Get Mystery Box with random crypto!

ƝƲƦƲ ቴክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nurutech — ƝƲƦƲ ቴክ Ɲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ nurutech — ƝƲƦƲ ቴክ
የሰርጥ አድራሻ: @nurutech
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.02K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን
🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት !
🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ቦት ያሳውቁን!
https://t.me/nurudish_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-02 07:11:47
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፊጥር በዐል በጤና አደረሳችሁ ፤ አደረሰን!

ኢድ ሙባረክ!
2.9K viewsNurhusen Yesuf, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 21:38:12 ውድ የኑሩ ሳይቴክ ቤተሰቦች ተመልሰናል
በ DOC File እና በ DOCX File መካከል ያለው ልዩነት
**********
በኮምፒውተር የተለያዩ የጽሁፍ ስራዎችን ለመስራት ስናስብ በብዛት የምንጠቀምባቸው መጻፊያዎች DOC እና DOCX የሚባሉት ናቸው፡፡ ሁለቱም የማይክሮሶፍ ወርድ ዶክመንት ክፍሎች ሲሆኑ የተለያዩ ምስሎችን፣ የተለያዩ ቴብሎችን እና ቻርቶችን ለመጻፍ ያገለግላሉ፡፡ ለመሆኑ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ማይክሮሶፍት ዎርድ DOC የሚባለውን የመጻፊያ ስርዓት ዋና መገልገያ (default) አድጎት ቆይቷል፡፡ እስከ 2006 ድረስ DOC በምዝገባና በፈቃድ ጥቅም ላይ የሚውል ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም የተለያዩ መሻሻሎች ተደርገውበታል፡፡ አሁን ላይ እንደ LibreOffice Writer፣ OpenOffice Writer፣ KingSoft Writer የመሰሉ በነጻ የቀረቡና በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ መጠቀሚያዎችን አካትቶ ቀርቧል፡፡ እነዚህ ፐሮግራሞች የ DOC ፋይሎችን ለመክፈትና ለማስተካከል ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
በሌላ በኩል DOCX የተባለው የመጻፊያ ፕሮግራም የ DOC ተከታይ ሆኖ በማይክሮሶፍት ወርድ የቀረበ ነው፡፡ በ2007 ተሻሽሎ በቀረበው የወርድ ወይም የመጻፊያ ፕሮግራም ቀዳሚ መጠቀሚያ ሆኖ የቀረበው DOCX ነው፡፡ ይህም የሆነው ማይክሮሶፍት ወርድ እንደ ኦፕን ኦፊስና ODF ካሉ ነጻና ክፍት መጠቀሚያዎቸ በገጠመው ፉክክር ምክንያት ነው፡፡
በ DOCX ውስጥ ያለው የኮድ መስሪያ በ XML የተሰራ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ያለችው X ይህንን የምታመለክት ናት፡፡ ይህ ኮዲንግ ሲስተም አዳዲስ መገለጫዎችን ጥቅም ላይ ያዋለ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ PPTX እና XLSX ያሉ ፎርማቶች ላይ ለውጥ አድርጓል፡፡ አሁን ላይ በሁለቱ መካከል ይህ ነው የሚባል ትልቅ ልዩነት ባይኖርም በጣም ትናንሽ ፋይሎችን ለመፍጠር DOCX የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ይነገራል፡፡


የቴሌግራም ቻናል https://t.me/nurutech
6.3K viewsNurhusen Yesuf, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 13:11:59 Telegram Update ከሆነ ቦኋላ ያመጣቸው አዳዲስ ገራሚ ፊውቸሮች

፩ Protected Content in Groups and Channels

ብዙዎችን ያስደሰተ በተለይ የTelegram ቻነል ና ግሩፕ ላላቸው ሰወች እንደምናውቀው Copypast እና Forward ለብዙ የቻነል Owneሮች ራስምታት ና ሲያስመርር የቆየ ነገር ነው አንዱ ላብን ጠብ አድርጎ ግዜውን ሰውቶ ቻነሉ ላይ የፃፈውን ማንኛውም Program ሌላኛው ዘና ፈታ ብሎ ወደ ራሱ ቻነል Copy past በማድረግ እራሱ እንዳዘጋጀው አስመስሎ ይለቃል ይሄ በራሱ የሚሰራውን ሰዉ Moral ይገላል አንዳንዶቹ ደግሞ Credit እያሉ Copy ና Forward ያደርጋሉ ከዚህ ቦኋላ ከማንኛውም ቻነል Copypast ና Forward ማድረግ አይቻልም.

ቁርጥሽ እወቂ አዳሜ እስካሁን ያዛጋቹን ይበቃል

፪ Auto Deleted Message

ይሄ ፊውቸር ደግሞ ለ አንድ ሰው መልክት ልከን ከ 24 ሰአት ከ 1ድ ሳምነንት ና ከ 1ድ ወር ግዜ ቦኋላ ከላክልነት ሰውዬ ጋር Automatically Deleted እንዲሆን የሚያስችል ነው.

፫ New emoji

ለምሳሌ የአንድ ሰዉ Bio ላይ ይሄን emoji ብንመለከት በቀላሉ ስለ ሰውየው feeling Guess እናደርጋለን እንደሚታወቀው emojiወች የሰወችን Emotion ወይም ስሜት ከቃላት በማይተናነስ መልኩ ይገልፃሉ Telegramምም ይህን በመገንዘብ ሰወች በይበልጥ የተሰማቸውን ስሜት እንዲገልፁ አዳዲስ emoji አምጥቷል
በጥቂቱ



፬ Delete My Message

ይህኛው ፊውቸር ደግሞ ከ አንድ ሰዉ ጋር ካወራነው የChat History ላይ የኛን Message ብቻ ከላክልነት ሰውዬ ጋር ነጥሎ ያጠፋል

የClear History እህት በሉዋት

፭ Change Color / Theme

ይሄ ደግሞ የChat Background Color ና Themeን ለመቀየር ና ለማስዋብ የሚያስችለን Setting ሲሆን በፊትም ነበር ሲሆን አሁን ግን ተሻሽሎ በአዳዲስና ማራኪ Themeሞችና Background colors መቷል ሞክሩት

፭ Attach
ከስሙ እንደምንረዳው Attach ማያያዝ ሲሆን ማንኛውንም ፃሁፍ ከPhoto ጋር አንድ ላይ ለማያያዝ ያስችላል ትንሽ ቀለል ብሎ መጣ እንጂ ድሮም ያለ ፊውቸር ነው

እንደ ከአለም ጋለሪ የድንቃድንቅ
የግጥም Channel ላላቹ Owneሮች ምርጥዬ ናት

፮ Automatic Terminate

ይሄ ፊውቸር ደግሞ ከኛ ስልክ ውጪ በሌላ ሰዉ ወይም በጓደኛችን ስልክ የTelegram አካውንታችንን Login ካደረግንና ከተጠቀምን ቦኋላ Automatically ከጓደኛችን ስልክ አካውንታችንን በራሱ Logout ያደርጋል እኛ Logout ማድረግ አይጠበቅብንም.

ይሄ ሚሆነው ግን በገባንበት ሰው አካውንታችንን Automatic Terminate ከሞላን ነዉ

፯ Jump to Next Channel

እንደምናውቀው አብዛኞቻችን Telegram ላይ የተለያዩ ቻነሎች ውስጥ join ብለናል ይሄ ፊውቸር
ምንድነው የሚያደርገው አንድ ቻነል ላይ ተገብታቹ የሆነ ነገር እየተመለከታችሁ ወይም እያነበባቹ ወደ ሌላኛው ቻነል
ለመሄድ ከዛ ቻነል መውጣት አይጠበቅብንም የስልካችንን Screen ወደ ላይ Scroll ስናደርገው ወደ ሌላኛው ቻነል ይወስደናል or ያልፋል


፰ Live Stream

live stream is a one-way
video broadcast System.

Live Stream ማለት ባጭሩ ቀጥታ ስርጭት ማለት ነው

ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ እኛ ቤታችን ሆነን በቀጥታ በTvያችን ቴዲን እንመለከታለን እሱ ግን እኛን አያየንም ቴዲ መመልከት የሚችለው ኮንሰርቱን ላይ የታደሙትን ነው ስለዚህ Live Stream የተባለው Technology አንድን ሰው የትም ቦታ ሆነን በTv በTablets በስልክ ቀጥታ መከታተል ያስችላል ኮንሰርቱን ታደምን ማለት ነዉ Telegram ይህን ፊውቸር ነው ያመጣው

፱ Flexible Forwarding

ይሄ ፊውቸር ጥቅሙ ለምሳሌ አንድ ሰዉ message ቢልክልን ያን መልክት ለሌላ ሰዉ ሶስተኛ ወገን ስልንክ መጀመሪያ የላከውን ሰው Name Hide ያደርጋል ይሄ ደግሞ መጀመሪያ ላይ ለላከው ሰውዬ privacy ደህንነት የተጠበቀ ያደርገዋል.

፲ Unpin All Message

ቻነላቸን ላይ Pin ያደረገውን Post በሙሉ በአንዴ Unpin ለማድረግ የሚያስችል ፊውቸር ነው እያንዳንዱን Post Unpin ከማድረግ ይታደገናል

Telegraph ሌሎችም ብቹ ገራሚ ፊውቸር አምጥቷል Telegram በዚህ ከቀጠለ Social mediaውን መቆጣጠሩ አይቀርም Facebook IG Twitter WTs'App የመሳሰሉት ላይ የሌለ ፊውቸር ነው እያሳየን ያለው Developeሮቹ ማሻሻያውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል
7.9K viewsNurhusen Yesuf, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 20:11:55 #የፌስቡክ_ፕሮፋይላችንን_እንዴት_መቆለፍ_እንችላለን?

የፌስቡክ ፐሮፋይላችሁን እንድትቆልፉ እመክራለሁ፡፡

ፌስቡክ ላይ ፖስት የምታደርጉት ፎቶ፤ቪዲዮ፤ ወይም መልዕክት ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያየው ለማድረግ ፐሮፋይላችንን መቆለፍ ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም ፕሮፋይላችንንም ከጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያይ ፕሮፋይላችንን መቆለፍ አለበት፡፡

ለአንድሮይድ ስልኮች ላይ ብቻ ነው ይሄ አገልግሎት ያለው፡፡iOS ስልኮች ላይ አይገኝም፡፡

እንዴት ነው የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ሎክ /መቆለፍ የምንችለው?

1ኛ፦ፌስቡክ አፕሊኬሽን እንከፍትና ወደ ፕሮፋይላችንን እንገባለን

2ኛ፦ በቀኝ በኩል በመደዳ የሚታዩትን ሶስት ነጥቦችን ክሊክ ማድረግ፤

3ኛ፦ “Lock Profile” የሚል አማራጭ ሲመጣ እሱን ክሊክ ማድረግ፤

4ኛ፦ ቀጥሎ “Lock Your Profile“ የሚል ምርጫ ከስር ይመጣል፡እሱን ክሊክ ማድረግ፤

5ኛ፦ በመጨረሻ‘You Locked Your Profile' የሚል ይመጣል፤እዛው ላይ OK ብለን እንጨርሳለን፡፡

አሁን ፌስቡክ ፕሮፋይላችን ተቆልፋል፡፡

ፕሮፋይላችንን ጨምሮ ፖስት የምናደርጋቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡
9.1K viewsNurhusen Yesuf, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 10:52:56 አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡


ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡
7.2K viewsNurhusen Yesuf, 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 19:56:11
ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።

@nurutech @nurutech
5.3K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 11:27:02 ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች

መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል ።

መልቲ ሜትር:- ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመለካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል ።

ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል ።

ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጓዳ ይጠቅማል ።

ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል ።

ካዉያ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል ።

ሊድ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት ነዉ ።

ጃምፐር ዋየር ፦ ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን /የተላቀቁ ክፍሎችን/ ለማያያዝ የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ ።

ትዊዘር(ፒከር) ፦ አይሲ ወይንም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር ስናሞቅ እንደ መቆንጠጫ የምንይዝበት ነዉ ።

ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ፦ ከባትሪ የምናገኘዉን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ የሚሰጥ ክፍል ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ ስልካችን ኦፕን ይሁን ሾርት ወይም ስልኮች የሶፍትዌር ችግር እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉ ሊያሳየን የሚችል በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነዉ ። በተጨማሪም ስፒከርን ወይም ሪንገርን ለመፈተሽ ይጠቅመናል።

ኮምፒውተር ፦ ለሶፍትዌር ጥገና ፣ ለሃርድዌር ላይብረሪ እና ሙዚቃ ለመጫን ይጠቅመናል ።

ፍላሽ ቦክስ ፦ በሶፍትዌር ጥገና ሰአት በሞባይልና በኮምፒዉተር መሃል የሚገኝና ሁለቱን አካሎች የሚያግባባቸዉ መሳሪያ ነዉ ።

ቦርድ ፕሌት :- የስልካችንን ቦርድ በምንበይድበት ጊዜ ወይም አይሲ በምንነቅልበት ጊዜ ቦርዱ እንዳይነቃነቅ የሚያደርግ መሳሪያ ነዉ ።

ሶፍትዌር ኬብል ፦ በሶፍትዌር ጥገና ስአት ስልካችንን ከፍላሸር ቦክስ ጋር የሚያግባባ ነዉ።

ቫይብሬተር ፦ ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ወይም ስታክ ያደረገ ስልክ እንዲሰራ ቫይብሬተር ዉስጥ ተዘፍዝፎ ፣ የተወሰነ ደቂቃ ይቆያል ።

@nurutech @nurutech
4.4K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 14:47:59 የተለያዩ አይሲዎችን ለመለየት የሚጠቅም ዘዴ

1. ሲፒዩ :- ወርቃማ እግር አለዉ ።
2. ቻርጅ አይሲ:- R22 የሚል አነስተኛ ሬዚስተር አጠገቡ ይገኛል ።
3. ዩአይ አይሲ :- 20 እግር አለዉ እግሮቹም ወጣ ወጣ ያሉ ናቸዉ ።
4. ቪሲኦ :- አብዛኛዉን ጊዚ በቆርቆሮ የታሸገ ነዉ አልያም በወርቃማ መስመር ብቻዉን የታጠረ ነዉ ። ቪሲኦ የሚገኘዉ Rx ክፍል ዉስጥ ነዉ ።
5. ክሪስታል ኦሲሌተር :- ጠፍጣፋ ሬክታንግል መልክ ያለዉ ነዉ ።
6. ኔትወርክ አይሲ :- ከክሪስታል ኦሲሌተር አጠገብ ይገኛል ። ኔትወርክ አይሲ Rx ክፍል ዉስጥ ይገኛል ።
7. ፓወር አምፕሊፋየር :- አብዛኛዉን ጊዜ የመጀመሪያዉ (ከላይ የሚገኝ) አይሲ ነዉ ።
8. ኤፍ ኤም አይሲ(ሬዲዩ አይሲ):- አጠገቡ ባለቀለም ኢንዴክተር ይኖራል : ቀለሙም ደማቅ ወይም ደብዛዛ ሰማያዊ ነዉ ።
9. ብሉቱዝ አይሲ :- ሬክታንግል ቅርፅ ያለዉ ነጭ : አነስተኛና ጠፈር ያለ አካል ካጠገቡ ይገኛል ።
10. ፓወር አይሲ:- አጠገቡ ትንሽ እና ቀጭን አካል (አርቲስ) ሁሌም ይኖራል ።
11. ባካፕ ባትሪ :- የሰአት አይሲ የሚመስል ነዉ ።
12. ላይት አይሲ :- አጠገቡ ጥልቅ ሽቦ (ቡስተር ኮይል) ይኖራል ።
13. ሲም አይሲ :- ትንሽ : አንጸባራቂ : ብራማ ከለር ያለዉና ከሲም ማስቀመጫ አጠገብ ወይም ማስቀመጫ በስተጀርባ ይገኛል ።
14. ኪይ ፓድ አይሲ :- ከኪይ ፓድ እና ከኮኔክተር አጠገብ ወይም ከሲፒዩ አጠገብ ይገኛል ።
15. ካፓሲተር :- ቀለል ያለ ቡኒ ቀለም ያላቸዉ ናቸዉ ።
16. ኢንደክተር :- ጥቋቁር እና አብዛኛዉን ጌዜ ከካፓሲተሮች በመጠናቸዉ ተለቅ ብለዉ ይገኛሉ።
17. ሬዚስተር :- ጥቋቁር እና ትናንሽ ክፍሎች ናቸዉ።
4.3K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 12:41:32 የፌስቡክ ኩባንያ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተከሰሰ


በኦሂዮ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ የቀረበበት ፌስቡክ በህጻናት ላይ ባደረሰው ጉዳት 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ክስ ቀርቦበታል

የፌስቡክ ኩባንያ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍለ ተከሰሰ፡፡

የኩባንያውን ስም ወደ ሜታ የቀየረው ፌስቡክ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል በኦሃዮ ፍርድ ቤት መከሰሱን የሩሲያው አርቲ ዘግቧል፡፡

ኩባንያው ክስ የቀረበበት በፈረንጆቹ 2021 ዓመት ውስጥ ካለፈው ሚያዝያ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ውስጥ በፌስቡክ ህጻናትን ላልተገባ ጉዳት የሚያጋልጡ ጎጂ ይዘቶች በፌስቡክ በመተላለፋቸው መሆኑን የኦሂዮ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዴቭ ዮስት ተናግረዋል፡፡

እንደ ክሱ ከሆነ ፌስቡክ በህጻናት ላይ አሉታዊ መልዕክቶች እንዳይዘዋወሩ መከላከል የሚያስችል አሰራር ቢተገብርም ትርፉን ለመሰብሰብ ሲል ተግባራዊ አለማድረጉ ተገልጿል፡፡

እነደ ዘገባው ከሆነ ፌስቡክ ላደረሰው ጉዳት 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል እና የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ተጠይቋል፡፡

የሜታ ኩባንያ ቃል አቀባይ ጆ ኦስቦርን በበኩላቸው ክሱ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ ራሳችንን እንከላከላለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ፌስቡክ ላይ ክሱ የቀረበው የቀድሞ የኩባንያው ሰራተኛ አማካኝነት በወጣ ሪፖርት መነሻነት ሲሆን ፌስቡክ የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ እና ሌሎች የተለያዩ ማህበረሰብ አካላትን ሆን ተብለው የሚጎዱ መልዕክቶች ሲዘዋወሩ ኩባንያው ለትርፍ ሲል እርምጃ አልወሰደም የሚል ክሶች ቀርበውበታል፡፡

የሜታ ኩባንያ መስራች እና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በበኩላቸው በድርጅታቸው ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድረገው ትርፍን እንደማያስቀድም ተናግረዋል፡፡

@nurudish
4.0K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, edited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-13 19:29:00
Samsung S9+
128Gb
Used
Price negotiable

@nurudish_bot
4.2K viewsƝƲƦƲ ሳይቴክ, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ