Get Mystery Box with random crypto!

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የከተማው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የከተማው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጎን መሆናቸውን አሳወቁ።

የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን  የሚደግፍ ምክክር አካሒደዋል።

የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ምክክር  በከተማው የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሃይማኖት ተወካዮች በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ክስተት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

ቤተ ክርስቲያን ወደ ቀድሞው ሰላም እስክትመለስ ድረስ ሁሉም ቤተ እምነቶችና ምእመናን  በጾምና በጸሎት ከኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚሆኑ  አሳውቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩም ቅዱስ ሲኖዶሱ በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሠረት የሚጠይቁት ጥያቄ  እስኪመለስ ድረስ በማንኛውም ነገር  ከኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ኅብረተሰቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሰላም ማስከበር ሥራውን አጠናክሮ በማስቀጠል  እንግዳ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጎን በመሆን የተለመደ ተግባሩን ሊያከናውን እንደሚገባም ተገልጿል። ዘገባው የአርባ ምንጭ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።