Get Mystery Box with random crypto!

የመጋቢት ፍሬዎች አገራዊ ለውጡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው በለውጡ የተለውጡ ጠንካራ ተቋማት | Natnael Mekonnen

የመጋቢት ፍሬዎች

አገራዊ ለውጡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው በለውጡ የተለውጡ ጠንካራ ተቋማት አሉ፡፡ የአገራዊ ለውጡ አንዱ ፍሬ ይህ ነው፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለዚህ ማሳያ የሚሆን ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ በለውጡ ብቻ በ6 ዓመታት ብቻ ከ 100 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ሐብት መፍጠር የቻለ ነው፡፡

የኮንስትራክሽ ዘርፉን በማናቃቃትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስታዋወቅ እና የሬልስቴት ገበያው ይታይበት የነበረውን ያልተረጋጋ የገበያ ሁኔታና የዋጋ ጭማሪ በማረጋገት የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እንደ ደቡብ ኮሪያና ሲንጋፖር የመሰሉ አገራት ያሏቸውን መንግስታዊ ቅርጽ የተላበሱ የሬል-ስቴት ተቋማት ጋር ተመሳሳይነት ባላው መልኩ፡- እራሱን በዘመናዊ መንገድ እያደረጃ ያለና ፍጹም ኢትዮጵዊነትና የአገር ፍቅር ጎልቶ ከሚታይባቸው ተቋማት መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ተቋሙ ከነበረበት እጅግ ውስብስብ ችግር አንጻር ይለወጣል ብሎም የገመተ የነበረ ባይኖርም የመጋቢት ፍሬነቱን በተግባር እያረጋጋጠ ያለ ስኬታማ ተቋም ሆኖ ቀጥሏል፡፡