2022-08-27 10:32:36
#ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ እጅግ ትልቅ ስፍራ ያላቸው አንጋፋው እና ስመጥሩ የስፖርት ሳይንስ ባለሞያ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ፕሮፌሰር ዶ/ር በዛብህ ወልዴ በቀድሞው የኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ (በአሁኑ አጠራር የኮቴቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ) እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ትምህርት መምህር የነበሩና እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ
√ በአትሌቲክስ ስፖርት ሳይንስ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ባለሙያዎችን ያፈሩ፣
√ በስፖርት አስተዳደር ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተርነት፣
√ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ልዩ ልዩ አካዳሚያዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀት፣
√ በበርካታ ሚዲያዎች ለስፖርት ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ በሙያቸው ‹‹አንቱ›› ከተባሉ ምሁራን ጎራ ቀድመው የሚጠሩ ሰው ነበሩ፡፡
ዶክተር በዛብህ ወልዴ በቅርቡ አሜሪካን ሀገር በተካሄደው እና ኢትዮጵያ ውጤታማ በነበረችበት 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የልዑካን ቡድኑ አመራር እንደነበሩም ይታወሳል።የቀለም አባትነታቸውም የሚዘነጋ አይደለም።
ስርዐተ ቀብሩ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ 21/12/2014 አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል ከዛ በፊት በ 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አሸኛኘት ይደረግላቸዋል።
@poemmylove
202 viewsMeskerem Mekonen , 07:32