ብንገድልም፤
ባለ ብዙ ምህረት ቸር አምላክ ነህና፣
አገኛለሁ ብለህ ቀናዒ ልቦና።
በእዝነት አስበህ ልትምረን ከመጣህ ፣
አትጠራጠረኝ፤
ድጋሚ መገረፍ መሰቀል ነው እጣህ።
ስለዚህ ጌታ ሆይ.....
እኛ ብኩን ህዝቦች፣
እኛ ብስቁል ህዝቦች፤
በ'ለት ኑረት መሃል በስጋ ህላዌ፣
ክፋት ምቀኝነት የከረመ ደዌ።
ጠፍሮ ተብትቦ እንዳወላገደን፣
'ባክህ ቶሎ ናና ጠራርገህ ውሰደን።
.
.
.
በል ፀሎቴን ሰማኝ፤
አንተ ታላቅ ንጉስ አንተ ታላቅ ጌታ፣
"እግዚኦ.. ዘላለም እግዚኦ.. ማራናታ።"

ዓቢይ ( @abiye12 )

Join & share

@sinekal
@sinekal
@sinekal
178 views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 16:38:27 ፍቅር በዚያ ወራት
(ሚካኤል.አ)
#ክፍል 3
ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም።
ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ።
ሺት !
የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም !)... በሷ ቤት አንድ ቀን ኒቃቧ ከፊቷ ሲወርድ ቀድሜ ስለደረስኩላት በችግሬ ጊዜ ቀድማኝ መድረሷ ነው። ችግሬ እሷ እንደሆነች ብታውቅ ስል ተመኘሁ።
"ነጅዬ እባክሽ handle " አድርጊያት ብሎ ዶክተር ወደ ክፍሉ ገባ። ነጅዬ ሲላት ደግሞ ነብር ሆንኩኝ... ከየት መጣ ያልተባለ ቀዝቃዛ ውሀ ፊቴ ላይ ከነበለችብኝ።
የዛክዬን ከናፍር ከመጉረስ ስታግደኝ ነው መቀዝቀዝ የጀመርኩት ።
"ተረጋጊ እንጅ ፀጉሬን ..." ብዬ ጮህኩባት ።
እሷ እንኳን ልትደነግጥ ወገቤ ስር ገብታ አነሳችኝ ። በጥፊ ጉንጯን ባቀላው ስሜቴ ነው ።
እሷና ጓደኞቿ አንከብክበው ጥላ ያላት አፀደ ስር አኖሩኝ ። ንፋሱ ከውሀው ቅዝቃዜ ጋር ተዳብሎ በረደኝ ።
ጥርሶቼ በእልህና ቅዝቃዜ ተንገራገጩ።
"አይዞሽ ንፁህ.. . "
ራስሽ አይዞሽ ብዬ ልመልስላት ይሆን?
አይኖቿ የሚስቁለት.. .ነፍሷ የምትፈነጥዝለት ዛኪን ልቀማት መሆኑን ማን ሹክ ባላት ?
...
ከዛ ክስተት በኋላ ወደ መደበቂያዬ ሮጥኩ !
ክለብ.. .
ጠጣሁ.. . አምሮቴ ንቅል እስኪልልኝ ጠጣሁ ።
ሞቅ እንዳለኝ ያየ አንድ ጎረምሳ የሚያጨሰውን ሺሻ ትቶ ወደኔ አቅጣጫ መጣ።
"ቆንጆ ነሽ" አለኝ።
ዝም!
"ምነው የከፋሽ ነገር አለ ?"
ዝም!
ምናለ ከዛኪ በስተቀር የዓለም ወንዶች ሁሉ ባያናግሩኝ? አባቴና ወንድሜ እንኳ እንዲያናግሩኝ የምፈልግ አይመስለኝም።
አሁን ይሄ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወደል እንዴት ያናግረኛል ?
ጠጪ ...አጫሽ ወንድ ነው ያስጠላኝ።
ያዘነ ለመምሰል ሞከረ !
ውሸት.. . አይኖቹ ውሸት! ...ሳቁ ውሸት...ንግግሩ ውሸት ...
ቆንጆ ነሽ ሲለኝ አመሰግናለሁ ቢለኝ ...አብረን እንፍታታ ብሎ ይቀጥላል ።
እሺ ብለው እኔ ጋር ለማስመሰል ውስኪ ያወርዳል።
ምድር ላይ ያፈቀራት ሴት እኔ ብቻ የሆንኩኝ ያህል አስመስሎ ይንከባከበኛል...ከዛ መተኛት !
አንዴ ጭኔ ስር ገብቶ በለሴን ከቀጠፈ እኮ በነጋታው ስልክ አያነሳልኝም።
ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል.. . ነፍሴ ዛኪ ጉያ ገብታ መሸሸግ ትፈልጋለች ።
ሀጥያቴ የሚጠራው በሱ ላቦት ነው።
"ማሬ አመልሽም ?"
"ማርህን ጎዣም ፈልግ !" አንባረቅሁበት ። ከመቅፅበት ከስሬ በሮ ጠፋ ። ፈሪ ወንድ !
አሁን ይሄ ነው የኔን ጀንታላ ዛክ የሚተካልኝ?
ሌላ ብስጭት.. .
መጠጥ.. . ሻት ...
በቃ ራሴን አጣሁት ። የክለቡ ብልጭ ድርግም መብራት ...መጠጡ.. .ሙዚቃው ናላዬን አዞረኝ ።
ምንም ሆንኩ !
እንደምንም ተንገዳግጄ ሰው መሀል ገብቼ ጨፈርኩ።
እንደ ልማዴ የሰው ሆንኩ...ሳቄ ...ደስታዬ ሁሉ የሰው ሊሆኑ ራሳቸውን ከመቃብር ቀስቅሰው ተነሱ።
ከሩቅ ለሚያየኝ ሰው ደስተኛ ነኝ...ነፈዝኩ...ነጎድኩ ...ብንንንንንንንንንን....
አላልኩም ?
ስጠጣ የሰው ነኝ ብዬ አልነበረምን ?
ማልዶ ስነሳ ራሴን ከሰው ጋር አገኘሁት ።
አንሶላዬን ገልጬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ።
አብሮኝ ያደረው ወንድ እንደ ጆንያ ተንደባሎ ፊቱን ወደኔ አዞረ?
እንዴ?
ይሄ የኢኮኖሚክስ መምህሩ እዘዝ ነው እንዴ?
ዛኪ የነፍስና ገላዬን መርከስ አይቶ የጠላኝ መሰለኝ...
"አንተ ማነህ ?"
.
(ይቀጥላል)

@poetry_timee
244 views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 08:50:54 ፍቅር በዚያ ወራት 

ክፍል 2

(ሚካኤል .አ)

የክፍላችን በር ጋር እስክደርስ የነበረኝ በራስ መተማመን ስሜት እምን ጉድጓድ እንደገባ አላውቅም። ዶክተር ዛኪን ሳየው ልቤ በአፌ ልትወጣ ታገለችኝ። 

እንደ ልማዱ ፅድት ብሎ መጥቷል። (በጣም የሚገርመኝ ነገር ጫማው ላይ እንኳ ብናኝ አቧራ የለምኮ ) ... ለነገሩ ከቤቱ ወጥቶ በኔ ልብ ላይ ተራምዶ ክፍል እየደረሰ በየት በኩል አቧራ ሊነካው ይችላል?

በማስተማሩ በፊት ሁላችንንም በስስት እያየ ሰላምታ ይሰጠናል...ጨዋታ አዋቂ ነው። 

ቢያንስ ፊት ለፊት ከሚቀመጡ አንድ ሁለት ልጆች ጋር ሳይጨዋወት ወደ ማስተማሩ አይገባም። ሲስቅ ከልቡ ነው ... ነጭ ባይሆንም ፈዛዛ ሽሮ መልክ ያላቸው ስድር ጥርሶች አሉት ። ድዱ በእጅ ሳይወቀር ተፈጥሮ አሽሞንሙና ሰርታዋለች ። 

እሱ ይስቃል.. .ልቤ ታለቅሳለች ። ስድር ጥርሶቹ የኔን ነፍስ የሚያጠፋባቸው ድርድር ጥይቶች መሆናቸውን ማን በነገረው ?

ፈገግታው ደስም ይለኛል.. .ያስቀናኛልም። 

በተለይ ለነጃት ሲስቅላት እነዳለሁ ።

ደግነቱ እንደዚህ አይነት አክራሪ ክርስትያን ሙስሊሟን ነጃት ሊወድ ስለማይችል ለራሴ ቅናት መፅናኛ አላጣም።

ይሁንና ግን ይሄን አስቤ እንኳ ልቤ እርፍ አትልልኝም...ያቺ ጣውንቴ አይኖቿ ያምራሉ ...ሰውነቷ ከኔ ይበልጥ የሚስቡ ይመስለኛል...ብዙ ጊዜ ዛኪ አቀርቅሮ ትምህርት ሲተነትን እነዛ ሎጋ የእግር ጣቶቿን እያየ ስለሚመስለኝ እበሽቃለሁ ።

የሆነ ቀን ላይ የፊት ኒቃቧ ሲወርድ መልኳን አየሁት ...ለክፋቱ ደግሞ ዶክተር ፊትለፊታችን ነው። መልኳን ሲያይ መደንገጡን አይቼበታለሁ ...(ድንገትም ስለማፈቅረው መስሎኝም ሊሆን ይችላል )

ከሁሉም ተማሪ በላይ ዘልዬ ፊቷን የሸፈንኩላት እኔ ነኝ። ሙስሊም ጓደኞቿ አላህ ይባርክሽ ብለው መረቁኝ... (ይሄን ያደረኩት ከነጃት የውበት ፆር ዛኪዬን ለመደበቅ መሆኑን የሚያውቀው አላህ ሲባርከኝ እኮ ታየኝ !)

በቃ ከዛን ቀን በኋላ አይኖቼ ሁለቱንም ይከታተላቸዋል። ለሴት ልጅ ውበት ግድ አልባው ዛኪ ለነጃት ግን የተመየ ስሜት ያሳደረ ይመስለኛል....። ክፍል ውስጥ ፊትለፊት ስለምትቀመጥ ሳያሳስቃት ምንም ነገር አይጀምርም። 

ደግሞ ሌላ የሚያበሽቀኝ ነገር የሷ ሳቅ ነው። ስታየው ገና አይኖቿ ይበራሉ.. .ትንሽ ያወራት ጊዜማ ነፍስያዋ ትዘላለች) 

በዚህ ቅናት ተነሳስቼ እኔም እንደሌሎች ቸካይ ተማሪዎች ፊትለፊት ሄጄ ተቀመጥኩ ።

ብዙ አልምጥ ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ። ትምህርት እንደሚደብረኝ ብቻ ሳይሆን እኔም ትምህርትን እንደምደብረው ሁሉም በዙሪያዬ ያሉ ልጆች ያውቃሉ። የኔ ፊት ወንበር ሄዶ መቀመጥ ተማሪውን ብቻ ሳይሆን መምህሬንም ገርሞታል ።

"ዛሬ እንዴት ነው? ... የመማር ሞራልሽ መጥቷል ማለት ነው" ፈገግ አለልኝ ።

ሞትኩለት !

ክለብ ለክለብ የሚቅለበለበው ምላሴ ጉሮሮዬ ላይ ገብቶ ተሰነቀረ ።

የሆነ ቅጥ የሌለው መልስ መለስኩኝ.. .

"አ....አ......መ...ሰ....ለ....እ....ኝ "

ስደናበር ነጃትና ጓደኞቿ ተያይተው ሳቁብኝ። 

በቃ ጠመድኳት ይህችን ሴት !

"ንፁህ ምን ሆነሻል እጅሽ እየተንቀጠቀጠ ነው እኮ!  አመመሽ እንዴ? "

"አዎ ቲቸር !" 

ይኸው የኔ ትሁት ዛኪ ደገፍ አድርጎ ከክፍል እንድወጣ ዕድል ሰጠኝ ።

አለንጋ ጣቶቹ ወገቤን ሲይዙኝ የእውነት ታመምኩለት ...ሰውነቴን እሱ ላይ ጣልኩት ።

የክፍሉን በር ከፍቶ ወጣን ።

"አይዞሽ ንፁህ.. ."

እንዲህ ሲለኝ የነጃት የቅናት ዛር አናቴ ላይ ተፈናጠጠ ።

በድፍረት ከናፍሩን ስሜ ፍቅሬን ልገልፅለት ደፈርኩ ...

አንድ 

ሁለት

ሶስ.....

     (ይቀጥላል)

@poetry_timee
269 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:46:33 ፍቅር በዚያ ወራት

፤፤፤ ሚካኤል.አ ፤፤፤

(ክፍል 1)

ስሜ ንፁህ ይባላል ። የስሜ እዳ አለብኝ። እንኳን ለሰው ልጅ ለመላዕክት እንኳ ያልተገባ መጠሪያ መያዜን ሳስበው እሸማቀቃለሁ።
ከክፍል ጓደኞቼ ጋር እየጨፈርን.. .ሺሻ እያጨስን በምናሳልፋቸው ወቅቶች ስሜን የሚጠራኝ ሰው ባይኖር ስል እመኛለሁ።
ደግሞ ማንም እንደሚያውቀው የትምህርት ቤት ህይወት (ላይፍ ይሉታል ጓደኞቼ በቋንቋቸው) ፈታኝ መሰናክሎች አሉት ።
ጥሩ ፋሽን የማይለብስ ...የማያጨስ ...የማይጨፍር ተማሪ ፋራ ተደርጎ ይቆጠራል። ከማህበራዊ ህይወት ገሸሽ ይደረጋል። ከዚህ ክበብ መውጣት የማይፈልግ ሰው ደግሞ በሰዎች ፍላጎት መሾር ይጀምራል።
ስጨፍር የሰው ነኝ...ከወንዶች ጋር ስላፋ የሰው ነኝ...አጭር ቀሚስ አድርጌ እንደ እሳት የሚጋረፉ ወላፈን ጭኖቼን ሳሳይ የሰው ነኝ።
ስስቅ የሰው ነኝ ። ሁሉ ነገሬ አርቴፊሻል !
ከዚህ ግብግብ ስወጣ ግን ጥያቄ አለብኝ።
የህሊናዬን ጥያቄ ማፈን ስለምፈልግ መጠጥ እጠጣላሁ።
ለምን ትጨፍሪያለሽ?
ለምን ከወንዶች ጋር የውሸት ትስቂያለሽ?
ለምን ትቅሚያለሽ?
ለምን ታጨሻለሽ?
ከዛ መጠጣት.. . መጠጥ ደግሞ ጀንትል ያደርገኛል። ህሊናዬን እናትህን እለዋለሁ ።
እጠጣለሁ.. .እጨፍራለሁ...እቅማለሁ...አምራለሁ ...
እንቅልፍ ይወስደኛል።
ስተኛ ም ዝም አልልም...ተኝቶ ማሰብ ይቻላል ወይ? ለምትሉኝ ሰዎች መልሴ ድብን አድርጎ ማሰብ ይቻላል የሚለው ነው።
የማስበው ዶክተር ዘካርያድን ነው። ምርጥ መምህሬ ... ማኔጅመንት ያስተምረናል...ራሴን ማኔጅ ማድረግ ለተሳነኝ ሴት የድርጅት ማኔጅመንት መማር ግን አያስቅም?
ዛኪ መደበቂያዬ ነው። በሱ ክፍል እኔን ጨምሮ የብዙ ሴት ጓደኞቼ አይን ይስለመለማል ። የሄዋን ዘር ይውደድህ ተብሎ የተመረቀ መምህር ።
አይቅለበለብም...አይቸኩልም...
እርጋታው...እውቀቱ.. .ንፅህናው (ፍንትው ያለ ነጭ ሸሚዝ የሚያደርግ ብቸኛው መምህር እኮ ነው)... ሁሉም ባህሪያቶቹ የሴትን ልጅ ልብ መክፈቺያ ቁልፎች ናቸው።
ቆፍጣና ወንድ !
ከትምህርት በተረፈው ሰዓት ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያገለግል ሰምቻለሁ።
እሱ ሰላም ሲለኝ ሀጥያቴ ተሰርዮ የተቀደስኩ ይመስለኛል። ሳቁ.. .ጨዋታ አዋቂነቱ አይምጣብኝ ። በመሀል ጣል የሚያደርጋት ስብከት ለኔ የህይወት ስንቅ መሆኑን ማን በነገረው?
እንደ ሌሎች ቀለብላባ ወንድ መምህራን ለሴት ልጅ ባትና ዳሌ እጅ ስለማይሰጥ የፍቅር ፋኖስ ልቤ ውስጥ ተለኮሰ!
ቡም !
አዲስ ወጋገን...አዲስ ፍኖት ተለኮሰ !
ከእንቅልፌ ስነሳ ትራሴን ጭምድድ አድርጌ አቅፈዋለሁ። ዛኪ ነፍስያዬን ያግላታል። ሰውነቴን ሲተኩሰኝ እሰማዋለሁ። ትንፋሹ ከሱ ጋር ሳይሆን ከኔ ጋር ያድራል።
ከሁለት ሰዓታት በኋላ አይኑን ማየቴን ሳስበው ሀሴትን አደርጋለሁ።
ሆኖም ከደስታዬ ሲለጥቅ አንድ ጥያቄ ገረፍ አድርጎኝ ያልፋል።
ኪሩ ከዚህ ሁሉ አፍቃሪ ሴቶቹ መሀል እኔን እንዴት ሊመርጠኝ ይችላል?
ከኔ በላይ ቆንጆ ሴቶች ደግሞ አሉ። ልቤ ን ግን አያክሉትም...ልቤ ተራራ ነው። ማንንም ማንበርከክ ...ማንም እንዲያሸረግድልኝ የሚያደርግ ቅብዓ ቅዱስ አለኝ።
ሰለዚህ እሱን አማልሎ ወጥመዴ ውስጥ የማስገባበት ብልሀት ወጠንኩኝ...ትምህርት ቤት ስሄድ እሱን እንደምረታው ለራሴ እየነገርኩት ነው።
ንፁህ ታሸንፊያለሽ ! ብሎ የሚፎክር ጀብደኛ ልብ አለኝ።
ዶክተር ኪሩ መጣሁልህ !

(ይቀጥላል...)

@poetry_timeee
1.8K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:46:23 ሰላም ሰላም አዲስ ተከታታይ ታሪክ ሊጀመር ነው......
210 views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 12:39:43 'ባለቤቷ ሆንኩኝ'
__
አይነ ግቡ ባትሆን
ስሜት ባትሰጥም
በውበት አማላ
አፍዛ ባትጥልም
ሲያዩአት ባታረካ
አንጀት ባታርስም
የሚደነቅ ውበት
ሚስጥር ባይኖራትም
ቁመትሽ ሎጋ ነው
ባይባልላትም
ሰሙን ባትታቀፍ
ወርቁን ባታዝለውም
ባለቤቷ ሆንኩኝ
ለዚች አጭር ግጥም




ከወደዱት ያጋሩ

https://t.me/EdomGenetB
https://t.me/EdomGenetB
https://t.me/EdomGenetB

♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------
267 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 12:39:43 እኔ ቅብዝ ቅብዝብዚት
ችኩል ችኩልኩሊት
ወረት ወርትሪትሪት
አቋም አልባ ሽክርክሪት

ቀን ለሰላት የምፋጠን
ጎህ ሲቀዳድ የ'እግዜር መቅደሱን የማጥን።

ድንጉጥ ድንጉጥጉጢት
ፓስተር ይዞኝ መፅሀፍ ሲገልጥ
የጌታ ነኝ ብዬ ማቀልጥ።

እኔ ልጂት
ጅላ ጅሊት
ቂላ ቂሊት

ያዋቂ ቤት ተንበርካኪ
የ'አትሮንሱ ፊት ሰባኪ
ቀን የሚያምረኝ ቲሪኪሚሪኪ
ማታ ሚያምረኝ መጠጥ ዉስኪ
የማለዳዉ ቅዱስ ባሪያ
የከሰዓት የ'አላህ ባሪያ
የፓስተሩ አማካሪ
ድምብር ደምበርባሪ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
202 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 17:18:22 #መስታወት_ልግዛልሽ
:
:
መቼስ በዚች ዓለም፤
አምናለው አልክድም፣
የሰው ፍፁም የለም።


ሰው ስህተት ይሰራል፤
ከዚያም ይታረማል፤
ከስ'ተቱ ይማራል።


ያንቺ ግን ፍቅርዬ መሳሳትሽ ወዛ፤
በ'ኔና አንቺ መሀል ደርሶ ሰው ሳይበዛ፤
እየው ዕድሜ ላንቺ ፍቅራችን ጠነዛ።


ከሰራሺው ስህተት ትማሪያለሽ ብዬ፣በተስፋ ስጠብቅ ወይ ዛሬ ወይ ነገ፤
እንኳን ልትማሪ ጥፋትሽ ስር ሰዶ፣ቅርንጫፍ አውጥቶ ይባሱን አደገ።


እናምልሽ ፍቅሬ...
ትናንት በመቅረዜ ድንግዝ ብርሃን ይዤ፤
ሁሉን ላ'ምላክ ጥዬ እሱን ተመርኩዤ፤
አጣጥቤ ልኬሽ ጨቅይተሽ ስትመጪ፤
ፍቅርሽ እንዳይርቀኝ ከልቤ እንዳትወጪ፤
መውደድ አስገድዶኝ ዳግም እንደገና፤
አምጥቼልሽ ነበር ውሀና ሳሙና።


ዛሬ ግን ታከተኝ ዛሬማ በቅቶኛል፤
ጭቃሽን ለማንፃት ውሀ ምቀዳበት ጉልበቴም ከድቶኛል።


እናም ካሁን ወዲህ ለኔም እንዲቀለኝ፣ላንቺም እንዲበጅሽ፤
በሳሙና ፈንታ ጭቃሽን እንድታይ፣መስታወት ልግዛልሽ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

@EdomGenetB
@EdomGenetB
@EdomGenetB
273 views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 23:12:54 እሱን የሚቀድመው የለም!

ህይወቴ ባዶ ናት፣ ትርጉም የላትም፣ እንደበረሀ ደርቃለች ብለህ ተስፋ ልትቆርጥ ስትል አንጀት የሚያርስ መልስ የሚሰጥህ ፈጣሪህ አለ። ወዳጄ የዘገየ ይመስልሀል እንጂ እሱን የሚቀድመው የለም! አንተ ብቻ ታገስ!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@bmchannle
@bmchannle
Know join us
264 views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 18:23:09 ያቀን
እንደ ሰማይ ራቀን
እንደ ሞተ ዘመድ ናፈቀን
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ትርጉም ኖሮን ምንኖርበት
ምክንያት ይዘን ማንሞትበት
ህይወት ጣዕሟን ምናይበት
ነን ያልነውን ምንሆንበት
ያቀን....

ዛሬን ኖረን ነገን ጓግተን
አዲስ ጠዋት ተመኝተን
ከርሞችንን ሳንጠላው
እኛው እኛን ሳንጣላው
አሉ ሲሉን አለን ብለን
ባምላክ ፍቅር ተጠልለን
ለምን ብለን ሳንሞግተው
"እርሱት ሲሉን የምንረሳ"
ተውት ሲሉን የምንተው
ምንሆንበት.....

ካጀብ ማዕብል ተነጥለን
ሸክማችንን ላምላክ ጥለን
እኛን ሆነን እኛን መስለን
እንዴት ብለን ሳንጠይቀው
"ያልፋል ያሉት እያለፈ"
ሁሉን እግዜር እያወቀው
ምንኖርበት.....

ዕርስታችን ሳይታረስ
የዘሩትን ሳንለቅም
ገነት ደጇን ስንናፍቅ
ኗሪ አለምን ሳንንቅም
ላለመሞት አንዲት ምክንያት
ለመኖርም አንዲት ጥቅም
ምንይዝበት...

ያቀን
እንደ እናት ጡት ተነጠቀን
እንደበራች ፀሃይ ራቀን
እንዳባት ክንድ ተናፈቀን

[ ቶማስ ትግስቱ ]

@yourpoim
@yourpoim
257 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ