Get Mystery Box with random crypto!

🌼ናታኒም ቲዩብ🌼

የቴሌግራም ቻናል አርማ natanimtube — 🌼ናታኒም ቲዩብ🌼
የቴሌግራም ቻናል አርማ natanimtube — 🌼ናታኒም ቲዩብ🌼
የሰርጥ አድራሻ: @natanimtube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19
የሰርጥ መግለጫ

✝❤️የምትወዱት እና የናንተው የሆነው ናታኒም ቲዩብ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ሁላችሁም የግዚአብሔር ሰላም ከሁላችውም ጋር ይውን‼️ የyoutube ቻናላችን
SUBSCRIBE አድርጉን።
SUBSCRIBE
ለማድረግ ኦርቶዶክሳዊ አስ ሳሰብ ብቻ በቂ ነው።
👇👇👇
https://youtu.be/2JQS3iytxUQ
https://youtu.be/2JQS3iytxUQ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-07-08 06:55:20
ምልዕተ ፀጋ
ክብረ ቅዱሳን ንፅሕት ነሽ 2
የአምላክ እናት ኪዳነ ምሕረት ደስ ይበልሽ

አዝ

አባሕርያቆስ በመንፊስ ቅዱስ እየተቃኘ
ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ አፈለቀ አለ
ያንቺን ምስጋና በማብዛት ሳይሆን እያሳጠረ (2)
ስለዚህ ድንግል ከፋ ከፋ አርገን እንወድሻለን
ስለ ወለድሽው ያለሙን ንጉስ መዳሐኒአለምን
አስገኝተሻል የሚበላውን የሚጠጣውን2

አዝ
ሰማይ ብርሀና ወንዞች ቀለማት ሆነው፡ቢሰሩ
ፀጋ ክብርሽን እንፃፈው ቢሉ መች ይበቃሉ
እንደሐዋርያት ዕፁብ ድንቅነሽ ብለው ያርፋሉ 2
እንቺ ሙሽራ እመ ክርስቶስ ምስራቀ ፀሐይ
ፀጋሽ ይድረሰኝ መሻቴን ሙይው ፅድቁንም እንዳይ
ነይ ከልጅሽ ጋር ኪዳነ ምሕረት የነብሴ ሲሳይ 2

አዝ
ስምሽ ስንቅ ነው ለተሰደዱት ለባዘኑት
ግርማ ሞገስነሽ በባዕድ ሀገር ለባዘኑት
ከአይን ጥቅሻ ስለ ፈጠነ የምልጃሽ ሙላት 2
ማርያም ውድስት በአፈ መላእክት ወአፈ ሰብ
እንደ ማር ወለላ የምስጋናሽ ጣም ጣፋጭ ሚበላ
ኪዳነ ምሕረት ሆንሻት ለነብሴ ጥላ ከለላ 2

ዘማሪ ዲያቆን ፋፁም ከበደ
የተዋህዶ ልጆች ሼር ሰብስክራብ እናድርግ !









14.3K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 05:23:58 ዓለምን አትውደዱ

ክፍል ፫

ቅዲሳን ሰዎች ዓለም በሕግ እያሳበበ ፈተናን ከሚያመጣባቸው በቀር ከሕግ ጋር አይተዋወቁም፤ ሕግም ከቅዱሳን ጋር የሚተዋወቅበት ምክንያት የለውም።

ቅዱሳን ከዓለም ቢሆኑ ዓለም ያውቃቸው ነበር፤ ነገር ግን ከዓለም አይደሉምና ዓለም አያውቃቸውም፤ ከሕግ ጋር ጭቅጭቅ የለባቸውም፤ ሆኖም ሕግ በቅዱሳን ዘንድ ብቻ የተፈጸመ ሆኖ ይገኛል። ይህንም ስንል ቅዱሳን ዓለማዊ ሕግን ስለጠበቁ አይደለም፤ በመንፈሳዊ ሕግ ስለ ተከተሉ ነው፤ ሥራቸው ዓለማዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ስለሆነ ነው ።

ቅዱሳን ከፈጣሪያቸው የተቀበሉት ትእዛዝ ጠቃሚና የማይለወጥ ሲሆን ዓለማዊ ሕግ ተለዋዋጭ ነው፤ ያለፈው ዓለም የደነገውን ሕግ ሌላው መጪው ዓለም ያፈርሰዋል፤ የሌላው ምብትና ነፃነት በሌላው ዘንድ አፈጸምም።

ሕግ በዓለም ተፈጻሚነት ያጣ ስለሆነ ዓለም በየጊዜው ቀውጢ እየተፈጠረበት ይኖራል።
ከሕግ ፍርድም አያመልጥም።
ይህ ዓለም ከእግዚአብሓር ፀጋ ጋር ለሥራ ስለማይነሣና ራሱ ስለማይፈጽመው ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ከስልጣኔው ይልቅ ጒስቁልናው ሲያመዝን ይታያል።

ጦርነት፤ የጦርነት ወሬ፤ መለያየት፤ በሽታና ረሐብ፤ ድንቁርና፤ ድርቅ፤ የውሃ መጥለቅለቅ፤ ከድህነትና መናፍቅነት፤ የመሬት መደርመስና የውሸት ፖለቲካ ሲፈራረቁበት፤ በሚታደስበት ጊዜ አርጅቶና ተጎሳቅሎ የሚገኝ ነው (ማቲ.24፤ 3-8) ግዛቱ የባሕርዩ ማለትም ከሰዎች ጋር የሚቃወስ፤ የዚህ ዓለም አበጋዝ የሆነው የሰይጣን ዲያቢሎስ ስለሆነ ዓለም እጅግ በጣም ጎስቋላ ነገር ነው (ራዕ.13፤7-10)

ዓለም የስልጣኔው ውጤት እግዚአብሔርን እያመለከበት የሚያስፋፋ ቢሆን ኖሮ ሰላም ገንዘቡ ነበር።
ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ጸጋ በመቀበል በፊቱ ያለውን ሕግ እየፈጸመ በሰላም የመኖር ባሕርይ ስለሌለው ለእልፈት የተወሰነ ሆነ (1ኛዮሐ.2፤17) ሕግ ቅንና ሚዛናዊ ቢሆንም በቅንነት ያልተያዘና መንፈሳዊ ህይወትን ያልተለበሰ ፊደል ብቻ ሆኖ የቀረ ስለሆነ የራሱን ፍርድ ከሚያመቻች በቀር በዓለም ዘንድ ተፈጻሚነት አልተመቻቸለትም፤ ፍቅር ፤ ሰላም ፤ አንድነት ፤ በረከት ፤ ረድኤት አልተገኘበትም ፤ ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ተገዢ በመሆን አልዳነም፤ ስለሆነም ዓለም ከሕግ ፍርድ አያመልጥም።

ዓለም በፍርድ ውሳኔ እየተጎሳቆለ ከሚኖር በቀር ሰላም ከማይሰፍንበት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊና የመንፈሳዊያን ሰዎች የሥራ ኃላፊነት የሚጠናከርበት ዋና ምክንያት ነው።

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ "ወንድሞች ሆይ ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ሁሉ አትውደዱ ዓለምን የሚወድ እግዚአብሔርን አይወድም።

የሥጋ ምኞት የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብ መመካት ከዓለም እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለምና ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል" ይላል (1ኛዮሐ.2፤15-17) ዓለምን አትውደዱ
ወይም በዓለም ያለውን የሚለውን ቃል የምንማረው ዓለም ሕግን የማይፈጽም ስለሆነና በሕግ የሚፈርድበትን ስለሆነ በሕግ እዳይፈረድብን ነው።

ይቀጥላል.......

አቅራቢ ናታኒም ቲዩብ

"ትምህርቱ ለሌሎች ይድረስ የተዋህዶ ልጆች"

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
8.0K views02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ