Get Mystery Box with random crypto!

እኔ'ምለው… ቆይ ሰው ሲሞት የሚደገሰው ልክ ያጣ ድግስ ምንድን ነው? በሆነ ቪድዮ ላይ ጥቁር የለበ | Nehnu Tube ◈ ነህኑ ቲዩብ_||ኢስላማዊ ጥበብ||

እኔ'ምለው… ቆይ ሰው ሲሞት የሚደገሰው ልክ ያጣ ድግስ ምንድን ነው? በሆነ ቪድዮ ላይ ጥቁር የለበሱ ሰዎች ልክ እንደ ሰርግ ቡፌ ሲያነሱ ተመለከትኩ። ሟች ምን ያክል ቢበድላቸው ነው? ያስብላል። ጉዱን አላየ እርሱ ከሄደ በኋላ እየሆነ ያለውን!

ሌላው ደግሞ ሰው ሲኖር መቶ ብር እንኳ ቸግሮት በችግሩ ቀን ፊት የነሱትና ዓይኑን ማየት ያልሹት፣ ከርሱ ጋር አብሮ መሄድን እንደ መዋረድ የቆጠሩት፣ ለድሃ ከፍተኛ ንቀት ያለባቸው ዘመዶች የሞተ ቀን መኪና ይዘው ማጀባቸው ፋይዳው ምንድን ነው?


ሰዎችን ሲያገኙ ብቻ ሳይሆን ሲያጡም ቅረባቸው። ካለህ ስጣቸው፤ ከሌለህ ቢያንስ የሃሳባቸው ተጋሪ ሁንና አብሽሩ በላቸው።

ጥቅም ስታይባቸው ብቻ አትሽለጥለጥ።