Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምን በዜማ📚🎻

የቴሌግራም ቻናል አርማ poembyton — ግጥምን በዜማ📚🎻
የቴሌግራም ቻናል አርማ poembyton — ግጥምን በዜማ📚🎻
የሰርጥ አድራሻ: @poembyton
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 284
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለእናንተ ይህ የናንተው ቻናል "ግጥምን በዜማ" ነው። በዚህ ቻናል የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ያገኛሉ።
ለማንኛውም አስተያየት @Firew1221

ግጥም መላክም ይቻላል /

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-07 21:53:12 አንዳንዴማ
"""""""""""""""


ሁኔታዎች
ደስ አይሉህም ያገልሀል ከሰው መንጋ ፣
በተመስጦ ብዙ እያሰብክ ታወራለህ ከራስህጋ ፣
ያለ ጩኸት ያለ ምላስ ፣
በዝምታ በለሆሳስ ፣
አንዴ ደስታ አንዴ ሀዘን አንዴ ፀፀት ፣
ለምን በሚል በአእምሮ ጥልቅ ጩኸት ፣
በንፋስ ላይ እየሳልከው ትዝታህን ፣
ስታደንቀው ስትነቅፈው ምግባርህን ።

አንዳዴማ

ሰውን ማየት ያስጠላሀል ብቸኝነት ይስብሀል ፣
ታለቅሳለህ ትስቃለህ ብቻ ሁሉን ያሰኝሀል ፣
ብቻ አንዳንዴ ትናፍቃለህ ራስህን ፣
በማስመሰል ሌላን ስትሆን ያጣኸውን ።

አንዳንዴማ

ሁሉን ነገር ስቆ ማለፍ ይደክምሀል ፣
ውስጥህ ያለ አንዳች ህመም ይሰማሀል ፣
ጭር ያለውን ትመርጣለህ ከሁካታ ፣
የራስህን መራር ሀዘን ከሀሰት ደስታ ።



#በረከትዘውዱ
90 viewsblessing_crown, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:06:32 ~አኩርፈኝ~
+++++++

አኩርፈህ አልይህ ሚል አይደል ምኞቴ
ኩርፊያውን አብዛልኝ የሚል ነው ፀሎቴ
እባክህን ፍቅሬ ስወድህ አኩርፈኝ
ይጋርድህ ደመናው ፍፁም ጥቆርብኝ፤

... አኩርፈኝ ...

ዝናብም ሚዘንበው ሲያኮርፍ አይደል ሰማይ
አኩርፍና ፍቅሬ ዶፍህን አዝንበው የፍቅርህን ሲሳይ
ናና አረስርሰኝ ጥርት ብለህ ታይ ቂሞችህ ይለፉ
ግን ጠንቀቅ በልልኝ እንዳይወስደኝ ጎርፉ ።

#ቱሪስትለገሰ

@yegtm_hywet
@amharic_poet
92 viewsblessing_crown, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:55:54 ለኔ ምን አርገሀል
"""""""""""""""""""""""""""""


ወይም እንደ ሙሴ ባህር አላቆምክም ፣
ደሞ እንደ ዳንኤል
የአንበሶቹን አፍ ዲዳ አላደረግክም ።

ለኔ ምን አርገሀል ዮናስን አርገኸኝ
ያሳ ነባሪው ሆድ ደልቶኝ አላደርኩም ፣
አልያ እንደ ሶምሶን
በአህያ መንጋጋ ሺውን አልገደልኩም ፣
በትሬን እንደ አሮን እባብ አላረኩት ፣
አላዛርን ሆኜ ሞቴንም አልሻርኩት ።

ብዬ እየወቀስኩህ

ሙሴ ባህር ቢያቆም ሶምሶን ሺ ቢገድል ፣
ለኔም ሰጥተኸኛል የነሱ አይነት እድል ፣
በትሬን እንደ አሮን ወደ እባብ ባልቀይር ፣
አላዛር አርገኸኝ የሞቴን ቀን ባልሽር ፣
ቀን ትሰጠኛለህ እንድፈፅም ገድል ።

መክሊቴን ባላገኝ ድርሻዬን ባልጠብቅ ፣
በቀረብከኝ ቁጠር እኔ ካንተ ስርቅ ፣
በይቅርታህ ብዛት በቸርነት አለም ፣
ያልጠበኩት እንጂ ያልሰጠኸኝ የለም ።

#በረከትዘውዱ

@yegtm_hywet
@amharic_poet
103 viewsblessing_crown, edited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 00:03:59 እሷን ላላገኛት ራሴን አጣሁኝ
መራር እውነት ትቼ
በአብረቅራቂ ውሸት ስሰቃይ ከረምኩኝ
እርግጥ ነው አልክድም
ልረሳት ፈልጌ ብዙ ሰው ቀረብኩኝ
ጉድለቴን ሸፍነው እሷን እንዲያስረሱኝ
እሷ ብትኖር ኖሮ ከሚል ምኞት አለም
ነጥቀው እንዲያወጡኝ
ቢሆን ኖሮ እያልኩ በቅዠት እንዳልኖር
በትናንት ህይወቴ ተቸንክሬ እንዳልቀር
አዲስ ሰው ለመድኩኝ
ቢሆን ኖሮን ትቼ የሆነውን ልኖር
እርግጥ ነው አልክድም
እርሷን ልርሳ ብዬ የማደርገው ነገር
ይበልጥ ሲያስታውሰኝ ባስ ሲል ሲጎዳኝ
በብዙ ህመሞች ስታገል ነበርኩኝ
ነበርኩኝ? ወይም ነኝ
ብቻ ግልጽ አይደለም
ቢሆንም
ጉዳቱ ጥልቅ ነው
ከቃል በላይ ሲሆን ህመም
እርግጥ ነው አልክድም
ትልቁ ስህተቴ አጉል ፍላጎቴ
እሷን ላላገኛት ራሴን ማጣቴ
ቢሆንም....።

ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)
118 viewsWho i'm i? , 21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:36:01 Check out የግጥም ህይወት: https://t.me/yegtm_hywet
125 viewsፍሬው ተካልኝ, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 22:01:05 ምን መሰለሽ አለም
ተይ ያንቺ እንዳልመስልሽ ከመክኖሽ ብገኝም።
ምን መሰለሽ መሬት
ስጋዬ በአፈርሽ ተዋቅሮ ቢሰራ፣
ስኖርም ብሰክን ከፍሬሽ ብጋራ።
ስጋዬ እምብርትሽ ውስጥ ይመለሳል እንጂ፣
እኔ ያንቺ አይደለው አቅልሽን አትፍጂ።

ግን እኔ ያንቺ ነኝ
የመኖሬ ህላይ በአንቺ ተወስኖ፣
ብትኖሪልኝ ኑሬ ባጣሽ ዕድሜ ባክኖ።
ለመኖር ተስዬሽ
በሞቴ ብዘክርሽ፣
ሁልጊዜ ላንቺ ነኝ እናቴ ልንገርሽ።

#Join_now @yene_eyta.

#ፍሬው_ተካልኝ
108 viewsፍሬው ተካልኝ, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 18:38:21 ዘንድሮም !!!!

""""""""""""""""""""""


አንድ ቀን እያልኩኝ
ወራቶች ተንደው አመት እንደሰሩ ፣
እልፍ አእላፍ ቀናት እንደተገበሩ ፣
ስንት መንፈቅ አልፎ ዛሬም ሄደ በጋ ፣
እንደተለመደው ሳልነግራት ተዘጋ ።

እኔ እንደምወዳት እሷ መቼ አውቃ ፣
እንዲሁ እያየኋት ሳልነግራት አበቃ ፣
ከበሯ ጀምሮ እስከ ትምሮ ቤት ፣
ደሞ ከትምሮ ስሸኛት እስከቤት ፣
ባይኔ ስከተላት፣
ከሩቅ ሆኜ ሳያት ፣
አንዴም ሳላወራት ፣
እንደ ዘበት ሄዱ እነዛ ዘመናት ።

ግድር አንደበቴን ስወቅሰው አስሬ ፣
ቃላት ላልተነፍስ ሲከተልሽ እግሬ ፣
ማፍቀሬን ደፍሬ ላላወራው ነገር ፣
ነገ ነገ እያልኩኝ ሀሳቤ ሳይሰምር ።

በቃ ተለያየን

የአምና አይነት ዘንድሮ እየተደገመ ፣
ልቤ እያፈቀረሽ ጥግ ይዞ እንደቆመ ፣
በሽታዬን ይዤ ፈውሴ አንቺ ርቀሺኝ ፣
ልክ እንደ ከችአምናው ሄደሻል ጥለሺኝ ።

ዘንድሮም ሳልነግርሽ
ልቻል ልታመመው ......

#በረከትዘውዱ


@yegtm_hywet
@amharic_poet
129 viewsblessing_crown, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 22:44:13 እውነትን ቀበርናት
ተባብረን ባንድነት
ነብስ እንዳትዘራ
ሀውልት አቆምንባት

ፍቅርን ፈለግናት
አንድ ሆነን ለመኖር
ሞክረን ሞክረን
ፈልገን ስናጣት
ፍቅር ድሮ ቀረች
ብለን ወሰንባት

እውነት ቀድመን ቀብረን
ፍቅር የለም ማለት
እውነት ገፍተን ጥለን
ፍቅርን መናፈቅ
ባቄላውን ዘርተን
ስጋ እንደመጠበቅ።

ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)
125 viewsB4 u go , 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 12:14:46 ቀይ አሻራ
""""""""""""


ነይ ሰውን እንትከል ፣
ና ትውልድ እንትከል ፣
አልወጣም የማይል ካልተንኳኳ በሬ ፣
ነግ በኔ ነው የሚል እኔ አለሁ ለሀገሬ ።


ዘመን ሲከረፋ ትውልድ ሲሆን ጭንጋፍ ፣
ችግኝ እየጣለ ገጀራ ያነሳል የሚያለማ መዳፍ ፣
ነፍስ ይጎዘጎዛል ማዳበሪያው ቀርቶ ፣
ደም ነው የሚጠጣው ውሀን አገር'ሽቶ ፣

ነይ ሰውን እንትከል ፣
ና ትውልድ እንትከል ፣
አልወጣም የማይል ካልተንኳኳ በሬ ፣
ነግ በኔ ነው የሚል እኔ አለሁ ለሀገሬ ።

እያለቅን ያለነው መች ሆነ በኦክስጂን ፣
የሚያገዳድለን የዘረኝነት ጂን ፣
መች እንጨት አጠረን ቤት የሚገነባ ፣
እንጨት ሲሰዱብን ቆስለን ስናነባ ።

ሁሉንም አደረግን መጥፎን እና ክፉ ፣
ይብቃን እስቲ መኖር ቂም እያተረፉ ፣
ደግ ነው የቀረን መልካሙን ረሳነው ፣
ፍርዳችን ላይጎድል ቢዘገይ ላንቀድመው ።

ቀይ አሻራ ይብቃን በአረንጓዴ ድንኳን ፣
የተከልነው ክፋት ሰው ነው የሚያሳጣን ፣
ያለውን ስንነቅፍ የሄደን ስንናፍቀው ፣
መኖር እያቃተን ተስማምተን እንደሰው !!

#በረከት_ዘውዱ


@yegtm_hywet
131 viewsblessing_crown, edited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:30:51 የግጥም ህይወት
ለግጥም አፍቃሪያን የተከፈተ ቻናል
103 viewsፍሬው ተካልኝ, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ