Get Mystery Box with random crypto!

የኔስ ማኩረፊያዬ! የእኔስ ማኩረፊያዬ! የኔስ የቁጭት መርዶ መጽናኛዬ ፣ የከባድ ኀዘኔ ጭነትና | "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

የኔስ ማኩረፊያዬ!
የእኔስ ማኩረፊያዬ! የኔስ የቁጭት መርዶ መጽናኛዬ ፣ የከባድ ኀዘኔ ጭነትና የጭንቀቴ መክፈያዬ፣ የደስታዬ መፍሰሻ፣ የብስጭቴ ማርከሻ ፣የእልሄ መታገሻ፣ እኔስ ያላንቺ ማን እናት አለኝ??አንቺው ነሽ እንጉርጉሮዬና ዜማዬ!!
እናት ዓለም የስሜ ዐርማ ፣የሕይወት ወዝ፣ የዓይኔ ማማ፣ የማትነፍጊ፣ የማታቅማሚ ፣ረኀቤን የምትራቢ፣ ጥማቴን የምትጠሚ፣ ቁስሌን የምትታመሚ።
የዘመን ቅርስ መክሊቴ!
የጌታዬ እናት እመቤቴ!
የሐዲስ ኪዳን መሠረቴ!
ቸሪቱ፣አዛኝቱ ፣አማላጅቱ ማርያም እወድሻለሁ!!