Get Mystery Box with random crypto!

የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ 1) #ብልጫ አለው! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ | Muslims Ummah 🌍

የቀኑ 3ቱ ሐዲሶች
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

1) #ብልጫ አለው!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿صلاةٌ في المسجدِ الحرامِ أفضلُ من مائةِ ألفِ صلاةٍ فيما سِواهُ﴾
“በመስጂደል ሀረም የሚሰገድ ሰላት ሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሰላት በመቶ ሺህ የሚበልጥ ብልጫ አለው።”
ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1163

2) #ከኛ አይደለም!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَنْ أَفْسَدَ امرأةً على زَوْجِها فَليسَ مِنّا﴾
“ሴትን ልጅ በባሏ ላይ እንድትበላሽ ያደረገ ከኛ አይደለም።”
ምንጭ፦ ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 324

3)#ለደረቀ ልብ ፍቱን መድኃኒት!
ከአቡ ሁረይራ ( رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  አንድ ሰው ወደ ረሱል (ﷺ) በመምጣት ቀልቡ እንደደረቀ ስሞታ አቀረበላቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉት፦
﴿إنْ أردتَ أنْ يَلينَ قلبُكَ، فأطعِمْ المسكينَ، وامسحْ رأسَ اليتيمِ﴾
“ቀልብህ እንዲለሰልስ ከፈለክ ምስኪኖችን ምግብ መግብ። የየቲሞችን (አባት የሌላቸውን ልጆች) እራስ ዳብስ።”
ምንጭ፦ ሶሂህ አልጃሚዕ: 1410



ሼር አድርጉት።
||
ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ

.. @Muslims_Ummahh