Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጂንካ ኤርፖርት ያስገነባውን ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ እያስመረቀ | Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጂንካ ኤርፖርት ያስገነባውን ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ እያስመረቀ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጂንካ ኤርፖርት ያስገነባውን ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ/ተርሚናል/ እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲና የአሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

እንዲሁም የአሪ ዞን የአገር ሽማግሌዎች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና የሀይማኖት አባቶችም በስነ-ስርዓቱ ላይ ታድመዋል።