Get Mystery Box with random crypto!

' ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው ' - የአርባ ምንጭ ከተማ | Natnael Mekonnen

" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል ።
የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት ያላቸዉን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ብሏል።
የአለልኝ አዘነ ህይዎት መቀጠፍ ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮችን ለማወቅ የስልክ ልውውጦችን ከመመርመር በተጨማሪ በዙሪያው የነበሩ አካላትንም በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ፖሊስ ገልጿል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ እነማን ተያዙ ? የምርመራዉ አካሄድስ ምን ይመስላል ? በሚል ለአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የለሆኑት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ጥያቄ ቀርቧል።
" የተጫዋቹ መሞት በተሰማበት ወቅት አጠራጣሪ ጉዳዮች ስለነበሩ ፖሊስ የምርመራ እንቅስቃሴ ጀምሯል " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም " በዚህ ወቅት ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " ብለዋል።
በሶሻል ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለዉን የእናቱ እና ባለቤቱ መያዝ በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ " አሁን ላይ ከእህት እና ወንድሙ ዉጭ የተያዘ አካል የለም በማለት ወደፊት ግን ከተያዙት የሚለቀቅ ካልተያዙት ደግሞ የሚያዝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።
" አሁን ላይ ምርመራዉን በፍጥነትና በጥንቃቄ እያካሄድን ነው " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ውጤቱን ለመላ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማድረስ ማሰባቸዉን ጠቁመዋል።