Get Mystery Box with random crypto!

️🌙ኢስላም የሰላም መንገድ🌙️

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimnegnenesul — ️🌙ኢስላም የሰላም መንገድ🌙️
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimnegnenesul — ️🌙ኢስላም የሰላም መንገድ🌙️
የሰርጥ አድራሻ: @muslimnegnenesul
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 396
የሰርጥ መግለጫ

🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌
ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሰራ
<<እኔ ከሙስሊሞች ነኝ>>
ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?
አል–ፉሲለት ምዕ41:33
t.me/MuslimNegnEneSul
t.me/MuslimNegnEneSul
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 00:43:17
9 views21:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 23:37:41 ከአቢ-ቀታዳ አል-አንሷሪ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው
#ነቢዩ_ሶለላሁ_ዐለይሂ_ወሰለም_እንዲህ_አሉ:-
የዐረፋን ቀን መጾም ከሱ በፊት (ያለፈውን) አመት እና ከሱ ቡሃላ (የሚቀጥለውን) አመት ወንጀል ያስሰርዛል ብዬ ከአሏህ እከጅላለሁ።
ሙስሊም ዘግበውታል


#የአረፋ_ቀን_የፊታችን_ጁመዓ_በ01/11/2012 ( #ዙል_ሂጃ_9_ይውላል።

#የውሙ_ነህር_የእርድ_ቀን_ዒዱል_አረፋ_ቅዳሜ_በ02/11/2012 ( #ዙል_ሂጃ_10__ይውላል።
34 views20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:52:01 #መቻኮል_የሸይጧን_ነው
#በ❺ ነገር ሲቀር!!
<-------------------------------------------------->
● العجلـة مـن الشيطـان إلا فـي خمـس
١) إطعـام الضيـف.
٢) تجهيـز الميـت.
٣) تزويـج البكـر.
٤) قضـاء الديـن.
٥) التوبـة مـن الذنـب.
❶ እንግዳን መመገብ
❷ መይትን ማቻኮል
❸ ቢክራንማግባት!!
❹ እዳን መክፈል
❺ ከወንጀል መመለስ እነዚህ ላይ ተቻኮሉ።
43 viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:40:48 #ቁርስ ቁርስ #ቁርስ ቁርስ

#አዳራችሁ_እንዴት_ነበር ?

የሰው ምርጡ ሰው #ሦስት ባህሪዎች አሉት ይላል አንድ ጠቢብ

① #ድህነቱን_ይደብቃል
ሰዎችም ስላለው ነው ዝም ያለው ብለው ያስቡታል

② #ቁጣዉን_ይቆጣጠራል
ሰዎች ተስማምቶ ነው ተቀብሎ ነው ብለው ይገምቱታል

③ #መታመሙን_ይደብቃል
ሰዎች ተመችቶታል ድሎት ዉስጥ ነው ብለው ያስወሩበታል

#ለዱንያ_አትስገብገቡ፤
#ለሷ_አትንበርከኩ፤
#ለሷ_ቀልባችሁን_አትስጡ
#አላህ_ይወዳችኋል

#የሰው_እጅ_አትዩ
#ከሰው_ቤት_ያለዉን_አትመኙ
#በአላህ_ክፍፍል_አመስግኑ_ሰዎች_ያከብሯችኋል

#ሪዝቃችሁ_ሰፍቶ_ምኞታችሁ_ሰምሮ_የምትዉሉበት_ቀን_ይሁን

ፀሐፊ MuhammedSeidABX
363 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 09:51:42 "አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦

"ሃይማኖት ገር ነው።
ሃይማኖት (ያለአግባብ) እንዲጠብቅ አይደረግም፣ (አጥባቂውን) ያሸነፈ ቢሆን እንጂ! መካከለኛና ሚዛናዊ ሁኑ፣

(ሃይማኖታዊ ክንውኖችን) በተሟላ መልኩ መፈፀም ባትችሉም ወደ ፍፁምነት የተቃረበውን ለመስራት ጥረት አድርጉ፣ ብስራት ለእናንተው ይሁን፣ በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ፣ ከለሊቱ
መቋጫም ጥቂትን በመጠቀም ታገዙ።"

(ቡኻሪ እንደዘገቡት)"
==========================================
ይህን ሐዲስ ያገኙውት ከ ኢትዮ ቢላል ሃዲስ አፕ ነዉ ።
50 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 11:46:59
#ቁርዓንን_አያስተነትኑምን?
#ከአላህ_ሌላ_ዘንድ_በነበረ_ኖሮ_በርሱ_ውስጥ_ብዙን_መለያየት_ባገኙ_ነበረ።
353 views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:00:33 የጁሙዐ ቀን ሱናዎች

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3- ሸዋር መውሰድ

4- ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5- ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6- ሽቶ መቀባት (ለወንዶች )

7- ወደ መስጂድ በግዜ መሄድ

8- ወደ አቅራቢያ መስጅድ በግር መሄድ የተወደደ ነው

9- ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ
.
.
.

365 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 07:09:31
58 views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 07:22:32 ኡድሂያ ለማረድ ካቀዱ ከወዲሁ ጥፍርና ጸጉርዎን ከመቁረጥ ይቆጠቡ!
-------------------
☞ እንድ ሙስሊም ሀጅ የማያደርግ ከሆነና በዒድ አል አድሀ እለት ኡድሂያን ለማረድ ካሰበ የዙልሂጃ ወር ከገባበት የመጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም፤ ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህም ተከታዩን የኡሙሰለማ ሀዲስ መሰረት ያደረገ ነው።

عن أم سلمة رضي الله عنها أن النبي صلى الله عليه وسلّم قال : " إذا رأيتم هلال ذي الحجة ، وفي لفظ : "إذا دخلت العشر وأراد أحدكم أن يضحي فليمسك عن شعره وأظفاره ". رواه أحمد ومسلم ، وفي لفظ : " فلا يأخذ من شعره وأظفاره شيئاً حتى يضحي ". وفي لفظ : "فلا يمس من شعره ولا بشره شيئاً ".

ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያ ለማረድን ካቀደ፤ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል። በሌላም ዘገባም «ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። እንደዚሁ፤ «ከሰውነቱ ቆዳ ወይም ከፀጉሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል።

#ይህ_ማንኛውም_ሙስሊም_እራሱን_በሀጅ_ላይ_ካሉ_ሰዎች_ጋር_የሚያመሳስልበት_እና_የተወሰኑ_የኢህራም_ክልከላዎችን_ከነሱ_ጋር_የሚጋራበት_ዲናዊ_ስርአትና_ነብያዊ_ትዕዛዝ_ነው

☞ ጸጉርንና ጥፍርን ከመቁረጥ የሚከለከለው ለራሱ ወይም ለሰው በራሱ ገንዘብ የሚያርድ ሰው ብቻ ነው። ህጉ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው ሲባል፤ በወኪልነት ለሌላ ስው የሚያርድን ሰው አይጨምርም።

☞ እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም ማካካሻ ከፋራም የለበትም። አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን ወንጀሉን ቢፈፅምም ኡድሂያ ማረዱን መተው የለበትም።

☞ በስህተት ወይም በመርሳት ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰው ምንም ወንጀል የለበትም። በተመሳሳይ መልኩ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ቢቆርጥ ችግር የለውም። ለምሳሌ የተጎዳን የሰውነት ቆዳ ለማከም ወይም የተሰበረ ጥፍሩን ለማስተካከል መቁረጥ ይፈቀድለታል።

፠ ስለ ኡድሂያ ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች

1 - በዙልሂጃ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ አንዱ ነው።

2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፤

{ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37

አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» አል ሐጅ 37

4- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

5- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

6- ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

7- የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ ወይም የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

8- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋራትም ይቻላል።

9- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

10- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ ሶስት ቦታ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።
463 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 09:28:55ህመምና መከራ ሲመጣበት ጌታዬ ሆይ ብሎ ተጣራ
ልጅ ሲያጣና ብቸኝነት ሲሰማው ጌታዬ ሆይ ብሎ ተጣራ
ችግርና ጭንቀት ሲደርስበት ጌታዬ ሆይ ብሎ ተጣራ
☞ አላህም አላዋረዳቸውም ዱዓቸውን ተቀበለ ፍላጎታቸውንም አሟላላቸው, ካሉበት ችግርም አወጣቸው።

(وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنْتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ)
"አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ
አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ »
ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡"

[አንቢያእ 83]


(وَزَكَرِيَّا إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنْتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ)
"ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ
አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል»
ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡"

[አንቢያእ 89]


(وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِنْ قَبْلُ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ)
"ኑሕንም ከዚያ በፊት (ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)
ለእርሱም (ጥሪውን) ተቀበልነው
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን፡፡"

[አንቢያእ 76]

#አንተም_ሙሲባዎች_ሲደርሱብህ_ሰውን_ወደ_ጎን_ትተህ_እጆችህን_አንሳና_ጌታዬ_ሆይ_ብለህ_ተጣራ_አዛኙ_ሩህሩሁና_ቸሩ_አላህ_አያዋርድህም
113 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ