Get Mystery Box with random crypto!

ኢሽተቅና ልዩ የመድረክ ፕሮግራም የፊታችን እሁድ ጥር 29 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በሰፊው ሙሉዓለም | MUSLIM COUPLES

ኢሽተቅና ልዩ የመድረክ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ ጥር 29 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በሰፊው ሙሉዓለም አዳራሽ ለእይታ ይበቃል። (ኢንሻአላህ)

በፕሮግራሙ ላይ
የመንዙማው ንጉስ ክቡር ዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ በመረዋ ድምፃቸው የዐለማትን እዝነት ያወዳድሳሉ ያሞጋግሳሉ።

ሕፃናት በጣፋጭ አንደበታቸው ጥዑም ነሽዳዎችን ያቀርባሉ።

ትንታግ ዑለማዎቻችን በርቱዕ አንደበታቸው ኮርኳሪ ዳዕዋዎች ያደርጋሉ።

የተለያዩ ግጥሞች እና ጨዋታዎች በመድረኩ ፈርጥ ኡስታዝ ሷሊሕ አስታጥቄ መድረኩን ውብ ያደርጋሉ።

አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ሰዎች አዝናኝ፣ አስተማሪ እና አስቂኝ ተውኔቶችን ያሳያሉ።

ራምሳ እና ዒሽቅ ለመድሕ በተካኑ ማዲሖች ይታሸቃል።

ምን ይሄ ብቻ

ልዩ ልዩ ሰርፕራይዝ
ሽልማቶች
መነባንቦች
ወጎች
ኧረ ብዙ ብዙ

ታዳሚዎቻችን ሊያስደስቱ የሚችሉ ፕሮግራሞችን ደግሰን ፣ ቀምመንና መጥነን እንጠብቅዎታለን።

ቲኬቶችን በሁሉም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፎች እና በየሰፈሩ በወከልናቸው ወኪሎቻችን ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ 0918399260 ይደዉሉ።
ያስታውሱ 6 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

https://t.me/mehdi_multimedia