Get Mystery Box with random crypto!

አሳሳቢው የትምህርት ቤት ክሊኒኮች ጉዳይ! ——————————————————— ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ ። | ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒

አሳሳቢው የትምህርት ቤት ክሊኒኮች ጉዳይ!
———————————————————
ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ክሊኒኮች ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ ድንገተኛ የመፈንከት ወይም ሲወድቁ የመጎዳት ገጠመኞችን ለማከም፣ አልያም እንደ ስኳር ህመም፣ የነርቭ ህመም፣ ወዘተ… የመሳሰሉ የተለያዩ ህመሞች ያሉባቸው ተማሪዎች ላይ ድንገት ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ።

ሠሞኑን የገጠመችኝ ታካሚ የ 12 ዓመት ታዳጊ ናት። ልጅቷ በተለምዶ "የሚጥል በሽታ" እየተባለ የሚታወቀው ህመም (epilepsy) ተጠቂ ስትሆን፣ አስኮ አካባቢ የሚገኝ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ናት። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ ታዲያ ትምህርት ቤት ውስጥ ድንገት ራሷን ስታ ስትወድቅ ለስም ብቻ የተቋቋመው  እና ተማሪዎቹ እንደነገሩኝ እምብዛም ተከፍቶ አይተውት የማያውቁት የተማሪዎች ክሊኒክ እንደተለመደው ዝግ ስለነበረ አዝለዋት ከግቢ በመውጣት ወደ ህክምና ተቋም ሲሮጡ ትወድቅባቸውና እጇ ላይ ሌላ ጉዳት ይደርስባታል። ከነቃች በኋላ መንገድ ላይ የተጨመረውን መጀመሪያ ያልነበረ የአጥንት ጉዳት ለማሳከም ሌላ ውጣውረድ አስፈለገ።

የዕድል ጉዳይ ሆኖ እንጂ የልጅቷን አወዳደቅ እንደነገሩኝ ሙሉ በሙሉ ራሷን ስታ ስለነበረ ስትወድቅባቸው ጭንቅላቷ ከመሬት ጋር በመላተሙ ለጭንቅላት ደም መፍሰስ አደጋ የመጋለጥ ዕድሏ ሠፊ እንደነበረ ተረድቻለሁ። ወላጆቿ ለአጥንቷ ጉዳት ህክምና ሲያመጧት ምን ያህል ስሜታቸው ተጎድቶ እንደነበረም አትጠይቁኝ።

የልጅቷን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠው ይህ ክስተት የተፈጠረው የትምህርት ቤቱ ክሊኒክ በስራ ላይ ባለመገኘቱ እንደነበረ ሳስብ ግን ጉዳዩ በሐገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ለማስታወስ ወደድኩ። ለመሆኑ የትምህርት ቤት ክሊኒኮች አስፈላጊነታቸው ታውቆ በግብአት እና በባለሙያ ተደራጅተው አገልግሎቶች ስለመስጠት አለመስጠታቸው የሚከታተላቸው አካል ይኖር ይሆን?

ከእንደነዚህ አይነት አጋጣሚዎች ትምህርት መውሰድ ያስፈልጋልና ወላጆች ጉዳዩን ለመንግሥት ብቻ ከመተው ልጆቻችሁ የሚማሩባቸውን ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ክሊኒክ ለመገምገም ሞክሩ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
Follow us on:
YouTube: " Doctor Seid"
የቴሌግራም ቻናል: https://t.me/patientstories
የፌስቡክ ገፅ: የአጥንት ህክምና/Orthopedic Surgery (https://www.facebook.com/EthioOrthopedics/)