Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች 'በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ' ናቸው - | Natnael Mekonnen

በመዲናዋ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ" ናቸው - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው #ከአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች "በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት የሚያሟሉ ባለመሆናቸው" ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው፤ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ የማይቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከቀናት በፊት ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ የመልሶ ግንባታና ኮሪደር ልማት የቅርስ መስፈርት የማያሟሉ ቤቶችንና አካባቢዎችን በመልሶ ማልማት የቀደመ ስያሜና አገልግሎታቸው እንዲቀጥል እንደሚደረግ ማስታወቁን ፕሬስ ድርጅት መዘገቡ ይታወሳል።

ቤቶቹን በቅርስነት ለመመዝገብ ያላቸው ታሪክ፣ አሁን ያሉበት ውጫዊ እና ውስጣዊ ገፅታ፣ እድሜያቸው፣ አርክቴክቸርን ጨምሮ በርካታ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ገልጸዋል። በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጣ በቅርስነት እንደሚመዘገብ እና በአንጻሩ ከ50 በታች የሆነ ቤት ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ እንደማይችል ጠቁመዋል። ለየሀገር ከፍተኛ ትርጉም ያላቸውን ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ተገልጿል።