Get Mystery Box with random crypto!

Nolawi ኖላዊ ኄር

የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawiiher — Nolawi ኖላዊ ኄር N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawiiher — Nolawi ኖላዊ ኄር
የሰርጥ አድራሻ: @nolawiiher
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነወ።
#ለሃሳብ ለአስተያየት 👉 @Nolawiher1
Facebook :- https://www.facebook.com/estifanos.dejene.94
✟ወአንሰ በምሕረትከ ተወከልኩ ✞
✟ይትፌሥሐኒ ልብየ በአድኅኖትከ ✞

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-04 21:41:25 “ሌሎችን መጥቀም ትልቅነት ነው ፣ ካልሆነልን ግን አለመጉዳትም ጨዋነት ነው።”

@Nolawiiher
@Nolawiiher
1.8K views ŵūšţę, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 12:42:03
2.3K views ŵūšţę, 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 10:01:27 አንብቡ ! አንብቡ ! አንብቡ ! አረ እባካችሁ አንብቡ !!
2.8K views ŵūšţę, 07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:57:43 በጸሎት ኃይል ሊጠብቅ ይገባል ። እግዚአብሔር ያስበን !


እውቀት የትጉሐን ውጤት ፀጋ የልበ ንጹሐን ውጤት ናትና ለብዙ ቀናት  የመውደድ (ፍቅር) ዕድሜ ስንት ነው ? ብዬ ብዙዎችን ስጠይቅ ነበር ። የብዙዎች መልስ ፍቅር ዕድሜ የለውም የሚል ነው ። ልክ ነው ከምጽዓተ ክርስቶስ በኋላ በሰማይ ፍቅርና እምነት ይቀጥላሉ ። ይህም ፍቅርና እምነት ዘላለማዊ መሆናቸውን ይገልጣል ። ፍቅር ነጌን እንዲያገኝ ግን ዕድሜው ምን ይሆን የሚል ጥያቄ ነው የኔ ጥያቄ ። ፍቅር ዕድሜው ዛሬና ትናት ከሆነ ከፋትም ነውርም ዕድሜው የዛሬ ቀንና የሌቱ መንጋት ሊሆን ነው ። ይህ ማለት ቀዩም ጥቁሩም ኢትዮጵያዊ ነው ። ጥቁሩም ቀዩም ክርስቲያን ነው ልንል ነው ። ይህ ግን አያስኬድም ። ይልቅስ የፍቅር ዕድሜ ስንት ነው ስንል የምናገኘው ተመን ''ክብር" ነው ። አዎ የፍቅር ዕድሜው ክብር ነው ። እንዴት ? የሚል አይጠፋም ። እስቲ ምሳሌ እንጥቀስ ፦ ሁለት ጥዶችን በዘመኑ ቋንቋ (ፍቅረኛሞችን) አስቡ ። ወንዱ ልጅ ውዴ አፍቅርሻለሁ ብሎ በጥፊ ቢላት ፣ ፍቅሩን የሚገልጸው በጥፊ መቶ ቢሆን ያች ሴት አንድ ቀን ከእርሱ ጋር አታሳልፍም ። ሂድና ፍቀረኛኽን ፈልግ ነው የምትለው ። ከጥፊ ይልቅ ጉንጯን ስሞ አፍቅርሻለሁ ቢላት ግን ፍቅራቸው ዕድሜ ያገኛል ። ያለማክበር የፍቅርን ዕድሜ ይቀጫል ። እንኳን የሰው ፍቅር ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ፍቅር ዕድሜው እርሱን የምናከብርበት ልክ ነው ። (ዮሐ 14:15-17 ) ። ትዕዛዙን የማናከብረውን አምላክ እንዴት ልንወደው እንችላለን ? በማክበር ክብር ይገኛል ። ማክበር የትሑት ልብ መሠረት ነውና ትሕትና የክብር መነሻ ናት።

"የሸክላ ምርጥ የለም የሰሪው ምርጥ እንጂ ፤
በክፋትም ዘር ድግስ ውድማው አይበጅ ፤
የማክበርም ጌጥ በመውደድ መጠን ነው ፤
የከፍታም ሕይወት የትሑት ልብ ነው"

እግዚአብሔር ያከበሩትን ያከብራል ፤ የናቁትን ያዋርዳል  (1ኛ ሳሙ 2:30 ) ። ዛሬ መውደድ ከአክብሮት ላልቷል ።  አክብረን የምናቀለው እንጂ ወደን የምናከብረው እያጣን ነው ። እወነተኛ መውደድ ግን ከአክብሮት ጋር ነው ።  ሀገራችን ክብር የራቃት የመውደድ ዜማ የሚያዘቡባት እንጂ የክብርን መሥመር የሚያበጁ ልጆች ስላጣች ነው ። በእወድሻለሁ ቃል ብቻ የሚንገዳገደው እጮኝነት በአክብሮት ምሶሶ መጽናት አለበት ። እግዚአብሔር በፍቅር አደባባይ የክብርን ብርሃን ይትከልልን ! በርግጥም መውደድ ከአክብሮት ላልቷል ክብሩ ይጋርደን ! ።


ጸሎት

ታናሽነትን የማትንቅ ፣ ትልቅነተህ ትንሽነትን የምትቀበል ሰማይ መቀመጫህ ምድር የእግርህ ማረፊያ የሆነ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ተመስገን ። የሁሉ አባት አሳደሪ አንተ ነህ ክበር ። በዘመናት ውስጥ አንተ ለሁሉ መፍትሔ ነህ ተመስገን ። ዛሬ ኃጢአት በወለደው የጥላቻ ሰንሰለት መራራቅን በጥሰህ በፍቅርህ ሰንሰለት እንድታጣምረን እንለምንሃለን ። የአንተ ሰንሰለት ያያይዛል ። አንድ በሆነው መንግሥትህ አንድ አድርገን ። የላላብንን ነጻነት ፣ ሃይማኖት ፣ በጎነት ፣ አክብሮት እንተ እንደገና አጥብቀው ። አንተን እቢ ያለው ልባችን በእሺ ተባርኮ ፣ ሀገራችን በነጻነት እንድታጌጥ ፣ ሃይማኖታችን እንተን በመፍራት እንድታብብ ፣ ፍቅራችን በበጎነት እንድታጌጥ ፣ መውደዳችን በክብር ከፍ እንዲል እንለምንሃለን ። በማናፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን !!

@Nolawiiher
@Nolawiiher

ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ
የመጀመሪያ ጽሑፍ መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም
2ኛ ጽሑፍ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም
2.9K views ŵūšţę, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:57:43 ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኲሉ ጉባዔ ዘሐዋርያት፡፡
ሐዋርያት ባነጽዋት ከምኲራበ አረሚ ከምኲራበ አይሁድ በላይ በምትሆን ክብርት ንጽሕት ጽንዕት ልዩ በምትሆን ባንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን ሐተታ አሐቲ አለ በወርቅ በብር በጭቃ በጨፈቃ ቢሠራ በግብጽ በእስክንድርያ በጻድቃን በሰማዕታት በእመቤታችን ስም ቢሠራ አንድ ነውና በወርቅ በብር የተሠራ ቤተክርስቲያን ሥጋውን ደሙን ይለውጣል በጭቃ በጨፈቃ የተሠራ ቤተክርስቲያን ሥጋውን ደሙን አይለውጥም አያከብርም ብለዋልና አሐቲ አለ አንድም ሐዋርያት ያስተማሯት ያሳመኗት ያጠመቋት ከምዕመናነ አሕዛብ በላይ የምትሆን ክብርት ንጽሕት በምትሆን ባንዲት ምዕመን እናምናለን፡፡ ሐተታ አሐቲ አላቸው ምዕመናንን አንድ እምነት ያምናሉ አንድ ጥምቀትይጠመቃሉ አንድ ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉና አንድም ምዕመንን በሚያስተምሩ ባንድ መምህራን እናምናለን፡፡ ሐተታ መምህራንን አሐቲ አላቸው አንድ እምነት ያሳምናሉ አንድ ትምህርት ያስተምራሉ፡፡ አንድ ሥጋውን ደሙን ያቀብላሉና፡፡ አንድም በቤተክርስቲያን ምዕመናንን በሚያስተምሩ ባንድ በመምህራን እናምናለን፡፡ ሐተታ ሲያስተምሩ ሲያሳምኑ ሲያጠምቁ በቤተክርስቲያን ነውና ቅድስትን እንደ ሃይማኖተ አበው አትት፡፡
ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት፡፡
ኃጢአት በሚሠረይባት ባንዲት ጥምቀት እናምናል፡፡ ሐተታ በአብ ስም በወልድ ስም በመንፈስ ቅዱስ ስም ቢጠመቁ አንድ ነውና በዐርባ ቀን በሰማንያ ቀን በዐርባ ዘመን በሰማንያ ዘመን ቢጠመቁ አንድ ነውና፡፡ እንድም በሊቀ ጳጳስ በጳጳስ በኤጲስ ቆጶስ በቄስ እጅ ቢጠመቁ አንድ ነውና አንድም በዐቢይ ባሕር በማዕከላዊ ባሕር በንዑስ ባሕር ቢጠመቁ አንድ ነውና ፡፡
ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን፡፡
ከፈረሱ ከበሰበሱ በኋላ አካል አግኝተው ታድሰው ሙታን እንዲነሡም እናምናለን አንድም አንዘ ንሴፎ ይላል ሙታን እንዲነሡ አምነን ባንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡ ሐተታ ማጥመቅ ትንሣኤ ሙታን ካሳመኑ በኋላ ነውና ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም፡፡
ሐይው ከመ መላእክት እንዳለ እናምናለን፡፡


የሃይማኖት መሠረት ብላ ዓለም አቀፋዊት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያስተማረችን ትምህርት ይህ ነው ። ዛሬ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚለው በዚህ መሠረት ላይ የታነጸ ወይስ እንደ ባህታዊ ሰላሳ መስቀል ያሰረ ። በዚህ መሠረት የሚያምን ወይስ መሪ በሌለው ተመሪ የሚነዳ ሃይማኖተኛ ስንል የሚታወቅና እያየን ያለነው ጉዳይ ነው ። በኢትዮጵያ ውስጥ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይ 43.8% ነው ። 31.3 % ሙስሊም ነው ።  ፕሮቴስታንት 22.8 % ነው ። ካቶሊክ 0.7% ነው ። በድምር 98.6 % ሃይማኖተኛ በሆነበት ሀገር ሰው  ዛሬ እየተጋደለ ፣ በዘር በሃይማኖት እየተከፋፈለ ፣ የሰውን ደም እደ ጅረት እያፈሰሰ ያለው ሃይማኖተኛና  መስቀል በአንገቱ ላይ ያሰረ ኦርቶዶክስ ፤ ጌታን ተቀበል እያለ በየመንገዱ የሚሰብክ ፕሮቴስታንት ፤ Allah ዋዓክበር እያለ የሚሰግድ ሙስሊም ሰው ሲሆን ልብ ይነካል ። በርግጥም የሃይማኖት ስም መመልስ አለበት ።   ክርክትና  ሃይማኖተኝነት ማለት ሳይሆን እግዚአብሔርን በማወቅ የምንጀምረው ሕይወት ነው ።  በዚህ የሃይማኖት መሠረት ግን እግዚአብሔር በመጠናችን ይታወቃል ። ሃይማኖት ወኔ አይደለችም በደረት አትለካም ። ሃይማኖት ዘመናቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ክቡራን ሰዎች ስብስብ እንጂ ነጂ በሌለው ነጂ የሚነዱ የባለስሜቶች ተቋም አይደለችም ። ሃይማኖት በእምነታቸው ዓለምን የሚኮንኑ ሰዎች መዋቅር እንጂ የባለ ወኔዎች  መሪ አይደለችም ። ሃይማኖት ጉብዝናቸውን ፈጣሪን በማሰብ ያስጌጡ ሰዎች መሰብሰቢያ እንጂ ለስድበና ለመንቀፍ የሚጀግኑ ሰዎች መግቢያና መውጪያ አይደለችም ። ሃይማኖት እንደራሴ ከሚሉ ሰዎች የዳነች እንደ እግዚአብሔር ብለው ነጌን በሚያስቡ ልበ ትጉሐን የበራች  ናት ። ሃይማኖት እንዴት እነርሱ ሳይሆን እንዴት እኔ ብለው ዓለምን እምቢ ባሉ ነዑዳን ሰዎች የተከበበች እንጂ ስሜት ሸቀጥ ሆኖባቸው ሀገርን በሚያምሱና ቤተክርስቲያንን በሚያሰድቡ ሰዎች የማትለካ አይደለችም ። ይልቅስ ሃይማኖት እግዚአብሔርን ከመፍራት ላልቷልና ይህ ሰንሰለት እንዲጠብቅ እግዚአብሔርን በማወቅ የሚጀመር የክርስትና ሕይወት የሃይማኖት ወርቅነት ይጋብዛል ። እግዚአብሔርን የማያውቁ ሃይማኖተኞች ናቸው ዛሬ ቤተክርስቲያንን እያመሱ ያሉት ። ስለዚህ ክርስትና ሃይማኖተኝነት እንዳልሆነ ብንረዳ መልካም ነው ። እግዚአብሔርን ማወቅ ብቻ ወደ ትክክለኛ ሃይማኖት ይመራል ። ሃይማኖትኝነት ጥልቅ ትርጉሙ ዛሬ ተጎሳቁሏል ። እባካችሁ ይህ ሰንሰለት ከመላላት አልፎ እንዳይበጠስ ጸልዩ  ። በርግጥም የሃይማኖት ስም መመለስ አለበት ። ሃይማኖት እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለበት ሃይማኖት መሆኑ ይቀራል ። እግዚአብሔር ያስበን !



ፍቅር የጥርስ ወረርሽኝ የሆነባት ሀገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት ። መሪዎች የሟቾችን ሰነድ ደፍነው ነጻ ባልወጣች ሀገር በንግግር የደልሉናል ። አገልጋዮቻችን የፍቅርን መድረክ አስጎብኝተው ድንበሩ ተነካ ይሉናል ። ትምህርት ቤቶቻችን ትምህርት መሰልጠን ነው እያሉ በፈረንጆጅ ወረቀት ከሀገር ፍቅር ያጉድሉናል ። የሃይማኖት ዘብ ቋሚ ነኝ የሚሉ ጥቅማቸው ሲነካ ቤተክርስቲያን ተደፈረች ብለው ስንዴ ለሌለው እንክርዳድ ያሯሩጡናል ። ማህበረሰባችን ለሞት ቀን ዕድር አቋቁመው ለመኖሪያ ፍቅር እግዜር ያውቃል ይሉናል ። ቀበሌያችን ስብሰባ ብሎ የጉቦ እጩዎችን ያስመርጠናል ። ቤተሰቦቻችን ሺህ ብር ከፍለው እያስተማሩ ቤተክርስቲያን ይከለክሉናል ። ታላላቆቻችን ስንፍና በተሞላው ትዕግሥት ይሸከሙናል ። ታዲያ የዚህ ሁሉ መደምደሚያ "ስለምንወዳችሁ" የሚል ነው ። እርግጥ ነው ፍቅር አለው ግን በጎነት የለውም ። ፍቅርና በጎነት እንዲህ ይተረጎማል ፦ ጠዋት በማለዳ ከቤተክርስቲያን መልስ መንገድ ላይ የምናገኘውን ሰው ''እንደምን አደርግ" ? ስንል ''እግዚአብሔር ይመስገን" እንደሚለን ሰው እንደ ማለት ነው ። በርግጥ በዛሬው ዘመን በጣም የሚያስለቅሱ ተግባራትን እያየንና እየሳማን ነው ። እንዴት አደርክ/ሽ ላለማለት መንገድ ቀይሰው የሚያልፉ ሰዎች እንደማየት ምን ይከብድ ይሆን !? ወገኖቼ ሰላምታ የከበደበት ዘመን ላይ ደርሰናል ። እንዴት አደርክ ማለት ፍቅር ነው ። እግዚአብሔር ይመስገን እንዲል ማድረግ ነወና ። ማስባልም በጎነት ነው ። ዛሬ ቤተሰቦቻችን ቤተክርስቲያናችን ፣ መሪዎቻችን ፣ ትምህርትቤቶቻችን ፣ ማህበረሰቦቻችን ፣  ከበጎነት ላልቷል ። የሚያሳየው ፍቅር እንጂ የሚሰጠው በጎነት አጥቷል ። "እንዴት አድርክ" ሲሉት "እንደዚሁ" የሚል ይመስላል ። ፍቅር ያለ በጎነት ምንም ስለሆነ ምንም ማለት አይቻልም ። ከጸባዖት የሚመነጭልን የእግዚአብሔር ፍቅር ወራጁ በጎነት ስለሆነ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስና እስከዘላዓለም አይነጥብም ። ለድሆች ሳንቲም ብቻ አይደለም የተስፋ ቃል በጎነት ያስፈልጋቸዋል ። ለሕፃናት አሻንጉሊት ብቻ አይደለም ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክም ያስፈልጋቸዋል ።  ልብስና ጫማ አይደለም የልብ ካባ ወደሆነችው ቤተክርስቲያን ልንመራቸው ይገባል ። አዎ ፍቅር ምንጭ ነው። በጎነት የፍቅር ወራጅ ውኃ ነው ። በረሃ ውስጥ በውኃ ጥም የተቃጠለን ሰው ስለ ውኃ ብንተርክለት ምን ጥቅም አለው ? ። ከማውራት ለተጠማው ሰው መስጠት  ይጠቅማል ። ፍቅር ንግግር ብቻ ስለሆነ በጎነት በሚባል መርህ ሊገለጥ ይገባል ። ከፍቅር ላልቶ በመለያየት ላይ ያለው በጎነት ዳግም በእያንዳንዳችን የልብ ጓዳ 
1.7K views ŵūšţę, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:57:43 ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ፡፡
የሚታየውን ግዙፋኑን የማይታየውን ረቂቁን የፈጠረ፡፡ ዘያስተርኢ ሐተታ፡፡ የሚታየው ግዙፋኑ ወዘኢያስተርኢ የማይታዩት ረቂቃኑ በርኅቀት በርቀት፡፡ በርኅቀት አድማስ ናጌብ ብሄሞት ሌዋታን በርቀት ነፍሳት ነፋሳት መላእክት ናቸው አንድም ዘያስተርኢ በዘፈቀደ የሚገለጥ ወዘኢያስተርኢ፡፡ በባሕርዩ የማይገለጥ አንድም ለበቁት የሚገለጥ ላልበቁት የማይገለጥ፡፡ አንድም ዘይርኢ ወዘኢያስተርኢ ይላል ፡፡ የሚጠብቅ ሲጠብቅ የማይታይ፡፡
ወነአምን በ፩ዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ
በተለየ አካሉ አንድ በሚሆን አንድም በባሕርይ በሕልውና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ በሚሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፡፡
ወልደ አብ ዋሕድ፡፡
ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው የአብ የባሕርይ ልጁ በሚሆን፡፡
ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም፡፡
ዓለም ሳይፈጠር በሱ ሕልውና፡፡ አንድም ከሱ ጋራ እንደሱ በነበረ፡፡
ብርሃን ዘእምብርሃን፡፡
ከብርሃን ከአብ በተገኘ በብርሃን በወልድ፡፡
አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን፡፡
ከባሕርይ አምላክ ከአብ በተገኘ በባሕርይ አምላክ በወልድ፡፡
ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ፡፡
በተወለደ ወአኮ ዘተገብረ ባልተፈጠረ፡፡ ሐተታ አርዮስ ሸክላ ሠሪ መሥሪያውን ሠርታ እንድትሠራ ደበናንሳ መዶሻውን ሠርቶ ዘመደ ሐፃውንትን እንዲሠራ ፈጥሮ ፈጠረበት ይላልና ወአኮ ዘተገብረ አለ፡፡
ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፡፡
በሥልጣን በጌትነት በባሕርይ ከአባቱ ጋራ አንድ በሚሆን፡፡
ዘቦቱ ኲሉ ኮነ፡፡
ሁሉ በእርሱ ቃልነት በእሱ ህልውና የተፈጠረ
ወዘእንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ፡፡
ያለሱ ቃልነት ያለሱ ህልውና የተፈጠረ የሌለ፡፡
ወኢምንትኒ፡፡
ምንም የተፈጠረ የሌለ፡፡ ሐተታ አርዮስ ፈጥሮ ፈጠረበት ይላልና ወኢምንትኒ አለበት፡፡
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ፡፡
በሰማይ ያሉ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት መላእክት በምድር ያሉ ዕፀው አዕባን እንስሳት አራዊት ሰውም ቢሆን ያለሱ የተፈጠረ ምንም የሌለ፡፡
ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ
ዘበእንቲአነና ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት ፩ድ ወገን ስለእኛ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፡፡
ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ፡፡
ወተሰብአ እመንፈስ ቅዱስ ይላል አብነት እም፡ በ፡ ነው በግብረ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ሐተታ የከፈለ ያነፃ ያዋሐደ መንፈስ ቅዱስ ነውና ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፡፡ እም እና እም አንድ ወገን ነው እመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው የሆነ፡፡ አንድም መንፈስ ቅዱስ ከመክፈሉ የተነሣ እመቤታችን ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ ከማለቷ የተነሣ ሰው የሆነ፡፡
ኮነ ብእሴ፡፡
የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆነ፡፡ ወአመ ኮንኩ ብእሴ አውሰብኩ ብእሲተ ከመ ኲሉ ሰብእ እንዲል፡፡
ወተሰቅለ በእንቲአነ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ፡፡
የጳንጦስ ሰው ጲላጦስ ነግሦበት በነበረ ወራት ስለእኛ የተሰቀለ፡፡ ሐተታ፡፡ እንደ ሰማዕታት ዕሤት ሽቶ እንደ ሌባ እንደ ወምበዴ ስቶ አይደለምና በእንቲአነ አለ፡፡
ሐመ ወሞተ፡፡
ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ሞተ፡፡
ወተቀብረ
ተቀበረ፡፡
ወተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ውስተ ቅዱሳት መጻሕፍት፡፡
ንጹሐት ክቡራት በሚሆኑ መጻሕፍት እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ እሁብ እኩያነ ህየንተ ሞቱ ወአብዕልተ ህየንተ መቅበርቱ ወልድየ ዕርግ እምህዝዓትከ ተብሎ እንደተጻፈ አንድም በከመ ጽሑፍ ዓርገ ይላል፡፡
ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት፡፡
በብርሃን በቅዳሴ በክብር በሥልጣን ዐረገ፡፡
ወነበረ በየማነ አቡሁ፡፡
ባባቱ ዕሪና ኖረ፡፡ ሐተታ፡፡ ንጉሥ የተጣላውን ሰናፊል አትታጠቅ በትር አታንሣ እንዲህ ካለ ቦታ አትውጣ ብሎ ቦታ እንዲወስንበት ቦታ ወሰነበት ማለት አይደለም፡፡ በምልዓት ሲል ነው እስመ ብሂለ የማን ይመርኅ ኀበ ተዋሕዶቶሙ በክብር እንዲል ነበረ የእንግድነት የማን የባለቤትነት ነው፡፡ አንድም ነበረ የባለቤትነት ነው፡፡ እንግዳን ንበር ይሉታል እንጅ ነበረ ይሉታልን፡፡
ዳግመ ይመጽእ በስብሐት፡፡
ዳግመኛ በብርሃን በሥልጣን በቅዳሴ ይመጣል፡፡
ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ፡፡
በሕያዋን በሙታን ይፈርድ ዘንድ አንድም ሕያዋንን ሙታንን ይገዛ ዘንድ ፡፡ ሐተታ ሕያዋን ያላቸው ጻድቃን ናቸው በነፍስ ሕያዋን ናቸውና አንድም በነፍስ ሕያዋን የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና አንድም የሕያው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናቸውና ሙታን ያላቸው ኃጥአን ናቸው በነፍስ ሙታን ናቸውና አንድም በነፍስ ሙታን የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና አንድም የምውት የዲያብሎስ ማደሪያ ናቸውና አንድም ኃጥአንን ሕያዋን አላቸው ጸላእትየሰ ሕያዋን ወይኄይሉኒ እንዲል በዚህ ዓለም ሕያዋን ናቸውና ጻድቃንን ሙታን አላቸው ምውት አነ በኀበ ዓለም ወዓለምኒ ምውት በኀቤየ እንዲል የሹትን አያገኙትምና አንድም ኃጥአንን ሕያዋን ሙታን አላቸው ሕያዋን እስከዕለተ ምጽአት ሙታን ከዕለተ ምጽአት በኋላ አንድም ሕያዋን አላቸው በዚህ ዓለም ሙታን አላቸው በወዲያው ዓለም አንድም ሕያዋን አላቸው በሥጋ ሙታን አላቸው በነፍስ አንድም ጻድቃንን ሕያዋን ሙታን አላቸው ሙታን አላቸው እስከዕለተ ምጽአት ሕያዋን አላቸው ከዕለተ ምጽአት በኋላ አንድም ሙታን አላቸው በሥጋ ሕያዋን አላቸው በነፍስ አንድም ሙታን አላቸው በዚህ ዓለም ሕያዋን አላቸው በወዲያው ዓለም፡፡
ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ፡፡
ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም ሐተታ፡፡ ዳዊት ሰሎሞን ቢገዙ ዐርባ ፤ ዐርባ ዘመን ነው ያውም እስከ ዳን እስከ ቤርሳቤህ ነው የሱ ግን ፍጻሜ የለውምና፡፡
ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ፡፡
የባሕርይ ገዢ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን፡፡
ዘሠረፀ እምአብ፡፡
ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የሠረፀ፡፡
ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ፡፡
ከአብ ከወልድ ጋራ እንስገድለት እንደ አብ እንደ ወልድ እናመስግነው፡፡
ዘነበበ በነቢያት፡፡
ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት ብለህ ግጠም ከአብ ከወልድ ጋራ በነቢያት አድሮ የተናገረ ንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ከአብ ከወልድ ጋራ እናመስግነው፡፡
ታሪክ ከጉባዔ ኒቅያ እስከ ጉባዔ ቍስጥንጥንያ ሃምሳ አምስት ዓመት ነው በዚህ ጊዜ መቅዶንዮስ ለአብ መንበር እንዳለው እግዚአብሔርሰ ይነብር ዲበ መንበሩ ቅዱስ ተብሎ ተነግሯል ለወልድ መንበር እንዳለው መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ተብሎ ተነግሯል ለመንፈስ ቅዱስ ግን መንበር እንዳለው የተነገረበት ቦታ የለምና ሕፁፅ ነው ብሎ ተነሣ ንጉሡ ዘየዓቢ ቴዎዶስዮስ ነው በቍስጥንጥንያ ጉባዔ ይሁን ብሎ አዋጅ ነገረ በዚህ ምክንያት መቶ ሃምሳ ሊቃውንት ተሰብስበዋል አፈ ጉባዔው ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት ነው ኢይቤ ሠናየ ይቤ አብ ኢይቤ ሠናየ ይቤ ወልድ አላ ይቤ፤ ይቤ ሰናየ መንፈስ ቅዱስ በአፈ ሲሳይያስ ነቢይ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዋኅ ወብሩህ ያለውን ይህን ባለመንበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ተርጉሞብሃል ብሎ ረትቶበታል በዚህ ጊዜ እሱን ተከራክረው ረትተው አውግዘው ለይተው ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ብለው ጨምረውበታል፡፡
1.2K views ŵūšţę, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:57:39 አንዲት ባለ ትዳር ሴት ናት አሉ ። ምን አሉ ? ካላችሁኝ ባለቤቷ ለጉዳይ ወደ ክፍለ ሀገር ይሄዳል ። በሄደበት ቀን ምሽት አንድ ወንድ ቤቷ ሲገባ በበበሩ እያለፈ ያለ የባለቤቷ ጓደኛ ያያል ። ጎራ ብሎ ሰላም ለማለት ፈልጎ አሁን እንግዳ ሲገባ እያየው እንዴት ጎራ እላለሁ ብሎ አለፎ ቤቱ ገባ ። እንደገና ጠዋት ወደ ስራ ሲሄድ ያ ማታ ያየው ወጣት ጠዋት ተሸፋፍኖ ሲወጣ ሴትዮዋም ስትሸኘው ያየል ። እንደገና ማታ ከስራ ሲገባ ያ ጠዋት ተሸፋፍኖ የወጣው ልጅ በር ተከፍቶለት ይገባል ። ውስጡ ቢጠራጥርም የጓደኛው ሚስት መልካም እንደሆነች እያሰበ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ያልተዘጋውን በር ያንኳኳል ግባ የሚል የለም ። ምርጫ ሲያጣ ሰተት ብሎ ቤት ሲገባ ከሳሎኑ መኃል በተዘረጋ ፍራሽ ላይ የጎደኛው ሚስት ከሰውየው ጋር ስትማግጥ ይመለከታል ። ሚስቲቱም ባለችበት ወጣቱም ባሉበት ደንግጠው ቀሩ  ። የባለቤቷ ጎደኛም ወዲያው ደንግጦ ወጣና እንደ ንጋቱ ይህን ነገር ለጓደኛዬ ከነገርኩት ይህ ትዳር ይፈርሳል ፤ ስለዚህ ልምከራት ቃል ላስገባትና ይህን ድርጊት ታቁም ብሎ ወደ ቤቷ ያመራል ። አሁንም ያልተዘጋውን ቤት አንኳኳ የሚከፍት የለም ። አንደፈረደበት ሰተት ብሎ ገባ ። ድንጋጤያቸው የደቂቃ የነበረው ያች ሴትነ ወጣት እንደ ትናንትናው በዛው ቦታ እየተሳሳሙ ያገኛቸዋል ። በዚህ ጊዜ ሚስት ''አንተ ሰውዬ ነጻነት ስጠን እንጂ" አለችው ይባላል ። ነጻነት ይህን ያህል ቀሎብናል ። እንዲህ ቀሎ እንደማየትም የሚከብድ ነገር የለም ።

ሀገር ከነጻነት የላላበት ዘመን ይህ ዘመን ነው ። ይህ የነጻነት ሰንሰለት እንዲላላ ወንዱ በወንድነቱ  ዓብዮት ከፍቷል ። ሴቷም በሴትነቷ ዓብዮት ከፍታለች ። ይህ የተከፈተ ዓብዮት አንድነት በሚባል አዎጅ ካልተሻረ ከጣሊያን በእጥፍ የሚበልጥ ወረራ እንደሚመጣብን ማሰብ ተገቢ ነው ። ይህ የነጻነት ሰንሰለት እንዲጠብቅ የሕይወት መጽሐፍ እንዲህ ይመክራል ፦ “እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤” / ምሳሌ 2፥7 / ይላል  ። የነጻነት ሰንሰለት እንዲላላ ምቀኞችና የነውርን ካባ እንደ ፅድቅ የለበሱ ሰዎች ትልቁን ሚና ይጫወታሉ ። የሕይወት መጽሐፍ ግን እንዲህ ይመክራል ፦“እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤” / ምሳሌ 2፥7 /  ። ቅንነት ውሳኔ ነው ። ያለነውር መገኘትም ለአምላክ ዘመንን መስጠት ነው ። ይህ ሰንሰለት በምን ይጥበቅ ስንል በውሳኔ ነው ። የፍቅር ውሳኔ ያስፈልጋል ። ሰውን እንደ ሰው ብቻ የሚቀበል የፍቅር ውሳኔ ያስፈልጋል ። ሀገርን ለማሻገር የአንድነትና የህብረትን ውሳኔ መወሰን ያስፈልጋል ። ሰባኪው  በስብከቱ ፤ የሃይማኖት አባቶች በስልጣናቸው ፣ ጎበዞች በጉብዝናቸው ፤ ቤተሰብ በመሪነቱ ፤ ሕፃናት በአስተዳደጋቸው  ፤ ሽማግሌዎች በሽምግልናቸው ፤ ሰራተኛው በስራው ፤ ነጋዴው በንግዱ ፤ አስተማሪው በአስተምህሮቱ ፤ ተማሪው በታናሽነቱ ፤ ጸሐፊው በድርሰቱ የፍቅርን ፣ የቅንነትን ውሳኔ መወሰን አለበት ። ያኔ ሀገሩቱም ድኅነትን ፤ ነፍስም የመለኮትን ጋሻ ትታቀፋለች ። የመጽሐፉን ክፍል በተከፈተ ልብ ድግምን እናስተውል ፦ “እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤” / ምሳሌ 2፥7 / ። አዎ እንዲህ ሲሆን ሀገር ከነጻነት ጋር  የእድገትን አክሊል ትቀዳጃለች ። እግዚአብሔር ያስበን !

በአንድ የገጠር ቀበሌ ማህበር ውስጥ አንድ  ሰው በሸለቆ ውስጥ ተገድሎ ንገኛል ። ይህን ያዩ የአከባቢው ነዋሪዎች ለቀበሌው ቅርብ በሆነ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ ። የከተማው ፖሊስም ጉዳዩን ሊያጣራና ሊመረምር ወደ ተገደለው ሰው ያመራል ። ብምርምር ሰዓት ታዲያ ለመሞቱ መሰረጃ የሚሆን ነገር ፖሊስ ያገኛል ። በሟች የኪስ ቦርሳ ውስጥ 500 ብር ተቀምጧል ። ፖሊሶችም እንዲህ ሲሉ ተማከሩ ፤ ይህን ሰው ሸፍታ ወይም ሌባ አልገደለውም ።  ሌባ ቢገድለው ንብረቱን በሰረቀ ነበር አሉ ። ስለዚህ ወደ አንድ ፍንጭ ተጠጉ ። ሟች በሽፍታ ሳይሆን በደመኛ እንደተገደለ ። በዚህ ጊዜ የአከባቢውን ማህበረሰብ ሟች ከማን ጋር ደም እንደተቃባ ያጠያይቁ ጀመር ። በዚህ ፍንጭ መሠረት ከቀናት መርምር በኋላ ገዳይ ተገኝቶ ፍርድ ፊት ይቆማል ። ዳኛውም ጥያቄን ጀመሩ ፤  እንደዚህ የሚባል ሰው ፣ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት ፣ በእንዲህ ዓይነት ቦታ ገድለሃል ? ገዳይም መለሰ አዎ ጌታዬ ገድያለሁ ። ዳኛውም በአንዴ ማመኑን እየገረማቸው ጠያቄውን ቀጠሉ  ፤ ጥሩ እሺ በሟች የኪስ ቦርሳ ውስጥ 500 ብር ተቀምጦ ነበር ወስደሃል ? አሉት ።  ገዳይም አረ ጌታዬ ብሎ ከአንገቱ ላይ ክር መዞ መስቀሉን እያሳየ እኔኮ ማሕተም ያሰርኩ ሰው ነኝ እንዴ አሰርቃለው ?! አለ ይባላል ። መስረቅን ለሃይማኖት መግደልን ለጀግንነት የሚጠቀሙ ሰዎች አሉ ። በሃይማኖት ስም ነግደው የማይደክማቸው የነፍስ ሌቦች ዛሬም አሉን ።  ዛሬም ሃይማኖት በወኔ ተይዟል ። በዚህ ምክንያት ሃይማኖታችን ማፍራቷ አይደለም መራመዷ አሳስቦናል ። ዘር ሞቶ ያፈራል እንጂ ገድሎ አያብብም ። ሃይማኖትም ለእውነቷ ሞታ ብዙ እውነቶችን ታፈራለች ። ክርስትና ሃይማኖትኝነት ማለት የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው ። ብዙ ገዳማት በመዞር የሚመጣ ፍሬ የለም ። ከእኛ በላይ ፈረንጆቹ ገዳሞቻችንን  ይጎበኛሉ ። ትሁት ሰው ለመባል ያልቆሸሸ የጳጳስ ቀሚስ የሚያራግፉ ፣ የቅዳሴው ዜማ ሲሰበር ልቤን ያዙልኝ የሚሉ ፣ ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ሳይታይባቸው በፅላቱ ፊት ሰማኒያ የሚሰግዱ ፣ ለሰይጣን እንተርቪዉ እልልታቸው ገደብ የሌለው ፣ ለአንዲት እውነት እራስ ምታታቸው የሚጨምር ፣ የክርስቶስን የመስቀል ሥራ በሠራቸው የሚያግፋፉ ፣ እንደ ባሕታዊ ሰላሳ መስቀል አንግታቸው ላይ አስረው አንዳች የመስቀል ሕይወት የሌለባቸው ፣ ለእግዚአብሔር ቤት መቅናት በሚመስል በብጣሽ ወረቀት አገልጋይን ወደ ዓለም የሚሰዱ ፣ በሩን የማይሰብኩ  በሩን የማይለቁ የሃይማኖት ተምክህተኛች ፣ ውግዘትና አለማመን የተምታታባቸው የሃይማኖት ዘብ ቋሚዎች ፣ ሀገራችን በሰማይ ነው ብለው እያዘመሩ ዕርስቴ ተነካ ብለው መሪ የሌለውን ትውለድ ወደ ሞት የሚሰዱ የሃይማኖት ጀግኖች የእምነት ደካሞች አፍርተናል ።

ሃይማኖት መሠረት አለው ። ከብዙ ሃይማኖት መሠረት ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የምታምንበት የሃይማኖት መሠረት የሚደንቅና ልብን የሚያሳርፍ ነው ። እኔ ከተማርኩት ሐተታውንና መልእክቱን እንዲህ ላካፍላችሁ ወደድኩ ። ሃይማኖት ምን መሆኑን በግልጽ ተመልከቱ ። ዓለም አቀፋዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሃይማኖት መሠረት ይህ ነው ፦

ነአምን በ፩ዱ አምላክ፡፡
በባሕርይ በሕልውና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ አንድ አምላክ በሚሆን፡፡
እግዚአብሔር አብ፡፡
በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፡፡
አኃዜ ኲሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር፡፡
ሁሉን የሚገዛ፡፡ አንድም ሁሉን የፈጠረ እግዚኦ አኃዜ ኲሉ ዓለም እንዲል፡፡ አንድም ሁሉን እንደ ጥና እንደ እንቁላል በመሐል እጁ የያዘ፡፡ ሰማይን ምድርን የፈጠረ ሰማየ ሰማያት ለእግዚአብሔር ብሎ ምድረሰ በሀበ ለእጓለ እመሕያው ካለው ሲለይ፡፡ አንድም ኢትፍርህዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ ካለው ሲለይ አንድም መላእክትን ደቂቀ አዳምን የፈጠረ 
1.2K views ŵūšţę, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:57:39 Nolawi ኄር:
የላላው ሰንሰለት

“እርሱ ለቅኖች ደኅንነትን ያከማቻል፤ ያለ ነውር ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፤” / ምሳሌ 2፥7 /


ተሰሪ በሰሪ ቦታ ሲሆንና ሰሪው በተሰሪው ዘንድ ስፍራ ሲያጣ ምድር ትጠባለች ። ሰሪ የተሰሪ ምንጭ ነው ። ተሰሪው ግን ሰሪውን ስፍራ አልሰጥም ማለቱ ከተሰሪነት ያጎድለዋል እንጂ ከሰሪው ዘንድ አንዳች ጉድለት አይሆንም ። ሰሪ ነው ለተሰሪ ስፍራ የሚሰጠው ። ተሰሪው ግን የእርሱ ባለሆነና በተሰጠው ስፍራ ስግብግብ ከሆነ የሚደንቅ ነው ። እንዲህ ያለ ተሰሪ የዚህ ዓለም አዝማሚያው ''የገና ጀምበር'' መሆኑን የማይስገነዘብ ነው ። የገና ጀብር ሌቱን ይጎትታል ፤ ቀኑን ያመሻል ። የገና ጀምበር ተፈጥሮን ያናጋል ሳይሆን ተፈጥሮን የትህምርት ርዕስ ያደርጋል ። በገና ጀምበር የምሽቱ ፍጥነት ይደንቃል ።  በገና ጀምበር ቀኑ ቶሎ ይመሻል ።  አስተውሉ ይመሻል ካልን መስፈርቱ ሠርክ አለው የሚል ነው ። ቶሎ ይመሻል ስንልም  ሰርክ የለውም እንደማለት ነው ። የዚህ ዓለም ክብር ፣ ሀብት ፣ ዝና ፣ ካባ  ተጠቅላይ ጨርቅ  ነውና ልክ እንደ ገና ጀምበር ፍስሐው ቶሎ  ይተናል ። ሀዘኑም (ሌቱም) ልክ እንደ ገና ጀምበር  ይረዝማል ። አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ሚዛናዊ ኑሮ መኖር በጣም ተቃሚ ነው ። ማግኘት ሲመጣ ማጣት የሚባል መጨረሻ እንዳለው ማሰብ ፤ የሕይወት ሌትም ሲመጣ እግዚአብሔር የደስታ ቀን ለእኛ እንዳለው ማሰብ ፤ ክፋትን ሲዘሩ ነጌን ማሰብ ፣ ሰው ቢከዳ የዘላለሙን ወዳጅ ጌታ  ማሰብ ፣ በዘረኝነት ውጥንቅጥ ውስጥ ስንገባ ሰው የተወለደው ዘሩን መርጦ እንዳልሆነ ማሰብ ተገቢ ነው ። እንዲህ ካልሆነ በሕይወታችን የገና ጀምበር የመጣ ዕለት ሌቱ በቀን  ቀኑ ከሌት ጋር ተደባልቆ ኑሮ መራራ ይሆናል ። በዓመት ልፋት ያዙኩት ያልነው ስልጣንና ሀብትም በዕለተ ሲፈርስ እናያለን ። ይልቅስ የገና ጀምበር የሆነብንን ኑሮ እግዚአብሔር በወራት መዋቅር  ውስጥ ለሚዛናዊ ኑሮ የሚደውለው ደውል ነው ። ታዲያ በዚህ በእኛ ዘመን እግዚአብሔር በቤተሰባችን ፣ በመንደራችን ፣ በማህበረሰባችን  ፣ በህዝባችን አልፎም በሀገራችን ላይ ያየለውን የገናን ጀምበር እንዲያነሳልን አጥብቀን  እንዲንይዘው የዘረጋልንን ሰንሰለት አታላሉት ይለናል ።

ከሁሉ በላይ ሀገራችን በገና ጀምበር ውስጥ ናት ። ለይቅርታ ቀኑ የሮጠባት ለቂም በቀል ሌቱ የረዘመላት ሆናለች ። ለአንድነት ሠርኩ የተሰወረባት ለዘረኝነትና ለጎሳ ሌቱ መስክ የሆነላት ሆናለች ። ለመልካሞች ቀኑ የመሸባት ለነውረኞች ሌቱ ክብር የሆነላት ሆናለች ። ጳጳስን ለማሰደብ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያላት ለወረዳ ባለስልጣት ወንበር የማይበቃት ሆናለች ። የምግባርና የሃይማኖት ክንፏ ሳይመሽ የነጠፈ በሌሊቱ ለእግዚአብሔር እቢ ያለች ጉደኛ ሆናለቸ ። የፍቅር አዋጇ  በሰርክ የደበዘዘ የጎሰኝነትን ድምፅ በሌቱ ያደመቀች ሆናለች ። ለክፋት ሌቱ አልበቃ ብሏት ለቀኑ ጨለማን የምታቀርበው አሀገሬ ታማለች ። አዎ ሀገሬ የገና ጀምበር ውስጥ ናት ። "የሀገርን ፍቅር ዜጋ አከሰረው ትናንትን ዛሬዎች ቀበሩት" የሚሉኝን ከሁለት ዓመት በፊት ያገኛዋቸውን አባት መቼም አልረሳም ። ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዊ አትሆንም ፤ ሀገርም የምትበጠበጠው መታወቂያው ላይ ዜግነት በሚለው ቦታ ላይ ኢትዮጵያዊ የተባለለት ሰው ነው ማለታቸው ነው ። እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ሰው ለማድረግ ሰው ሆኗል ። ይህ ቀሎብን ሰው እንደ ላስቲክ እናቃጥላለን ።  ለዛውም  ልክ እንደ ጀግና ይህን እናወራለን ። ለማያፍር የምናፍርበት ዘመን ይህ ዘመን ነው ።  ኢትዮጵያዊ ዛሬ እዚህ እንድትደርስ የተከፈለ ዋጋ አለ ። የዘመኑ ትውልድ ግን ኢትዮጵያን ዛሬ ያደረሳትን አንድነት ሳይሆን ትናንተ ኢትዮጵያን  ባፈረሳት ታሪክ ተዘፍቆ ዛሬን አጨልሟል ። አዎ ትናንትን ዛሬዎች ቀበሩት ሀገርን ዜጎች አከሰሩት የተባለው ለዚህ ነው ። ይህ በርግጥም ልብን በሀዘን ይሞላል ።  እኚህ አባት ይህን ሲሉኝ ብደነግጥም ''እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ጥሎ አይጥልም" እያሉ የሚደልሉንን አዝማሪዎች ሳልረሳ በእግዚአብሔር ተስፋ አለኝና ስለ ሀገሬ በዛ ሰዓት ወደ ልቤ ይህ ድምፅ መጣ ፦

"ሀገሬ ስንዴ ናት እንክርዳድ ማይከብዳት ፤
በውድማው ነፋስ ቅለቱ ሚደንቃት ፤
የአራሹ ደስታ ስንዴን ማትረፉ ነው ፤
የመሬቱ ሀዘን እንክርዳድ ማብቀል ነው" ።

በስንዴን ማሳ እንክርዳድ እንደ ባለ ዕርስት የሚጋራ በሚመስል መልኩ በቁመት እና በመልክ ይመሳሰላል ልዩነቱ ግን ፍሬ ላይ ነው ።  ሰው ስለምንሰራው ሰራ ሀሳብ መስጠት ይችላል ። ስራው ባመጣው ፍሬ ግን የሚሰጠው አሰተያየት አይኖርም ። ምክንያቱም ፍሬ የባለቤት እንጂ የባለ ሀሳቦች አይደለምና ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አልፎም ዓለምን ስንዴ አድርጎ እንክርዳዷን እንድታራግፍ የዘረጋው ሰንሰለት አለ ። ሰንሰለት ትልቁ ስብከቱ መያየዝና መያዝ ነው ። ታዲያ እግዚአብሔር የሰጠን እነኚህ አያያዥ ወይም የምድር ዋና ማዕከላት ዛሬ ላልተው እንደማየት የሚያሳዝን ነገር የለም ።  ምን ላልቶብን ይሆን ? ስንል ፦

ሀገር ከነጻነት ላልቷል ፤

ሃይማኖት እግዚአብሔርን ከመፍራት ላልቷል ፤

ፍቅርም ከበጎነት ላልቷል ፤

መውደድም ከአክብሮት ላልቷል ፤


ሀገር እንዴት ፈረሰች እንጂ ለምን ፈረሰች የሚል ትውልድ አጥተናል ። ሀገር ከነጻነት መላላቱ  ትናንትን ዛሬዎች ሲከድኑት እንደማየት ነው ። ለሀገር ትልቁ ጠላት የውጪው ሳይሆን የውስጡ ነው ። ዛሬ ከቅድስ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዓመታት የተሰረቁ ቅርሶች በጣም ያሳዝኑ ይሆናል ። በሕግና በታሪክ ምሥክር ለቤተክርስቲያኗ ቀን ወጥቶ ይመለስላት ይሆናል ። ከዚህ በልያ ግን ዛሬ በነጮች የተሰረቀው ወጣታችን ልብ ይሰብራል ። አንድ ወጣት መቼም ከልቤ አይጠፋም ። የነጮችን ዘፈን በጣም ያዳምጣል ። አለባበሱ አነጋገሩ ዘፋኙን ሆኗል ።  ቀበቶ ባልጠፋበት ምድር ሱሬው እጉልበቱ ላይ ይዳዳል ። ታዲያ አንድ ቀን ከጎኔ ተቀምጦ 12ኛ ክፍል በሚመማርበት ወቅት የእንግሊዝኛው ዘፈን በቃል ይዞት ይለዋል ። እኔም እንዴት ትሰማለህ ? ሳይሆን ለምን ትሰማለህ ? በማለት ጠየኩት ። የመለሰልኝ መስል ዛሬም ይደንቀኛል ። "university ስትሄድ ምን ልትሆን ነው" ? ሲል ይህን መራራ መልስ መለሰልኝ ። በዚህ መልሱ የሀገሬን ትውልድ መረመርኩ ። ታዲያ በአከባቢዬ ያላገኘውን ሰው አልነበረም ።  እርሱ ከጎኔ ሆኖ በጆሮዬ ስለሰማሁት ነው እንጂ ከሩቅ በልብ የምሰማቸው ወጣቶች ነበሩ ።  ስለ ዘፈን ብዙዎችን ጠየኩ የሚመልሱልኝ መልስ እንኳን ለእግዚአብሔር ለሰውም መራራ ነው ። እንዲህ በጥቁቱ በነጮጩ የሚሰረቅ ትውልድ ሀገርን ከነጻነት ባያሳማማ ምን ይደንቃል ?! ። የሀገሩን በሔራዊ መዝሙር የማያውቅ  የነጮችን ዘፈን ግን በቃሉ የሚያውቅ ትውልድ እኮ ነው ያመረትነው ። ከጠላት በላይ ትልቁ ጠላት የራስ ዜጋ ጠላት ሲሆን ነው ። በዚህ ሳምንት ውስጥ ብዙ ወጣቶችን ስለነጻነት ጠየኩ ብዙዎቹ የንግግራቸው አዝማሚያ መግደል ነው ። መግደል ለምን ? ስልም የጣልያንን ጀግኖች ይጠቅሳሉ ። የጣልያን ድል አድራጊ ህዝባችን ድሉ ጦር ብቻ ሳይሆን ይቅርታም እንደነበር ብዙዎቹ አላስተዋሉም  ። እንደ ዛሬ ሀገራችን የጎሰኝነትን ካባ ከመደረቧ በፊት ንጹህ በፍታዋ ይቅርታ እንደነበረ ታሪኮች ይመሰክራሉ ።
1.5K views ŵūšţę, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:37:33 ❝ ምን ያህል አፈቅራለሁ የሚለውን የምንለካው ያፈቀርነውን ሰው ስህተቱን በታገሥነው መጠን ነው❞

@Nolawiiher
@Nolawiiher
1.8K views ŵūšţę, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 09:13:05
1.9K views ŵūšţę, 06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ