Get Mystery Box with random crypto!

እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ። በ | Natnael Mekonnen

እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ።

በየጊዜው እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ሰለባ ላለመሆን ዜጎች ማንነታቸው ከማይታወቁ ግለሰቦች ጋር በበይነመረብ በሚደረጉት ግንኙነት ላይ ጥንቃቄ እንዲወስዱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥምር ግብረ- ኃይል አሳስቧል።

የማጭበርበር ወንጀሎቹ በዋናነት የሚፈጸሙት በውጭ ሀገር የሚኖሩ፣ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በስፋት የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ ኢ-ሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራም፣ ኢንስታግራም፣ ኢሞና ቫይበርን በመጥለፍና ወዳጅ መስሎ በመቅረብ ወንጀሎቹ እንደሚፈጸሙ ከተደረገው ክትትል ማወቅ እንደተቻለም ተገልጿል።

ግለሰቦቹ የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን ተጠቅመዉ ወንጀሉን እንደሚፈጽሙ የተገለጸ ሲሆን በተለይ ዉድ እቃዎችን በማስመሰል እቃው ለተላከበት ክፍያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ገቢ እንዲያደርጉ አድርገው የገባዉን ገንዘብ ወዲያውኑ ወጪ በማድረግ ወንጀሉን ይፈጽሙታል ብሏል መግለጫው፡፡

በዚህ የማጭበርበር ድርጊቶች ላይ የተሰማሩት ግለሰቦች በተጨማሪም ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ማተም፤ ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መገልገል እንዲሁም የአደንዛዥ እፅ ዝዉዉር ወንጀል ጭምር ላይ ተሳታፊ ሆነዉ ተገኝተዋል ተብሏል።

በተደረገው ክትትል የውጭ አገር ዜጎች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ተጣርቶባቸዉ በማረሚያ ቤት የሚገኙ፤ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ እና ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኙም እንዳሉ ተጠቅሷል፡፡

ሙሉ መግለጫው https://telegra.ph/ETH-05-14