Get Mystery Box with random crypto!

💠ኦርቶዶክሳዊ ህይወት💠

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxy_eywet — 💠ኦርቶዶክሳዊ ህይወት💠
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxy_eywet — 💠ኦርቶዶክሳዊ ህይወት💠
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxy_eywet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ተዋህዶ ሆይ ፣ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፣ ባላስብሽ ፣ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ።
#Share በማድረግ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ !

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-02 09:03:08 +++ "ለዚህ መቼ ጸለይን?" +++

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰባዊ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲረዳ የተቋቋመ የካህናት (የቀሳውስት) ጉባኤ ነበረ። የቀድሞው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳም ይህን ስብስብ እንዲቀላቀሉ ለአባ ሚካኤል ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት የዚህ ጉባኤ አባል ሆኑ። ታዲያ አንድ ቀን አባ ሚካኤልን ጨምሮ የጉባኤው የበላይ ኃላፊ የሆኑት ጳጳስና ሌሎችም ካህናት የተጣሉ ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ተሰበሰቡ። ይሁን እንጂ የባልና የሚስትየው ጠብ እንዲህ በቀላሉ ሊበርድ የሚችል አልነበረምና ጳጳሱም ሆኑ ቀሳውስቱም ሁለቱን ለማስማማት ብዙ ቢጥሩም ግን አልተሳካላቸውም።

በስተመጨረሻም ጳጳሱ ወደ አባ ሚካኤል እየጠቆሙ "አባ ሚካኤል ለምን ዝም ብለው ተቀመጡ? እስኪ እርሶ ይሻላል ብለው የሚያስቡትን ይንገሩን?" አሏቸው። አባ ሚካኤልም "ብፁዕነትዎ፣ እንጸልይበት!" አሉ። ጳጳሱም "ይህን ጉባኤ ከመጀመራችን በፊት እኮ ጸልየናል" ቢሏቸው አባ ሚካኤል "አዎን አባታችን፤ ለዚህ ችግር ግን አልጸለይንም" አሉ። ከዚያ ሁሉም ለጸሎት ተነሡ። በጳጳሱ ፈቃድ በአቡነ ሚካኤል መሪነት ጸሎት አደረጉ። ጸሎቱ እንዳለቀም እነዚያ የተጣሉት ባልና ሚስት ክርክራቸውን ሁሉ ትተው በጉባኤው ፊት በፍቅር ተቃቀፉ። ሰላም አወረዱ። ይህን ጊዜ ከቀሳውስቱ አንዱ "አባታችን ከመጀመሪያ እንዲህ ቢሉን ምን ነበር?! አሳረፉን እኮ" ብለው ጉባኤውን ፈገግ አሰኙት።

እኛስ ያልጸለይንባቸው ስንት ችሮች አሉብን?

ብዙ ቋጠሮ የሚፈታው ግን በብዙዎች የሚረሳው ትልቁ መፍትሔ፣ ጸሎት!!!

(አባ ሚካኤል ኢብራሂም (1899-1975) የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉና እጅግ የሚያስቀና የጸሎት ሕይወት የነበራቸው አባት ናቸው። በእርሳቸው ጉዳይ ከሰሞኑን መመላለሳችን አይቀርም።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ

@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
2.4K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:34:47 ኦርቶዶክሳዊ ህይወት pinned a photo
18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:24:56 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
           #ተዝካራ_ለጽዮን_ማርያም _(ኅዳር ፳፩)
    እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ ካሻገራቸው በኋላ በደብረ ሲና ተራራ ታቦተ ጽዮንን ሰጥቷቸዋል፤ (ዘጸ 12፥51 ፣ ዘጸ 31፥18 ፣ ዘጸ 34፥1)፡፡ ፵ ዘመን ሙሉ መና ከደመና አውርዶ ውኃ ከጭንጫ አፍልቆ እየመገበ በሙሴ ምትክ ኢያሱን በአሮን ምትክ አልዓዛርን ሰጥቶ ምድረ ርስት አገባቸው፡፡ ከዚያ መስፍን ሲሞት መስፍን ካህን ሲሞት ካህን እያስነሳ ከዔሊ ደረሰ፡፡ ዔሊ ክህነት ከምስፍና ይዞ ፵ ዘመን አስተዳድሮ ሲደክም አፍኒንና ፊንሐስ የተባሉ ልጆቹን የበላይና የበታች አድርጎ ሾማቸው፡፡ የዔሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩና በዔሊ ሥርዓት አልተጓዙም፤ በፊት የነበረውንም ሥርዓት አጠፉ፡፡ ካጠፉት ሥርዓት የተወሰኑት ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡፡
1. በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርቶ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የሚጠፋ የደብተራ ኦሪት የሙሴና የአሮን ሥርዓት ነበር፤ ምን ያደርጋል ብለው አስቀርተዋል፡፡
2. መሥዋዕት የሚሠው ሰዎች ሲመጡ ከታረደው ስጡን ይላሉ፤ መሥዋዕት አቅራቢዎቹም ‹‹መጀመሪያ ስቡ ይጢስ፣ ደሙ ይፍሰስ ዐጥንቱ ይከስከስና ከዚህ በኋላ የወደዳችሁትን ታደርጋላችሁ›› ሲሏቸው ‹‹ብትሰጡን ስጡን ባትሰጡን በግድ እንወስዳለን›› እያሉ ብልት ብልት ስጋ እየነጠቁ ይወስዱ ነበር፡፡
3. ጽዮንን  መቃጠሪያ አደረጓት፤ ሴቶችም ይህንማ መቼ ከባሎቻችን አጣነው ብለው ቀርተዋል፡፡
   ዔሊም ይህን ሰምቶ ‹‹ልጆቼ የምሰማባችሁ ይህ ነገር መልካም አይደለም፤ እንዲህ አታድጉ ሰውስ ሰውን ቢበድል በእግዚአብሔር ያስታርቁታል ሰው ግን ከእግዚአብሔር ጋራ ቢጣላ በማን ያስታርቁታል? ተው›› አላቸው፤ ልጆቹ ግን አልሰሙትም፤ (1ሳሙ 2÷22-26)፡፡ በቤተ መቅደስ ውስጥ ጽዮንን ለሚያገለግል ለሳሙኤል እንደነገረው እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ጦርነት ገጥመው ድል ኾኑ፡፡ እነሱም ‹‹ታቦተ ጽዮንን ባንይዝ ነው›› አሉ፡፡ እግዚአብሔር የአፍኒንና ፊንሐስ ሞት ፈቃዱ ነውና ታቦተ ጽዮንን ይዘው አብረው ዘመቱ፡፡ አሕዛብም እልልታውን ሰምተው ‹‹ወዮልን የእስራኤል አማልክት መጡብን›› ብለው ተጨነቁ፡፡ ነገር ግን አሕዛባውያኑ በድፍረት ጦርነቱን ገጠሙ፡፡ በጦርነቱም አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ታቦተ ጽዮንም ተማረከች፡፡ እስራኤል ከቀድሞው የበለጠ ፴ ሺህ እግረኞች አለቁ።

በዚህም ካህኑ ዔሊ በደብተራ ኦሪት ፊት ለፊት በወንበር ላይ ተቀምጦ የታቦተ ጽዮንን ነገር ያወጣ ያወርድ ነበር፡፡ ከዚያም አንድ የብንያማዊ ሰው ልብሱን ቀዶ እየሮጠ ሲመጣ ዔሊ ‹‹ከወዴት መጣህ?›› ብሎ ቢጠይቀው ‹‹ትናንት ከሰልፍ አምልጨ የመጣሁ ነኝ›› አለው፡፡ ከጦርነቱ አምልጦ የመጣው ብንያማዊም ለዔሊ ልጆቹ እንደሞቱ፣ እስራኤላውያን እንዳለቁና ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች ነገረው፡፡ ዔሊም ‹‹ልጆቼ ብመክራቸው እንቢ ብለዋል ታቦተ ጽዮን ግን እንዴት ትማረካለች?›› ብሎ አለቅሳለሁ ሲል ከወንበሩ ወድቆ ሞቷል፡፡ ‹‹ዔሊ የ፺፰ ዓመት ሽማግሌ ነበርና ከወንበሩ ወደቀ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ›› እንዲል (1ሳሙ 4÷9-18)።
   
   ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ወደ አዛጦን ወስደው በዳጎን አጠገብ አድርገው ሄዱ፡፡ በነጋታው ሲገቡ ዳጎን በግንባሩ ወድቆ አገኙት፤ እንደነበረው አድርገውት ቢሄዱም አሁንም በነጋታው ሲመለሱ እጅ እግሩ ተቆራርጦ ደረቱ ቀርቶ አገኙት፡፡ ከዚያ ታቦተ ጽዮንን ወደ ጌት ሰደዷት፤ ከዚያም ወደ አስቀሎና ኢሎፍሊ እየተዘዋወረች ለሰባት ወር ከተቀመጠች በኋላ ባደረገችው የኃይልና የመቅሰፍት ተአምር ቀንበር ያልተጫነባቸው ላሞች ጠምደው በአዲስ ሠረገላ ጭነው ካሳ ወርቅ ሠርተው ላኳት፡፡ ላሞቹም ያለ ነጅ ወደ እስራኤል ሀገር አምጥተው በቤትሳሚስ ከኢያሱ እርሻ አጠገብ ደርሰው ቆሙ፡፡ የቤትሳሚስም ሰዎች ሠረገላውን ፈልጠው ላሞቹን አርደው መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያ ወደ አሚናዳብ ቤት መጥታ ልጁ አልዓዛር እያገለገላት ዳዊት እስኪያመጣት ድረስ በዚያው ሃያ ዓመት ተቀምጣለች፡፡ ከዚያም ታቦተ ጽዮን ከአሚናዳብ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ (እስራኤል) በዳዊት የንግሥና ዘመን ተመልሳለች፤ (2ሳሙ 6፥1-19)፡፡

    በተጨማሪም ነቢዩ ዘካርያስ ጽዮንን በተቅዋመ ማኅቶት አምሳል ያየበት፣ ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የገባበት፣ በዮዲት ጉዲት ጊዜ በዝዋይ ደሴት ከ፵ ዓመት በላይ ቆይታ ሰላም ሲሆን ተመልሳ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ እንዲሁም አብርሃና አጽብሐ በአክሱም ከተማ ከ፫፻፴፮-፫፻፴፱ ዓ.ም ቤተ መቅደሱን ሠርተው ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት ስለሆነ የበዓሉ መታሰቢያ ኅዳር ፳፩ ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን!
(ውድ አንባቢያን ስለ ዔሊ ልጆች ጥፋት እና ስለ ታቦተ ጽዮን መማረክ ሙሉውን ታሪክ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ከምዕራፍ ሁለት እስከ ምዕራፍ ሰባት ያለውን ያንብቡት)፡፡

               ወስብሐት   ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መድበለ ታሪክ

@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
4.6K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:15:43
ህዳር 21 እንኳን ለጽዮን ማርያም አመታዊ በዓል አደረሰን።

፨፦ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ መሸሸጊያ ማለት ነው።

1ኛ ቀደምት በአሉ በ1ኛ ሳሙኤል 4-:-1-22
በምዕራፍ 5-:-1-12 ላይ ይገኛል እስራኤልና  ፍሌስጤማዊያን ሊዋጉ ወጡ ፍልስጤማዊያን የእግዚአብሔርን ታቦት ተማርከውም ወስደው።

ዳጎን/ጣኦት/አጠገብ አስቀመጡ።ማልደው በጠዋት ስመጡ ዳጎን ወድቆ ተሰባብሮ አገኙት።

፧፧፧ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ውጭ ያላችሁት ሰውች የእግዚአብሔር ታቦትንና ጣኦትን ለዩ።

እግዚአብሔርን ልቦና ይስጣችሁ/
፨ጽዮን ማለት ለአዲስ ኪዳን ለፍፆሜው ለእመቤታችን የተነገረ ነው።
መዝሙር 88-:-5 ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል።በውጧም ሰው ተወልዷል።
፧፧፧፧፧፧የጽዮን ማርያም በረከቷ ይደርብን፧፧፧፧፧፧

@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
1.8K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 07:46:31 https://youtube.com/shorts/UJj4Lt6u6jA?feature=share
710 views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 22:38:17 ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ  ። የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው  ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው ቁርአን በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....read more

ትምህርቱ ተከታታይ ክፍል ተጀምሯል።
595 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 22:06:04 ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ  ። የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው  ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው ቁርአን በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት.....read more

ትምህርቱ ተከታታይ ክፍል ተጀምሯል።
650 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 14:05:47 '' እንደ እኔ የማርከው ''


እንደኔ የማርከው ማንን ነው
እንደኔ ይቅር ያልከው ማንን ነው
ሀጢያቱ በዝቶበት በደሉ በዝቶበት
የማርከው እንደኔ ከቶ ማነው/2/



በሞገስ አስጊጠህ በዜማ ቃኘኸኝ
ፊትህ ምታቆመኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ
ለኔ ያደረከው አቤት ደግነትህ
ምረኸኝ ምረኸኝ አያልቅም ምህረትህ
        አይተኸኝ በምህረት/2/
        ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ__

የምስጋና መስዋዕት ማቅረቢያ መሰዊያ
ልቤ ንጹህ ባይሆን ጸጋዬን አለቀማህ
ትቀበለኛለህ ሞልተኽ በጎደለው
እኔን የወደደ እንዳንተ ማን አለ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ__

በምኞት ተስቤ ለሀጢያት ተሽጬ
በመስቀልህ ስራ ከሞት ጣር አምልጬ
አንተ እንዳዳንከው ሰው መሆን ቢያቅትም
እኔ ተስፋ ብቆርጥ ተስፋ አትቆጥርብኝም
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬ አለሁኝ በህይወት

አዝ___

በኖርኩበት ዘመን የቁጣ ልጅ ሆኜ
ምዕራፉ ተዘጋ በአንተ በአዳኜ
ከኔ ምንም ሳይኖር አንተ ሁሉን ሆነህ
ሰገነት ታየሁኝ ስለኔ ተንቀህ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬም አለሁኝ በህይወት

አዝ___

እኔን ማረኝ ከምል ከፊትህ ወድቄ
በሌላው ፈራጅ ነኝ እራሴን አጽድቄ
መመልከት ባልችልም የአይኔን ምሰሶ
ያኖረኝ ፍቅርህ ነው ይህ ሁሉ ታግሶ
         አይተኸኝ በምህረት/2/
         ዛሬም አለሁኝ በህይወት


ለመቀላቀል

@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ


| ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
2.4K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 22:01:22 አዲስ የንስሐ ዝማሬ "የመዳን ቀን ዛሬ" በዘማሪ ዲ/ን አክሊሉ

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።


613 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 10:09:21
~አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ~
990 viewsedited  07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ