Get Mystery Box with random crypto!

የተዋህዶ ፍሬዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ netsifinalart — የተዋህዶ ፍሬዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ netsifinalart — የተዋህዶ ፍሬዎች
የሰርጥ አድራሻ: @netsifinalart
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 249
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም የዚህ ቻናል አባላት በዚህ ቻናል ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በእኛ አቅም የምናገኛቸውን መረጃዎች፣መዝሙራት እና ስርአተ ቤተክርስቲያንን እናቀርብላችኋለን፡፡
#አባቶችን_ጠይቅ_ይነግሩሃል_የእምነትን_ምስጢር_ያስረዱሃል

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-21 09:32:44 (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 9)
----------
1፤ ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።

2፤ ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፥ ማዕድዋን አዘጋጀች።

3፤ ባሪያዎችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።

4፤ አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች።

5፤ ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።

6፤ አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።

7፤ ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል።

8፤ ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፤ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል። ...
286 views▉▏▌▎▋▉, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:26:39 https://youtube.com/shorts/e-eV7p9SjQw?feature=share
79 views🅵🅸🅺🆁🅴, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:25:56 https://youtube.com/shorts/e-eV7p9SjQw?feature=share
78 views🅵🅸🅺🆁🅴, 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 14:07:54 ፕሮቴስታንት!
እስኪ ልጠይቃችሁ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
☞ልደት ብላ መወለዱን የምታበስረው
☞ጥምቀት ብላም መጠመቁን የምትናገርለት
☞ስቅለት ብላ ስለ ሰው ልጆች መዳን መሰቀሉን የምትሰብከው
☞ትንሣዔ ብላ ሞትና መቃብር ሊይዙት ስላልቻሉ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን የምትመሠክርለት
☞ዕርገት ብላ የመሬት ግራቪቲ ሳይቆጣጠረው በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የምታውጅለት እርሱ ማን ነው???
ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን???
ታድያ ለምንድን ነው በዚህ ሁሉ እውነት ቤተ ክርስቲያናችን ሌሊትና ቀን ወገቧን ታጥቃ የምትሰጠውን አገልግሎት አፍናችሁ ለመደበቅ የምትሞክሩት???
እስኪ ንገሩኝ!

ሁል ጊዜ ከመቃወም ይልቅ እውነቱ የቱ ጋር ነው የሚለውን ቆም ብላችሁ በሰከነ መንፈስ በትመለከቱት ግን ምንአለ???
.
አሁንም ልጠይቃችሁ!
ማርቲን ሉተር ከመወለዱ በፊት
የእናንተም የእምነት ድርጅት ከመመሥረቱ በፊት
እናንተም በዚህች ምድር ላይ መኖር ከመጀሠራችሁ በፊት
ይህች ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
በእርሱ እመኑ፡
ሥጋውን ብሉ፡
ደሙንም ጠጡ፡፡
እያለች ስለ እርሱ ስትመሰክርለት የኖረችው ዛሬም ከዚህ እውነት ፈቀቅ ሳትል ወገቧን ታጥቃ ሌሊትና ቀን ተግታ ይህንን እውነት የምትመሰክርለት እርሱ ማን ነው???
ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን???
.
በየጊዜውም በ6.ኢየሱስ በ7.ሥላሴ በ27.መድኃኔዓለም በ28.አማኑኤል በ29.በዓለ ወልድ...እያለች በዓላቱን የምታከብርለት በየ በዓላቱም ስለ እርሱ የምትመሰክርለት እርሱ ማን ነው???
ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን???
.
ቤተ ክርስቲያናችን በምትተርከው የቅዱሳን ታሪክ ውስጥስ 100%ቱን የሚሰበከው እርሱ ማን ነው???
ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን???
.
ስለዚህ ይህችን እውነት እናንተ ገንዛችሁ ብትቀብሯትም መነሳቷ አይቀርምና ነገ መቃብሯን አፍርሳ የተነሳች ቀን ግን ለእናንተ የመቃብሯ ጠባቂዎች ወዮላችሁ!!
.
"እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን...፡፡
1ኛቆሮ.1:23
"...እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።"
ሮሜ.9:5
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
99 viewsTesfanesh Seyoum(YSimoen), 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 13:42:08 + አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡

ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ

‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]

ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18

ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡

የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 18 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፎቶ :- CMC ሚካኤል
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
67 viewsTesfanesh Seyoum(YSimoen), 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 13:42:08 ++ምናለ ብታስተምረኝ++
በክብር በሞገስ በመወደስ ፈንታ
መቀመጥ እንድችል ከመዋረድ ተርታ
ስድብን እየሰማሁ ያለ አንዳች ሁካታ
ለመቆም እንድችል ልቤ ሳይረታ
ምናል ብታስተምረኝ ብታስችለኝ ጌታ!?
ለእኔም አስተምረኝ ባላጠፉት ጥፋት
በጸጋ መቀበል የአይሁድን ትፋት
እንዴት እንደሚቻል ሳያጉረመርሙ
ንገረኝ ጌታዬ ይረዳኝ ትርጉሙ!
የመናቅን ጥበብ የውርደትን ዘዴ
እባክህ አስረዳኝ አስተምረኝ አንዴ
ብዔል ዜቡል ተብለህ ያልተበሳጨኸው
የኃጢአተኞች ወዳጅ መባል ያልጠላኸው
ጋኔን ይዞታልን የሰማህ በጸጋ
ለእኔም አስተምረኝ በቂም አልወጋ!
አልወጋ እባክህ በመራርነት ጦር
በቁጣ ጥላቻ ነፍሴ አትሰበር
እንዴት ነበር ያኔ የይሁዳን እግር

ዝቅ ብለህ ያጠብኸው ስታውቅ ሁሉን ነገር?
ለእኔም አስተምረኝ ብዙ ሳልናገር!
በችንካር ተጣብቀህ ከመስቀሉ ጋራ
የደምህ ነጠብጣብ ገና ሳያባራ
አያውቁትምና የሚያደርጉትን
ይቅርታን የለመንህ ላጠጡህ ሐሞትን
ምናል ብታስተምረኝ እንዲህ ዓይነት ሕይወትን?
አሁን ምን ቸገረህ ብትሰጠኝ ለአንድ አፍታ
የትሕትናን ቀሚስ የትዕግሥትን ኩታ
እያየህም አይደል ነፍሴ እንዲህ ተራቁታ?
የመሰደብን ዘውድ የመናቅን ካባ
ምናለ ብትኖር ይ’ች ልቤ ደርባ!?
ትዕቢት ለተሞላው ለአትንኩኝ ባይ ልቤ
ለክብሩ ለሚኖር ለኮርማው ሃሳቤ
ምናለ ብትቀባው የትሕትናን ሽቶ
እንደዚህ ከሚኖር ሸትቶ ተበላሽቶ!?
ኸረ እኔ አልቻልኩም አቅቶኛል በጣም
ስድብን መቀበል ሐሜትን ማጣጣም

ስተርከው እንጂ ስኖረው አቃተኝ
ይህን መራር ኑሮ አንተው ይዘህ ጋተኝ!
እንኳን እንደ አንተ ዝም ልል ሲረግጡኝ
ቁጣዬ ነደደ ስለገላመጡኝ
ያንን ሁሉ ታሪክ ያን ሁሉ ጥቅስ ረሳሁ
በቂምና በቀል በጥላቻ ከሳሁ
እንደ አራስ ነብር ለክብሬ ተነሣሁ!
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ /
118 viewsTesfanesh Seyoum(YSimoen), 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 08:41:03 አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡

ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡

ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን ፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ
386 views▉▏▌▎▋▉, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 16:31:14 ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር
93 views▉▏▌▎▋▉, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 14:23:47
392 views▉▏▌▎▋▉, 11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ