2023-01-28 12:29:34
እናምናለን!
“እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ … በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ።”
(የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ፤ 325 ዓ.ም)
“እርሱም ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ አምላክ፣ ከእናቱም በሥጋ በዓለም የተወለደ ሰው ነው።”
(የአትናቴዎስ የሃይማኖት መግለጫ፤ 4ኛው ክፍለ ዘመን)
“በአምላክነቱ ከዘመናት በፊት ከአብ በተወለደ፣ በዚህ መጨረሻ ዘመን በሰውነቱ ለእኛና ለድነታችን ከወላዲተ አምላክ ከድንግል ማርያም በተወለደ ...”
(የኬልቄዶን የሃይማኖት መግለጫ፤ 451 ዓ.ም)
. . .
(ማርቲን ሉተርንና ጆን ካልቪንን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያን ሓዳስያን በሙሉ እነዚህን የእምነት መግለጫዎች ይቀበላሉ።)
ከቤተ ክርስቲያን የተሓድሶ እንቅስቃሴ በኋላ የወጡትን የእምነት መግለጫዎችንም ማካተት ይቻላል።
“ከዘላለም በፊት ከአብ የተወለደ፣ እውነተኛና ዘላለማዊ አምላክ በሆነ፣ ... ከብፅዕት ድንግል ማኅፀን ውስጥ ከባሕርይዋ የሰውን ሥጋ የነሣ፣ የተጣመረ ...)
(1571 ዓም የአንግሊካን ቤ/ክ 39 አንቀጾች)
“ወልድ ከዘላለም ከአብ የተወለደ ...”
(1643-46 ዓ.ም የዌስትሚኒስተር የእምነት መግለጫ)
“ክርስቶስ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። በሥጋዌ ኢየሱስ ክርስቶስ ... ከድንግል ማርያም ተወለደ ...”
(1925 ዓ.ም ሳውዘርን ባፕቲስት ጉባኤ)
በዚህ ጉዳይ ትክክለኛውን አስተምህሮ ሳይገነዘቡ፣ ልከኛ አማኞችን የሚቃወሙ የክርስትና ጠበቆች መኖራቸው ያሳዝናል። እርግጥ ነው፤ የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ስለሆነ በዚህች አእምሮአችን ሁሉን መረዳት አንችልም። እግዚአብሔር ከመታወቅ በላይ ነውና የአእምሮአችንን አቅም ያልፋል። ነገር ግን ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብለው የሰጡን አባቶች ምን ምን እንዳስተማሩ ቢያንስ በአንቀጸ ሃይማኖት (በእምነት መግለጫ) መልኩ ያስቀመጡልንን መቀበል ካልቻልን እምነታችን ሐዋርያዊ እንዳልሆነ አጠራጣሪ አይደለም። አዎን፣ አንዳንዴ ባይገባንም መቀበል ይኖርብናል። I believe in order to understand ወይም faith seeking understanding የተባሉት የክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት መርሖች ከዚህ ጋር የሚሄዱ ናቸው። ለመረዳት ማመን ያስፈልጋል። ነገረ ነገሩ ባይገባንም፣ አምነን ለመረዳት መጣር አለብን። ይህን ሳያደርጉ፣ ተንደርድሮ ሌሎችን ሊተቹ መጣር ያሳፍራል።
https://t.me/PaulosFekadu
845 viewsedited 09:29