Get Mystery Box with random crypto!

@newayekidisat @newayekidisat #በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው ዕ | ንዋየ ቅድሳት

@newayekidisat
@newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ዐርብ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ
ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» በማለት
እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት
የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን
ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው
የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል
የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዅሉ
መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል
በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ
ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን
ነው (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በዚያን ጊዜ
አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት
አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት
አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ‹‹ንጹሕ ደም
አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ›› አለ፡፡ @newayekidisat እነርሱ
ግን ‹‹እኛስ ምን አግዶን? አንተው
ተጠንቀቅ፤›› አሉ፡፡ ይሁዳም ብሩን በቤተ
መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት
አለቆችም ብሩን አንሥተው ‹‹የደም ዋጋ
ነውና ወደ መባዕ ልንጨምረው
አልተፈቀደም፤›› አሉ፡፡ ተማክረውም
ለእንግዶች መቃብር የሚኾን የሸክላ ሠሪ
መሬት ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ
ድረስ ‹የደም መሬት› ተባለ (ማቴ. ፳፯፥፫-
፱)፡፡
ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት
(ቁራኝነት) እንኖርበት የነበረው የጨለማ
ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት
ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች
ዅልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ የክርስቶስን
ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን የምናስብበት
ጊዜ ነው፡፡ @newayekidisat በሮማውያን ሕግና ሥርዓት
መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት፤
የሕይወት መቅጫ አርማ ኾኖ ሳለ ለእኛ ግን
የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤
በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን
በዚህም ምክንያት ዕለቱ ‹መልካሙ ዓርብ›
በመባል ይታወቃል፡፡

#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat