Get Mystery Box with random crypto!

ቱርክ ፤ የፊንላንድ እና ስውዲን NATOን መቀላቀል እንደማትደግፍ አስታወቀች። የቱርክ ፕሬዜዳንት | Natnael Mekonnen

ቱርክ ፤ የፊንላንድ እና ስውዲን NATOን መቀላቀል እንደማትደግፍ አስታወቀች።

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፤ ሀገራቸው ስዊድን እና ፊንላንድን NATOን በአባልነት የመቀላቀል እቅድ እንደማትደግፍ ገልፀዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ በግልፅ ባያብራሩም የኖርዲክ ሀገራት የብዙ አሸባሪ ድርጅቶች መገኛ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ አንካራ ውስጥ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ኤርዶጋን ፥ " ስዊድን እና ፊንላንድን በሚመለከት ያለውን ሂደት እየተከታተልን ነው ፤ ነገር ግን በጉዳዩ ላይ አዎንታዊ አመለካከት የለንም " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም NATO ግሪክን በአባልነት መቀበሉ ስህተት ነበር ሲሉም ተደምጠዋል። " እንደ ቱርክ ተመሳሳይ ስህተቶችን መድገም አንፈልግም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝርዝር ባያብራሩም " የስካንዲኔቪያ አገሮች የአሸባሪ ድርጅቶች ማረፊያ ናቸው " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ፤ " እንደውም በአንዳንድ ሀገራት የፓርላማ አባላት ናቸው ፤ እኛ ደጋፊ መሆን አንችልም (NATOን የመቀላቀል ጉዳይ) " ብለዋል።

ቱርክ ስውዲንን እና ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ ሀገራትን አሸባሪ ስትል የፈረጀቻቸውን እንደ ኩርዲሽ ሚሊሻ ቡድን PKK እና YPG ፤ እንዲሁም በአሜሪካ መቀመጫቸውን ያደረጉትን የፈቱላህ ጉለንን ተከታዮች ይደግፋሉ/ያስተናግዳሉ ስትል በተደጋጋሚ ስትወቅስ ይደመጣል።

አንካራ ጉሌኒስቶች እ.ኤ.አ. በ2016 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል ስትል የምትከስ ሲሆን ጉለን እና ደጋፊዎቹ ክሱን አይቀበሉትም።