Get Mystery Box with random crypto!

'ከችግር ጋር ምቾት አለ!' . ባይገባኝ ነው እንጂ. . . ዝናብ ሲወርድብኝ፣ጎኔን የቀፈፈው፣ ቀል | Nehnu Tube ◈ ነህኑ ቲዩብ_||ኢስላማዊ ጥበብ||

"ከችግር ጋር ምቾት አለ!"
.
ባይገባኝ ነው እንጂ. . .
ዝናብ ሲወርድብኝ፣ጎኔን የቀፈፈው፣
ቀልቤን ያዛነፈው፤
እድፌን ነበረ አጥቦልኝ ያለፈው!
.
ባይገባኝ ነው እንጂ. . .
መንገዴን አርዝሞ፣ከርታታ ያ'ረገኝ፣
ለእጦት የዳረገኝ፤
ላሟን ሊሠጠኝ ነው ወተት የነፈገኝ!
.
እግሮቼ ሲከዱኝ፣በላሁ አፈር-ድሜ፣
ተደፋሁ በአፍ-ጢሜ፤
መውደቄን ዐየና፣ረገፈልኝ ሸክሜ!
የቸገረው ሁሉ . . .
የወደቀው ሁሉ. . .
በእንከኑ ቅኝት፣ምስጢር ካስተዋለ፤
ከችግር ጋር ምቾት አለ!
ከህመም ጋር ድሎት አለ!
.
መነሻ ሐሳብ፦ ሱረቱል ኢንሺራሕ (የልብ መስፋት ምዕራፍ)

#ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ

▽▽▽◊◊◊ለመ ላ ል◊◊◊▽▽▽
t.me/NehnuTube ኢስላማዊ ጥበብ
ሀሳብ አስተያየት @Nehnu_Tube_bot

የዩቲብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ_ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCBQvGAsLudI4X5U3pHYBgtw