Get Mystery Box with random crypto!

@newayekidisat #በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው ዕለተ ሠሉስ (ማክሰኞ) | ንዋየ ቅድሳት

@newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ሠሉስ (ማክሰኞ)

ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው
ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም
መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት
ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ @newayekidisat ጥያቄውም ጌታ
ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት
ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት
ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ
መፍታትን ‹‹በማን ሥልጣን ታደርጋለህ?
ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር
(ማቴ. ፳፩፥፳፫-፳፯)፡፡ ጌታችንም «…
እውነት እላችኋለሁ፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች
ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት
ይቀድሙአችኋል፤›› ሲል አስተምሯል (ማቴ.
፳፩፥፳፰)፡፡

#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat