Get Mystery Box with random crypto!

Educate Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia E
ርዕሶች ከሰርጥ:
Result
የቴሌግራም ቻናል አርማ educate_ethiopia — Educate Ethiopia
ርዕሶች ከሰርጥ:
Result
የሰርጥ አድራሻ: @educate_ethiopia
ምድቦች: እውነታው
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.48K
የሰርጥ መግለጫ

A channel dedicated to brighten Ethiopia through education .
We share study tips, tricks motivations and resources that will help your academic carrier.
For any questions @EducateEthiopiaBot
For any resources @EducateEthResources

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-10-10 09:19:04
#Result

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።
    
በዌብ ሳይት፡- eaes.et
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

@tikvahethiopia
10.2K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 18:51:22
ሐሳቦትን ያካፍሉን

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት ተመልሶ ለሚቀጥለውም አመት ተመሳሳይ ውጤት እንዳይደገም መፍትሄው ምን ሊሆን ይገባል ትላላቹ?

ሐሳብ አስተያየትዎን ከታች ይካፍሉን።

@educate_Ethiopia
7.4K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 18:20:21
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከነገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በቴሌግራም : https://t.me/eaesbot
በዌብ ሳይት : https://eaes.edu.et/
በአጭር የጽሑፍ መልዕክት : 6284

ትምህርት ሚኒስቴር
6.5K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 14:05:49
#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈተኑ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
6.4K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-26 11:56:33
ትምህርት ለሁሉም ተማሪዎች በነፃ !

አዎ በነፃ
!!!!

እንኳን ደስ አለን!! በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት(curriculum) e- Learning በኢትዮጵያ ተጀመረ! ከ4 - 12 ክፍል ያሉትን ትምህርቶች Mathematics, physics, Biology,Chemistry, General science እና ሌሎችም ሙሉ የመጽሐፉን ትምህርት በአዲስ አቀራረብ በማንኛውም ጊዜ ከየትኛውም ቦታ ሆነው YouTube ላይ መማር ይችላሉ።

YouTube : https://youtube.com/@globedockacademy

Telegram : @globedockacademy

Website : https://globedock.et/
TikTok- https://www.tiktok.com/@globedockacademy?_t=8fm3ycb334A&_r=1

GlobeDock Academy
8.4K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 17:04:07 Educate Ethiopia pinned «ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) እየተዘጋጃችሁ ነዉ?»
14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 14:00:15
#ማስታወቂያ አቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
1.5K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 07:09:42
#ማስታወቂያ

በ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁና በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ ቅሬታ

placement.ethernet.edu.et

ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ቅሬታችሁን እስከ የካቲት 07/2015 ዓ.ም 06፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻም ሆን ቅሬታ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

MOE
503 views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 11:50:28
#የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ማሳወቂያ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል።

MOE
727 views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 22:26:12
#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባ ተለቀቀ!

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመማር ያመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የ Remedial ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ ነገ ይፋ የሚደረግ መሆኑን እናሳውቃለን።

Website: https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot
877 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ