Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ዝሆን ድዳ አትሁን… የዝሆን ግልገል ከልደቱ ጀምሮ በትንሽ ቦታ ውስጥ እንዲሆን ይሰለጥናል | የኛ ግጥም ና ታሪክ

እንደ ዝሆን ድዳ አትሁን…

የዝሆን ግልገል ከልደቱ ጀምሮ በትንሽ ቦታ ውስጥ እንዲሆን ይሰለጥናል። አሰልጣኙ መሬት ላይ በተተከለ እንጨት ላይ የትንሹን ዝሆን እግር በገመድ ያስረዋል። ይህም የትንሹ ዝሆን የምቾት ቀጠና ነው። ትንሹ ዝሆን በመጀመሪያ አከባቢ ገመዱን ለመበጠስ ይሞክራል። ገመዱ ግን ጠንካራ በመሆኑ ትንሹ ዝሆን ገመዱን መበጠስ እንደማይቻል ይማራል። በገመዱ ርዝመት በተለካ አካባቢ ብቻ ተወስኖ መኖር ይማራል።

ዝሆኑ በቀላሉ ገመዱን ለመበጠስ የሚችልበት እድሜ ላይ ሲደርስም ለመበጠስ አይሞክርም። ምክንያቱም ገና በልጅነቱ ገመዱን መበጠስ እንደማይችል ተምፘልና። በዚህ መንገድ ትልቁ ዝሆን በጣም በቀጭን ገመድ መታሰር ይችላል።

ምናልባት ይህ አንተን ይገልፅህ ይሆናል። ልክ ዝሆኑን ባሰረው እይነት ቀጭን ገመድ አሁንም በምቾት ቀጠናህ ውስጥ ታስረህ ይሆናል። እነዚህ ያሰሩህ ቀጫጭን ገመዶች ደግሞ በልጅነትህ የተቀበልካቸው እንቅፋት የሆኑ እምነቶችና ምስሎች ናቸው። ይህ የሚገልፅህ ከሆነ መልካም ዜና አለ። ይኸውም የምቾት ቀጠናህን መለወጥ ትችላለህ። እንዴት ለዚህ ሶስት የተለያዩ መንገዶች አሉ፤

የምትፈልገውን እንዲገኘህ፤ እንደ ስራህና ነገሮች በፈለግከው መነገድ እያሄዱልህ እንደ ሆኑ ማረጋገጫና አውንታዊ የራስ ጋር ንግግር መጠቀም ትችላለህ።
የምትፈልገውን ስታገኝ፤ ስትሰራና ስትሆን ያለ አዲስ አስገዳጅ ኃይል ውስጣዊ ምስል መፍጠር ትችላለህ።
በቀላሉ ባህርይህን መቀየር።

እነዚህ አቀራረቦች ከአሮጌው የምቾት ቀጠናህ ያወጡሀል።