Get Mystery Box with random crypto!

بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العاملين الصلاة والسلام عل | Muslims Ummah 🌍

بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله رب العاملين الصلاة والسلام على ءشرف الأنبياء والمرسلين نبينا محمد صلى الله عليه وسلم السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ለዚህ ቀን ላደረሰን አላህ ምስጋና ይገባው። በመጀመሪያ እስልምና ምንድነው ከሚለው እንጀምር።
እስልምና ምንድነው???
ሸሀደቱ አንላ ኢላሀ ኢለላህ
ወሸሀደቱ አነ ሙሀመዱን ረሱሉላህ ሰ.ዐ.ወ
የኢስላም መሰረቶች 5 ናቸው።እነሡም
ሸሀደቱ አንላ ኢላሀ ኢለላህ
ወሸሀደቱ አነ ሙሀመድ ረሱሉላህ
ኢቃሙ ሰላ የ5 ወቅት
ሰላቶችን በአግባቡ መስገድ
ኢታኡል ዘካ በአመት አንዴ
ዘካ ማውጣት
ወሰውሙ ረመዳን በአመት
አንድ ወር ረመዳንን መፆም
ወሀጁል በይቲ መኒስተታዐ
ዐለይሂ ሠቢላ የአሏህን
ቤት(ካዕባ) በህይወት ዘመን
አንዴ ሀጅ ማድረግ ግዴታ ነው።
የኢማን መሰረቶች ደግሞ 6 ናቸው ።
አን ቱዕሚነ ቢላህ በአሏህ
ማመን
ወመላኢከቲሂ አሏህ በቁጥር
የማይገመቱ ብዙ መላኢኮች
እንዳሉት ማመን
ወኩቱቢሂ ብዙ ኪታቦች
እንዳሉት ማመን
ወሩሱሊሂ አሏህ ብዙ
መልዕክተኞች እንዳሉት ማመን
ከነዚህም 25 ዋና ዋናዎቹን መያዝ አለብን።
ወቢል የውሚል አኺሪ
በመጨረሻው ቀን ማመን
ወቢል ቀደሪ ኸይሪሂ ወሸሪሂ
ኩሉን ሚነሏሂ ተዓላ በፍርድ ማመን ጥሩውም
መጥፎውም ከአሏህ ነው ብሎ ማመን
ቤት ያለ ምሰሶ እንደማይቆመው እስልምና እነዚህ የእስላም እና የኢማን መሰረቶች ባይኖሩ እስልምና መቆም አይችልም ነበር ።
የዛሬው ትምህርታችን ይህን ይመስላል።
ወሠላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ።

..
@Muslims_Ummahh