Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴማ ''''''''''''''' ሁኔታዎች ደስ አይሉህም ያገልሀል ከሰው መንጋ ፣ በተመስ | ግጥምን በዜማ📚🎻

አንዳንዴማ
"""""""""""""""


ሁኔታዎች
ደስ አይሉህም ያገልሀል ከሰው መንጋ ፣
በተመስጦ ብዙ እያሰብክ ታወራለህ ከራስህጋ ፣
ያለ ጩኸት ያለ ምላስ ፣
በዝምታ በለሆሳስ ፣
አንዴ ደስታ አንዴ ሀዘን አንዴ ፀፀት ፣
ለምን በሚል በአእምሮ ጥልቅ ጩኸት ፣
በንፋስ ላይ እየሳልከው ትዝታህን ፣
ስታደንቀው ስትነቅፈው ምግባርህን ።

አንዳዴማ

ሰውን ማየት ያስጠላሀል ብቸኝነት ይስብሀል ፣
ታለቅሳለህ ትስቃለህ ብቻ ሁሉን ያሰኝሀል ፣
ብቻ አንዳንዴ ትናፍቃለህ ራስህን ፣
በማስመሰል ሌላን ስትሆን ያጣኸውን ።

አንዳንዴማ

ሁሉን ነገር ስቆ ማለፍ ይደክምሀል ፣
ውስጥህ ያለ አንዳች ህመም ይሰማሀል ፣
ጭር ያለውን ትመርጣለህ ከሁካታ ፣
የራስህን መራር ሀዘን ከሀሰት ደስታ ።



#በረከትዘውዱ