Get Mystery Box with random crypto!

🌼ናታኒም ቲዩብ🌼

የቴሌግራም ቻናል አርማ natanimtube — 🌼ናታኒም ቲዩብ🌼
የቴሌግራም ቻናል አርማ natanimtube — 🌼ናታኒም ቲዩብ🌼
የሰርጥ አድራሻ: @natanimtube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19
የሰርጥ መግለጫ

✝❤️የምትወዱት እና የናንተው የሆነው ናታኒም ቲዩብ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ሁላችሁም የግዚአብሔር ሰላም ከሁላችውም ጋር ይውን‼️ የyoutube ቻናላችን
SUBSCRIBE አድርጉን።
SUBSCRIBE
ለማድረግ ኦርቶዶክሳዊ አስ ሳሰብ ብቻ በቂ ነው።
👇👇👇
https://youtu.be/2JQS3iytxUQ
https://youtu.be/2JQS3iytxUQ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-04 09:05:08 የተዋህዶ ልጆች
#አዳዲስ እና ወቅታዊ መዝሙሮች በማቅረብ የሚታወቀው ናታኒም ቲዩብ
#አዲስ ወቅታዊ የንስሃ ዝማሬ ይዞላቹሁ ቀርቦዋል።
"ተዋሕዶ"በዘማሪ ዲ/ን ደምስ ዘበርጋ ዝማሬውን ለማግኘት እንዲሁም subscribe ለማድረግ ከስር የተቀመጠውን ሊንክ ይጠቀሙ ቤተሰብ ይሁኑ።






1.5K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:44:39

1.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 09:20:35
የጽሞና ጊዜ አለህ??

ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች ብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፈት ብቻውን ከዓምላኩ ጋር በበርሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራዕይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚህን ሁሉ ሰማያዊ ሚስጥራት የተመለከተው ብቻውን በፍጥሞ ደሴት ሆኖ ነው ። ስሙን በአሕዛብ ፣ በነገስታቱና በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፈት ይሸከም የተመረጠው ቅዱስ ጳውሎስ ፣ ከሁሉ አሰቀድሞ ግን የመረጠው አምላኩ መንፈሳዊውን ሐይል ያስታጥቀው ዘንድ የገዛ ድክመቶቹን ተሸክሞ ብቻውን ወደ አረብ በረሃ ገስግሶ ነበር ።

አንተስ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በመንፈስ የምትጎለምስበት በረሃህ ፣ እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣዕመ መንግሰተ ሰማያትን የምትዘክርበት ፍጥሞ ደሴትህ ፣ እንደ ሐዋርያዊ ጳውሎስ በነፍስ ታድሰህ  የምትወጣበት አረባዊ ገዳምህ የት ነው ? መቼ መቼሳ ወደዚያ ትወርዳለህ ??

          ቃሉን በልቦናችን ያሳድርብን !!!!!

ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ
    
   SHARE SHARE SHARE


https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
1.4K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 13:12:30

271 views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:32:58 መጽሐፈ ሄኖክ
287 views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:28:13 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
ዘማሪት አቦነሽ እዲውም
እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎች መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት



◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◥
➣ ➤ JOIN US
█◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢
784 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:28:30 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






2.5K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:13:52 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






1.6K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:06:59
የክርስትና መሰረት  ዘውግ አይደለም *


በጎሳ (ዘውግ) አንድነት ላይ የተመሰረተ እና ይህን ተጠቅመው በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን የሚሰሩ ሰዎች የሚመሩት ሃይማኖትም ብዙ ተከታይ ሊኖሩት ይችላል ። ክርስትና በምድር ሁሉ የተበተኑ ፣ ከሁሉም ዘውጎች የተሰበሰቡ ፣ ምድራዊ ክብርን እና የበላይነትን የማይፈልጉ ፣ ለመግደል ሳይሆን የክርስቶስ ምስክሮች ሆነው ለመሞት እንደ በግ በተኩላዎች መካከል የተላኩ ሰዎች የሰበኩት ሃይማኖት በመሆኑ የዘውግ አንድነት እና የኃይል የበላይነት ከክርስትና አመሰራረት እና እሳቤ ጋር አይሄድም ። ክርስትና በምድራዊ ኃይል እና ስልጣን በሌሎች ላይ የበላይ መሆን መፈለግን ስለሚከለክል የዘውግ እና የኃይል አንድነት የክርስትና  ማኅበር ለመቀላቀል ጥሩ ምክንያት አይደለም ።

(የልቦና ችሎት በረከት አዝመራው )


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

JOINE JOINE


https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
https://t.me/natanimtube
1.5K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:21:24 + ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም:: የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም


JOINE JOINE


https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
https://t.me/zdfitsumkebe
1.4K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ