Get Mystery Box with random crypto!

ORACLE OF CHRIST

የቴሌግራም ቻናል አርማ oraclekb — ORACLE OF CHRIST O
የቴሌግራም ቻናል አርማ oraclekb — ORACLE OF CHRIST
የሰርጥ አድራሻ: @oraclekb
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 943
የሰርጥ መግለጫ

ወንጌል ለሁሉም!!!
“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4
@oracleKB

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-04-28 20:42:05 እፎይታ

ክፍል ሁለት

#እነማን እየጠበቁን ይሆን?"

“ወዳጅ ምንጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።”
— ምሳሌ 17፥17 (አዲሱ መ.ት)

@OracleKB
1.7K views✞ቃለ-አብ✞, edited  17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 07:36:18 #ስንፍናን_እንደ_አቋም......

ቤት ውስጥ ማንኛውም ስራ መስራትን በተመለከተ ስንፍና አለብኝ። የመጀመሪያው ምንም አይነት የቤት ስራ ሰርቼ (በቅብጠት ሳይሆን በአጋጣሚ ) ባለማደጌ ሲሆን፥ ሁለተኛው ለመማርም ራሴን አለማዘጋጀቴ ነው። ስንፍና እንዳለብኝ ለመቀበል በዚህ አቅጣጫ ክፍተቴን ተቀብዬ ራሴን ለመለወጥ መነሳት እንዳለብኝ ተቀብያለሁ። ለዚህ ምንም አይነት ምክንያት አያስፈልግም በትንሹም ቢሆን ለመለወጥ ራስን ማዘጋጀት እንጂ።

በግል ህይወታችን፥ በቤተሰባችን፥ በስራችን ወዘተ ስንፍና ካለ የእድገት ጸር የሆነ ካንሰር አለብን ማለት ነው። አብሶ ደግሞ በቤተክርስቲያን ስራ ውስጥ ስንፍና ካለ፥ ለስንፍናችን ምክንያት ደርዳሪነት ካለ ማፍራት ማደግ የምኞት ጉዞ ነው።

ስንፍናን እንደ አቋም የምንይዝባቸውን መንገዶች ካልቀየርን ራሳችንንም አገልግሎታችንም መለወጥ አንችልም። ማንኛውም አይነት ስፍንና ስሙ ስንፍና ነው። በተለያዩ የህይወትና አገልግሎት አቅጣጫ ብዙ አይነት ሰነፍ ሰዎች እና አገልጋዮች ያጋጥሙኛል፤ መንጋቸውን ለመመገብ ዕለት ዕለት የማይተጉ፣ የማያነቡ፣ የማይጸልዩ፥ መንጋቸውን ለማገልገል ዝግጅት የሌላቸው፥ በትክክለኛው አመራር ብቃት ለማሳየት ራሳቸው ላይ የማይሰሩ፣ መደላደልና የምቾት ቀጠናን እንደ ስኬት የሚቆጥሩ፥ ከጌታ የተቀጠሩለትን አገልግሎት እንደው ዝም ብለው የሚከናውኑ፥ ለስንፍናቸው መንፈሳዊ መሳይ አቋም የገነቡ፥ የሚተጉ ሰዎችን የሚገፉ ወይም በሚተጉ ሰዎች ስራ ውስጥ የሚሸሸጉ ስንፍናን እንደ አቋም፥ አቋማቸውን መንፈሳዊ ያደረጉ አሉ።

የስንፍና አቋማችን ላለመለወጥ ትልቁ በራሳችን የገመድነው ጠላታችን ነው። ለሰው የከበረው ሐብቱ ትጋቱ ነው። ለሁሉ ነገር ምክንያት (Excuse) መደርደር እና ያለንበት የስንፍና መንገድ ትክክል እንደሆነ መቀበል ስንፍናን ቤታችን ውስጥ ማደላደል ነው። ስንፍና የሰው ትልቁ ጠላት ነው። የዚህ ጽሑፍ አላማ ትጉ የሆንበትን ነገር እያሳደግን፥ ስንፍናችን እየጣልን ለመሔድ እንድንችል ይረዳን ዘንድ ነው። ስንፍና ትልቁ የሰው ጠላት፥ የድህነት አባት ሲሆን ረዳቶቹ ምክንያት መደርደርና ስንፍናን እንደ አቋም መያዝ ናቸው።

“የስንፍና ሐሳብ ኃጢአት ነው.....”
— ምሳሌ 24፥9

ዘሪሁን ግርማ


Join And Share




@oracleKB
351 views✞ቃለ-አብ✞, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 10:17:25

300 views✞ቃለ-አብ✞, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 08:42:07
እዩት ፍቅርን እዩት


“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5


Nani


@oracleKB
583 views✞ቃለ-አብ✞, edited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 23:31:26
@oracleKB
292 views✞ቃለ-አብ✞, edited  20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 11:02:53
@oracleKB
291 views✞ቃለ-አብ✞, edited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 10:33:39 ፋ-ታ አልሰጥ ብሎኝ፤ የበደሌ ብዛት
ሲ-ኦል አፉን ከፍቶ፤ ነፍሴን ሲጠብቃት
ካ-ጠገቤ እሚሆን፤ አንድ እንኳ ሲጠፋ
ች-ጋር ላይ ወድቄ፤ አንገቴን ስደፋ
ን-ቆ ሁሉም ሲያልፈኝ፤ ሆኜ ያለ ተስፋ

ክ-ርስቶስ ግን አየኝ፤ ቀረበ ወደኔ
ር-ህራሄው ፍቅሩን፤ ሊያሳየኝ በአይኔ
ስ-ጋ ለብሶ መጣ፤ ከሰማይ ወረደ
ቶ-ሎ ብሎ እኔን ፤ለራሱ ወሰደ
ስ-ለ እኔ ሃጥያት፤ ሊቀጣ ወደደ

ታ-ሪኬን ሊቀይር፤ ሊፅፍ እንደገና
ር-ቄ የነበርኩትን፤ ሊያቀርብ ወደደና
ዶ-ሴው ተከደነ፤ የተከሰስኩበት
ል-ያዩ ከሳሾቼ ፤ስትሻገር ነፍሴ፤ ከሞት ወደ ህይወት
ና ልጄ እያለ ፤በአባት ፍቅሩ ጠራኝ
ል-ቤን በፍቅሩ ፤ነፍሴንም በደሙ፤ በውድ ዋጋ ገዛኝ


yku

@oracleKB
2.8K views✞ቃለ-አብ✞, 07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:23:58 የተወደዳቹ የጌታ ቤተሰቦች ይህን Channel ለሌሎች Share በማድረግ ወንጌልን አብረን እንስራ የተለያዩ ወጎች፣ግጥሞች፣አስተማሪ ትምህርቶች ሁሉም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን የምናይበት የተለያዩ ፅሁፎች የምንለቅ ይሆናል።

ወንጌል ለሁሉም!!!

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4


@oracleKB
287 views✞ቃለ-አብ✞, 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ