Get Mystery Box with random crypto!

​​​ ሮ ማ ን ክፍል ...በትናንትናው ቀፋፊ ቀን ከአለቃዬ | NK_Etertainment

​​​ ሮ ማ ን

ክፍል

...በትናንትናው ቀፋፊ ቀን ከአለቃዬ ጋር በመጣላቴ በንዴት ስራ አልገባሁም ነበር፡፡ ቀኑ ብርዳምና አልፎ አልፎ እንደህፃን ልጅ ሽንት እየተቆራረጠ የሚዘንብ ካፊያ ዝናብ የነበረበት ቀን ነው፡፡
የጥጥ ነጋዴ የሚያስመስለኝን ወፍራም ካፖርት ለብሼ የለመድኳት ካፌ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ፡፡ ራሴን ከብርዱና ከንዴቱ ለመገላገል አስቤ ኪሴ ውስጥ ያከማቸሁትን የተጨማተረ ሲጋራ በጣቶቼ እያልመዘመዝሁ በላይ በላዩ ማጨሴን ተያያዝኩት፡፡
ካፌዋ ‹ማጨስ ክልክል ነው› የሚል ማስታወቂያ የተለጠፈባት ቢሆንም ለኔ አይሰራም፡፡ ደንበኛቸው ስለሆንኩ አንድም ቀን ተናግረውኝ አያውቁም፡፡
ያዘዝኩትን ቡና አጋምሼ ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀመጥኩት አንዲት ሴት ወደኔ ተጠግታ ሰላምታ አቀረበችልኝ፡፡ የለመድኩት ፍርሐቴ መጣ፡፡

ለሰላምታዋ ምላሽ ለመስጠት ዘገየሁ፡፡ ወደውስጥ የሳብኩትን የሲጋራ ጭስ ረሳሁት፡፡ ሳንባዬን አስጨንቆት ኖሮ በትንታ ተጣደፍኩ፡፡
ልጅቷ ተደናግጣ ስትመለከተኝ ቆየችና ‹‹ይቅርታ›› አለችኝ፡፡ ከዚያም ከጎኔ ያለውን ወንበር በጣቷ እያመለከተች ‹‹ወንበሩ ሰው አለው?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ አንገቴን ግራና ቀኝ በማወዛወዝ ሰው እንደሌለው አሳወቅኳት፡፡ ቁጭ አለች፡፡

የተቀባችው ሽቶ አፍንጫዬን አልፎ ወደ ውስጤ ሲገባ አንዳች ልዩ ስሜት ውስጤን አናወጠው፡፡ እንደምንም ቀና ብዬ ለአፍታ አየኋት፡፡ ፀጉሯ አጭር ሲሆን የፊቷ ውበት ግን እንከን አይወጣለትም፡፡ ላነጋግራት ብፈልግም ቃላቶች ለዚያን ሰዓት ያልተፈጠሩ ይመስል አንደበቴ ዝግ ሆነ፡፡ በቃ ዝም-ዝም፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ‹‹መተዋወቅ ጥሩ ነው....እንተዋወቅ የኔ ስም ሮማን ወርቅ ይባላል ›› አለችና እጇን ዘረጋችልኝ፡፡ ፈገግታዋ ልብን ያሸብራል፡፡

እጆቼ እንዳይንቀጠቀጡ በመጠንቀቅ የተዘረጋውን እጇን ጨበጥኩትና የኔንም ስም ነገርኳት፡፡ ከዚያ ስለዓየር ሁኔታው፣ ስለተቀመጥንበት ወንበርና ስለሌሎችም ነገሮች አወራን፡፡ ብዙውን እሷ ናት የምታወራው፡፡

ሮማን ያዘዘችውን ማኪያቶ በማንኪያ እያገላበጠች ሲጋራ የጨበጥኩበትን እጄን ደጋግማ ስታይ ማጨስ የፈለገች መሰለኝና ከተጨማደዱት ሲጋራዎቼ አንዱን አውጥቼ ጋበዝኳት፡፡ ትንሽ ፈገግ ብላ እንደማታጨስ ነገረችኝ፡፡ አላግደረደርኳትም፡፡ ለራሴው አጨስኩት፡፡

ይቀጥላል...
ክፍል 4 ይቀጥል

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

NK_entertaiment
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━