Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ ከ200 በላይ የህንፃ ስር ፓርኪን አገልግሎ | Natnael Mekonnen

#AddisAbaba

የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ ከ200 በላይ የህንፃ ስር ፓርኪን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ፍተሻ ተካሄደ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህንፃ ስር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋለቸውን ለመለየት በ214 ህንጻዎች ላይ ፍተሻ አድርጓል።

በተካሄደው ፍተሻ ከ214 ህንፃዎች ውስጥ ፦

86 (40.2%) የህንፃ ስር ፓርኪንግ አገልግሎት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋላቸው ተረጋግጧል።

74 (34.6) ህንፃዎች ከታለመለት ዓለማ ውጭ በከፊል ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋላቸው ተረጋግጧል።

54ቱ (25.2%) ህንፃዎች ለምን አላማ እንዳዋሉ ማወቅ አልተቻለም ተብሏል።

የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታውን በከፊል ለሌላ አገልግሎት የቀየሩት ፦

ለውኃ ታንከርና ጀነሬተር ማስቀመጫ፣
ለእቃ ማከማቻ፣
ለቢሮ አገልግሎት፣
ለንግድ ስራ፣
ለቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ተረፈ ምርት ማከማቻ እና ለሌሎች ያልታወቁ አገልግሎት የዋሉ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በ11ዱም ክ/ ከተማዎች የህንፃ ስር ፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ተቋማት ላ እርምጃ ለመውሰድ ኤጀንሲው እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።