Get Mystery Box with random crypto!

​​​ ሮ ማ ን ክፍል ....ፈገግ አለች፡፡ ፈገግታዋን ከመብረቁ ብልጭ | NK_Etertainment

​​​ ሮ ማ ን

ክፍል

....ፈገግ አለች፡፡ ፈገግታዋን ከመብረቁ ብልጭታ ጋር ማወዳደር ጀመርኩ፡፡ በምድር ስትመጣ እንዳላየኋት ሁሉ ከሰማይ የወረደች መሰለኝ፡፡ እኔም ፈገግ አልኩላት፡፡ ጥርሶቼን ግን አልገለጥኳቸውም፡፡
ሁሌም እንዲህ ነኝ፡፡ በዓይኖቼ እንጅ በጥርሶቼ አልስቅም፡፡ በልጅነቴ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ አይኖቼ እንደሚያምሩ ይነግሩኝ ስለነበር

ከጥርሶቼ ይልቅ በአይኖቼ እኮራለሁ፡፡ በርግጥ ያኔ ጥርሶቼ ያምሩ ነበር፡፡ ዛሬ ግን በሲጋራ ጭስ በልዘው አፌን የሲኦል መንገድ አስመስለውታል፡፡

ሮማን እጆቿን ለሰላምታ ዘረጋችልኝ፡፡ ስለኔ ጥርስና ስለእሷ ውበት እያሰብኩ ለሰላምታ የትኛውን እጄን መዘርጋት እንዳለብኝ ጠፋኝ፡፡ ሁለት እጆቼን አነባብሬ ሰጠኃት፡፡ በሚያማምሩ ጣቶቿ የቀኝ እጄን ለቀም አደረገችውና ለአፍታ በአይኖቿ ገላይን ከላይ እስከታች ዳበሰችው፡፡
ዛሬ ያለወትሮዬ ሽክ ብያለሁ፡፡ አለባበሴን እንደወደደችው ከአስተያየቷ ተረዳሁ፡፡ ከጓደኛዬ የተዋስኩትን ጥቁር ሱፍ ጀርባዋ ከተቀደደ ባለነጠብጣብ ሸሚዝ ጋር ለብሻለሁ፡፡
የጨበጠችውን እጄን ሳትለቅ ‹‹ ወደመናፈሻው እንግባ?›› ስትል ጠየቀችኝ፡፡ ስትናገር የምትዘፍን ትመስላለች፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›› አልኳት ሊስም ፈልጎ ያሞጠሞጠ ከንፈሬን ወደ ቦታው እየመለስኩ፡፡

ሰላሳኛ አመቴን እየደፈንኩ ቢሆንም ካሁን በፊት የሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ፍቅሬን ለሲጋራ እንጂ ለሴት የሰጠሁበት ጊዜ አልነበረም፡፡ የወንድ ጓደኞቼ በየጊዜው ፍቅረኛዬ ናት እያሉ የተለያዩ ሴቶቻቸውን ያስተዋውቁኝና
‹‹ያንተን ፍቅረኛ ግን ለምን አታስተዋውቀንም?›› ይሉኛል፡፡
‹‹የለኝም›› ስላቸው አያምኑኝም፡፡
‹‹እንዴት ላይኖርህ ይችላል አንተኮ ለሴት እንጂ ለወንድ የማይገባውን ውበት ይዘሃል፡፡
መልከ መልካም ነህ፡፡ በዚያ ላይ ገንዘብ ባይኖርህ እንኳ አሪፍ ጭንቅላት አለህ፡፡ ታዲያ እንዴት ፍቅረኛ የለኝም ትላለህ?›› ይሉኛል፡፡ ዝም እላቸዋለሁ፡፡ እነሱን ለማስረዳት ከምሞክር ከአዲስ አበባ ባህርዳር በእግሬ ብጓዝ እመርጣለሁ፡፡ ፈፅሞ ሊያምኑኝ አይችሉም፡፡
እኔና እግዚአብሔር በምናውቀው ሃቅ ግን እኔ እንኳን ሴት ፍቅረኛ ሴት እህት የለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ቆንጆ ሴቶችን ሳይ ቀድሞ ጉልበቴ ይዝላል፡፡ ላብ በጀርባዬና በግንባሬ ይፈሳል፡፡ ያደኩት ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ከወንዶች ጋር ስለነበር ሴቶች ባሉበት ቦታ መገኘት ያስፈራኛል፡፡

ሴቶችን እንዴት ማናገር እንዳለብኝ እንኳን ጠንቅቄ አላውቅም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለሁ ጓደኞቼ ከሴቶች ጋር ‹በግተራ› ሲያመሹ እኔ ቤተመፅሐፍት ውስጥ ተቀብሬ ምሽቱን አሳልፍ እንደነበር አልዘነጋውም፡፡ አንዳንዴ ፍቅረኛ የሚኖረኝ መቼ ነው ስል እራሴን እጠይቅና አንድ ቀን በሚል መልስ እዘጋዋለሁ፡፡ እንዳልኩትም ያ - አንድ ቀን ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬ ከተፍ አለ፡፡

ይቀጥላል...
ክፍል 3 ይቀጥላል፡፡

•═••• NK_entertaiment •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••

━━━━✦ ✿ ✦━━━━━