Get Mystery Box with random crypto!

የመጨረሻውን የናፍጣ ተሽከርካሪ ሠራ የሃገራችን መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ኢትዮጵያ እን | Natnael Mekonnen

የመጨረሻውን የናፍጣ ተሽከርካሪ ሠራ የሃገራችን መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ አዲስ ህግ እንደሚያወጣ ሲነገር ብዙ ጫጫታዎች ነበሩ እንግዲህ አለም በአሁን ሰአት ምን ያህል በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት እያቆመ ወደ ኤሌትሪክ መኪኖች ፊቱን ማዞሩን እየሰማን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው::

ቮልቮ የተሰኘው የመኪና አምራች ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት አቆመ።

ቮልቮ ዋና ቢሮውን ጎተንበርግ ስዊድን ያደረገ የዓለማችን መኪና አምራች ኩባንያ ነው

ዋና መቀመጫውን ጉተንበርግ ስዊድን በማድረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል ቮልቮ ኩባንያ፡፡

ኩባንያው የመጨረሻዬ ናት ያላትን በነዳጅ የምትሰራ ተሽከርካሪ ምርትን ለገበያ ያስተዋወቀ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በቀጣይም ሙሉ ትኩረቱን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማምረት ላይ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በ2030 በአህጉሪቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ለሙሉ የማገድ እቅድ እንዳለው ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች ትኩረታቸውን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ ላይ መሆናቸው አልአይን በዘገባው አመልክቷል።