Get Mystery Box with random crypto!

ለህግ ይቅረብ ከጀርባው ልክ እንደሱ የባለገና ጭፍን ጥላቻ ያለው ባለስልጣን ሳይኖር እንዲህ ሊና | Natnael Mekonnen

ለህግ ይቅረብ

ከጀርባው ልክ እንደሱ የባለገና ጭፍን ጥላቻ ያለው ባለስልጣን ሳይኖር እንዲህ ሊናገር አይችልም:: ይህ ያልኩበት ምክንያት ቲክቶኩን በጥቆማ ገብቼ አብዛኛው ፎቶና ቪዲዮዎቹን ስመለከት ከተለያዩ አመራዎች ጋር ፎቶ አለው:: በኦሮሚያ ክልል ድሬድዋ ይመስለኛል ወይም ሃረር የብልጽግና ቢሮ ውስጥ ስብሰባ እንደሚመራ ሰው ተቀምጦ የተነሳቸው ምስሎች አሉ::

ልጁ ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ሜኖሶታ ሲሆን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው:: በዚህ ቪዲዮ ላይ የሚናገረው መረን የለቀቀና እጅግ አጸያፊ አንድ ማህበረሰብን የሚያንቋሽሽ አብሮ የመኖርን እሴት የሚሸረሽር አጸያፊ ስድቦችን የሚሳደብበትን ቪዲዮን ደግሜ እዚህ ላይ መለጠፍ ይቅርና ሰምቶ ለመጨረስም ያማል!!! እጅግ ይሰቀጥጣል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ በቀጥታ (Live) ይህን ሲናገር መስማት እጅጉን ያማል

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፌደራል ፖሊስ አዲስ አበባ ፖሊስ የብሔራዊ መረጃ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከወዴየት ነው ያላችሁት? ምንስ እየተከናወነ ነው???????!!!