Get Mystery Box with random crypto!

#አይዴ_ጨምበላላ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ-ጨምበላላ በታላቅ ድምቀት በሀዋሳ ከተማ እየተ | Natnael Mekonnen

#አይዴ_ጨምበላላ

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ-ጨምበላላ በታላቅ ድምቀት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። አባቶች በሶሬሳ ጉዱማሌ የቄጣላውን ዜማ እያሰሙ ይገኛሉ።

የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ የሲዳማ ህዝብ በፊቼ-ጨምበላላ ከዘመናቶች በፊት ከአለም የቀደመበት ታሪካዊ ፍታህዊነትን ያሰፈነበት በመሆኑ ዛሬ ዓለም ያደረሰብ ፍትሃዊነት እና እኩልነት ሲዳማ ከዛሬ መቶ አመታቶች በፊት ሲያደርገው የነበረ ነው።

በመሆኑም በፊቼ ጨምበላላ አባቶች በትኬሻቸው ጋሻ/ወንቆ እና ጦር በመያዝ ቄጣላ የሚያደርጉበት ኩነት ያለው ሲሆን ቄጣላ ደግሞ የሲዳማ አባቶች ሃዘናቸውን እና ደስታቸውን ብሎም ስሜታቸውን የሚገልፁበት የዜማ ስልት ነው። ይህም ፊቼ ጨምበላላ በአለም ቅርፅነት በዩኔስኮ በPerformance ሂደት እንዲመዘገብ የቄጣላ ዜማ ስርዓት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ መሆኑንም ገለፀዋል።

በተለይም በከሰሞኑ የተመረቀው የአፊኒ ፊልም የሲዳማ ህዝብ ግጭት አፈታት ሂደት ላይ ትኩረት ያደረግ ሲሆን አፊኒ ማለትም (አወቃችሁ) ማለት ሲሆንን የአፊኒ የግጭት አፈታት ባህልም የተወሰደው ከዚህው ከጨምበላላ በዓል ላይ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቂም በበቀል እና በግጭት ፊቼ ጨምበላላ መክበር በፍፁም እንደማይቻል አቶ ጃጎ ገለፀዋል።

አሁን የምናከብረው የጨምበላላ በዓል በጨምላላን እንኑር በሚል መሪ ቃል እንደመንግስት እየተከበረ መሆኑንም ገልፀዋል።