Get Mystery Box with random crypto!

ያሳየሽኝ ሁሉ የነገርሺኝ ሁሉ አለም ነው ሚዳሰስ ገመና የለውም እንደ ሚስጥር መንፈስ። አንቺዬ | እግር ኳስ Meme™

ያሳየሽኝ ሁሉ
የነገርሺኝ ሁሉ አለም ነው ሚዳሰስ
ገመና የለውም እንደ ሚስጥር መንፈስ።
አንቺዬ
በቃል ችሎ መቆም
ለነብስ ውሎን መፆም እንዴት አወቅሺበት
ያደፈ ይነጣል አንቺ ካለፍሺበት።
አዎ
ብቻ እንደው......ግራ ቢገባኝ ውሉ
ነብስ ዘርቶ ታየኝ የቃልሽ ምስሉ
ታድያ
ካጠገቤም ሆነሽ ፍቅርሽን ናፈኩት
ከቃልሽ ቃል ይልቅ ልብሽን አመንኩት።
አንቺዬ
የነካውት........ ያስነካሺኝ
ያሸተትኩት........ የነገርሺኝ
ሁሉም እውነታ አለው..... በቃል ያዋየሺኝ።

በረከት(@berii34)

@yegetemkalat
@poem_merry