Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ ለሁሉም ********** ዛሬ የደህንነት አባላት ከተወሰኑ ፌደራል ፖሊሶች ጋር በመሆን ወደ | 💫 ነፋኢስ መልቲሚዲያ 💫 - Nefaes Multimedia

መረጃ ለሁሉም
**********
ዛሬ የደህንነት አባላት ከተወሰኑ ፌደራል ፖሊሶች ጋር በመሆን ወደ አስ ሱና ቴሌቨዠን ዋና መስሪያ ቤት ያለ ምንም ህጋዊ አግባብ፣ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዘው ብለው በመግባት ዛሬ መጅሊስ ያደረገውን ስብሰባ ለመቅረፅ የተላኩ ሶስት አባላትን ከተቀረፀው ፋይልና ላፕቶፕ ጋር ይዘዋቸው ሄደዋል። ይህ እርምጃ ልክ አይደለም:: ህጋዊ ተቋም ውስጥ ያለ ህግ አግባብ መግባትም ሆነ ፋይልና ሰራተኛ መውሰድ ፍፁም ከህጋዊነት የራቀ ነው። መጣራት ያለባቸው ጉዳዮች ካሉም በአግባቡ እንጂ በዚህ መንገድ መሆን አልነበረባቸውም። አሁንም የመንግስት አካላት ጉዳዩን በጨዋነት ይዘው እልባት ሊሰጡ ይገባል!