2022-04-22 05:07:16
እንኳን ለጌታችን
ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ::
አርብ
ትልቁና ድንቁ ቀን እለተ አርብ።በሕማማት ሳምንት ውስጥ ያለው አርብ "ስቅለት "ተብሎ ይጠራል።ኢየሱስ ክርስቶስ በወታደሮች ከተያዘ ጀምሮ ነፍሱን እስከሰጠበትና ወደመቃብር እስከወረደበት ድረስ በዚህ እለት የተፈጸሙት ድርጊቶች ይታሰባሉ። በአራቱም ወንጌላትም ተጽፎ ይገኛል።
1. ጌታችንን ሐሙስ ማታ 3:00 ከተያዘበት ጀምሮ ወደ ካህናቱ አለቃ ግቢ ወስደው እስኪነጋ ደበደቡት
2. ንጋት 12 ሰአት ላይ ወደ ሸንጓቸው አቅርበውት በሐሰት ከሰሱት
3. ጠዋት 3:00 ላይ በጲላጦስ የፍርድ ወንበር ፊት ገትረውት የሐሰት መአት ክስ አወረዱበት
4. ጲላጦስ ምንም አላገኘበትምና ወደ ገሊላ ሐገረ ገዥ ሔሮድስ ዘንድ ላከው
5. ሔሮድስም በንቀት አናገረው የንግስና ካባውንም አልብሶ አፌዘበት።መልሶም ወደ ጲላጦስ ላከው
6. ወታደርች በአራት መአዘን አንገቱን አስረው እያንገላቱ አመላለሱት።እጅግ ብዙ ጊዜ እየወደቀ ተነሳ
7. ጲላጦስ ድጋሚ አገኘውና ምንም ስላልተገኘበት ገርፌ ልልቀቀው ብሎ በአደባባይ አስገረፈው
8. ወታደሮች እጃቸው እስኪዝል ጅራፍ የያዙበት እጃቸው እስኪቆስል ደበደቡት
9. በተራ በተራ እያረፉ ገበጣ እየተጫወቱ ከ6666 በላይ ጊዜ ገረፉት: ደሙ ጎረፈ ስጋው እየተቆረሰ ወደቀ: አጥንቱ ሁሉ ታየ ነጭ ስጋው ታየ: ደም ግባቱ መለየት እስካይቻል ጠፋ "እንወደው ዘንድ ደምግባት የለውም "የተባለው ትንቢት ተፈጸመ
10. አይሁድ አልረኩምና ሕዝቡን በጌታ ላይ አሳመጹ: "ክርስቶስ ስቀለው በርባንን ፍታልን "እያሉ ጮሁ
11. ጲላጦስ ስህተትም ስላላገኘበት ሚስቱም(አውሮቅላ ትባላለች) ከሌላ ቦታ አትፍረድበት ብላ ካየችው ህልም ጋር መልእክት ጽፉ ስለላከችለት ሊፈርድበት ባይፈልግም ህዝቡ ሁሉ ሲጮህበት "እኔ ከዚ ሰው ደም ነጻ ነኝ ወስዳችሁ እንደ ህጋችሁ አድርጉት አያገቤኝም " በማለት እጁን ታጥቦ በርባንን ፈቶ ክርስቶስን አሳልፎ ሰጣቸው።
12. እርጥብ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ ወደ ቀራንዮ ጎለጎታ ጉዞ ተጀመረ
13. ቀይ ልብስ አልብሰው: የእሾህ አክሊል ደፍተው ዘንግ አሲዘው ዘበቱበት
14. መንገድ ላይ ደበደቡት:ገፍትረው ጣሉት: ወደቀ ተደፋ:ተነሳ: ምራቃቸውን ተፉበት: እናቶች አለቀሱ: ከቀሬና የመጣ ስምኦን የተባለ መስቀሉን በመሸከም አገዘው: አንዲት ሴት ደሙን ከፊቱ በነጭ ጨርቅ ጠረገች።ፊቱን የጠረገችበት ጨርቅም የጌታን የፊቱን ስእል ያዘ።(አውሮቅላ የጲላጦስ ሚስት ናት(ቬሮኒካም እንደሆነች ይነገራል)
15.በስድስት ሰአት በመስቀል ቸንክረው ከሁለት ወንበዴዎች መሀል ሰቀሉት
16. ልብሱን እጣ ተጣጥለው ወሰዱት
17. በመስቀል ላይ ሳለ ተሳለቁበት: ሆምጣጤ አጠጡት: ጎኑንም በጦር ወጉት
18. በመስቀል ሆኖ 7 ታላቅ ቃላትን ተናገረ: 7 ታላላቅ ተአምራትም ተፈጠሩ
19. በመስቀል ላይም ከ6-9 ሰአት ብዙ ከተሰቃየ በዋላ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጠ
20. ዮሴፍ ዘአርማትያስና ኒቆዲሞስ በ11:00 ላይ አውርደው ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት
(ማቴ 26፥57 ሜቴ 27፥61 ማር 14÷53 ማር 15÷45 ሉቃ 22÷54 ሉቃ 23÷56 ዮሐ 19÷32...)
13ቱ ሕማማተ ደረሱበት
1. ተኮርተ ርእስ/ራሲን መመታቱ
2. አክሊለ ሶክ/የሾህ አክሊል መድፋቱ
3. ተአስሮ ድህሪት/የዋሊት መታሰሩ
4. ሰትየ ሐሞት/ሐሞት መጠጣቱ
5. ወሪቀ ምራቅ/ምራቅ መትፋታቸው
6. ተቀስፎ ዘባን/ጀርባውን መገረፉ
7. ጸዊረ መስቀል/መስቀል መሸከሙ
8. ተጸፍኦ መልታህት/በጥፊ መመታቱ
9. በሳዶር ቀኝ እጁን መቸንከሩ
10. በአላዶር ግራ እጁን መቸንከሩ
11. በዳናት 2 እግሩን ከመስቀል ጋር ቸነከሩት
12. በአዴራ መሐል ልቡን ቸነከሩት
13. በሮዳስ ደረቱን ቸነከሩት
7 ታላላቅ ተአምራት ከ6-9:00 ታየ
1. ጸሐይ ጨለመች
2. ጨረቃ ደም መሰለች
3. ከዋክብት ረገፉ
4. አለቶች ተሰነጣጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነስተው ታዩ
7. የቤተመቅደስ መጋረጃ ተቀደደ
ከሁሉም ትልቁ ተአምር የማይሞተው መሞቱ ነው እስካሁንም በአህዛብ ዘንድ መታመን ያልቻለ ሀቅ።
በነገራችን ላይ ጎኑን የወጋው ሌንጊኖስ ከጎኑ በፈሰሰው ደምና ውሀ እውር የነበረው 1 አይኑ ተፈውሶለት በጌታ አምኖ በሰማእትነት ሞቷል። ከመጀመሪያውም ጀምሮ ለጌታ ሲቆምለት የነበረው ለስልጣኑ ሲል ብቻ ጌታን አሳልፎ ሳያምንበት አለፍቃዱ የሰጣቸው ጰንጠናዊው ጲላጦስም ከትንሳኤው በሁዋላ ሊቃነ ካህናትና የመቃብሩ ጠባቂ የነበሩት ወታደሮች ትንሳኤውን መደባበቃቸውንና ሐዋርያት እንደሰረቁ ማስወራታቸውን ጌታ ግን የእውነት መነሳቱን ሲሰማ እርሱም አምኖ ተገድሏል
በዚህ እለት በቤተክርስቲያን በየሰአቱ የሚሰበኩ ምስባኮች
1:00 መዝ 35÷1
3:00 መዝ 22÷16
6:00 መዝ 69÷21
9:00 መዝ 143÷6
11:00 መዝ 143÷3
https://t.me/ortodoksawimezmur
300 viewsedited 02:07