Get Mystery Box with random crypto!

አስቸኳይ መረጃ፡፡ በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾሙት | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

አስቸኳይ መረጃ፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾሙት አካላት በጥር 27/2015 ዓ/ም እንደሚመጡ በቂ መረጃ ለሕቡ ሰለደረሰ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ከሕገ ወጦች ወረራ በንቃት እንዲጠብቁ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ መዋሉ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል፡፡

ከቀኑ 11፡45 ስዓት ላይ የመጡት ሕገወጥ ቡድን ለመንግሥት አካል እንደማይመለሱ ሲነግሩት ሙሉ ወጪ ችሎ እንዲያድሩ አድርጓል። በዚህ መሀል 10 የማይሞሉ ዱላ ይዘው እየዘፈኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ እነሱን ትቶ ቤተክርስቲያ እየጠበቁ ባሉት ላይ ተኩስ ተከፈተ።

በተኩስና አስለቃሽ ጭስ እስከ 2ስዓት ምዕመናን ሲያዋክብም አምሽቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ከበው ህዝቡን በተኩስ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ በዱላ እያሰቃዩ ሙሉ ህዝቡን እንዳስወጡና የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች ሞታችን በልደታ ብለው ግቢ ውስጥ ቀርተዋል፡፡

እስከምሽቱ 4ስዓት ላይም ቤተክርስቲያን ማን እንደሚገባ መመሪያ ከመንግስት እንጠብቃለን ብለው ከቆዩ በኋላ እና 5 ሰዓት ላይ ከሆቴል ጠርተው ሕገወጡን ቡድን አስገብተዋል፡፡ የጸጥታ እና የመንግስት አካላት ዛሬ እሑድ 4ስዓት ተደራደሩ ወይም ለሕገ ወጡ ቡድን ንብረት አስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ይገኛሉ።
አባቶች ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የምንመራ እንጂ በግል ምንወስነው አይደለም ብለዋል።

የጸጥታ ኃይሎች ተደራድረው ገብተዋል ለማለት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የመምሪያ ኃላፊዎችን አስገድደው ፎቶ ለማንሳት ሲሞክሩ እንደነበረ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መረጃውን ያደረሱን ገልጸዋል።