2022-05-16 14:44:23
#ዛሬ_የናቶች_ቀን_ነው_እንዴ?
የእናቶች ቀን ከ አመት 1ግዜ ብቻ ማሰብ አይከብድም?
ይከብዳል ምክንያቱም እናት ልጇን ስትወድ ወይም ስታከብር ቀን ስለሌላት ነው።
እናት ዛሬም ነገም ከነገ ወዲያም ልትከበር ልትወደድ የምትገባ ፍጡር ነች።
እናት ለልጇ ያላት ፍቅር ዘላለማዊ ነው።
ትላንት ገና ህፃን እያለህ ምላስህ እየተኮላተፈ ቃላቶችን አገጣጥመህ መናገር ሳትጀምር የምትሳሳልህ እናትህ ዛሬም ፍቅሯ ያው ነው አልተለወጠም። ዛሬም አድገህ የራስህን ህይወት ጀምረህ እንኳን እናት ስላንተ ማሰብና መጨነቅ አላቆመችም። አንተ ግን ዛሬ ከአመት አንዴ ፍቅርህን ትገልፅላታለህ
ከአመት አንዴ ፎቶዋን ለጥፈህ እናቴ እወድሻለሁ ትላታለህ ድንቄም መውደድ።
እናትህን ከወደድክ ሁሌም ውደዳት ሳትሰለች በየቀኑ ፍቅርህን ግለፅላት።
በቃላት ሳይሆን በተግባር አሳያት። ፍቅር ቃላት ሳይሆን መሆን ነው።
እናትህ ላንተ ስትል ወጣትነቷን ውበቷን እድሜዋን ገብራለች፣ ስላንተ የደም ላብ አልባለች። ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀጥላ ስላንተ ህይወት ስትል ትልቅ ዋጋን የከፈለች እናትህ ናት። በተለይ በችግርና ብድህነት ተሰቃይተው ያሳደጉን እናቶች ስለልጆቻቸው የከፈሉትን ስቃይና መከራ ሁሌም ሊረሳ አይገባም
ስለዚህ አንተም (አንቺም) እሷን ሆነህ ለሷ ያለህን ፍቅር አሳያት።
በቃ ለኔ የእናቶችን ቀን ማክበር ያ ነው።
ፍቅራችንን በቃላት ሳይሆን በተግባር እንግለፅላቸው።
786 views11:44