Get Mystery Box with random crypto!

«ለዒድ የሥጋ ስጦታ ለወገኖቻችን» ሚያዝያ 22/2014 ዓ/ል ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የ | ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር

«ለዒድ የሥጋ ስጦታ ለወገኖቻችን»

ሚያዝያ 22/2014 ዓ/ል

ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር ለ1443 ሂጅሪያ ዒደል ፊጥር በዓል ለ400 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ዒድን ከቤት ወጥተው የሰው ፊት ሳያዩ በቤታቸው በደስታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያሳልፉ ዘንድ በሶሻል ሚድያ ገንዘን በማሰባሰብ ወደ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ / ብር ገደማ ወጭ በማድረግ 4 ግመሎችን በመግዛት በዛሬው እለት በማረድ በከተማችን ከሁሉም ቀበሌ ለተውጣጡ ለ400 አቅመ ደካማ ወገኖች አበርክቷል።

ረመዷንን ከሚስኪኖች ጋር በሚል መሪ ቃል ለ400 አባወራዎች ከ1,000,000 /አንድ ሚሊየን/ ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለረመዷን የአንድ ወር አሰቤዛ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

ለፕሮጀክቱ መሳካት በገንዘብ፣ በጉልበት እና በዱዓ ከጎናችን ለነበራቹህ ሁሉ ምሰጋናችን ይድረሳቹህ ጀዛኩሙላሁ ኸይረል ጀዛ

ማህበሩ ለሚሰራቸው የተለያዮ የልማት ክንዉኖች በገንዘብ ለማገዝ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶች ይጠቀሙ ጀዛኩሙላሁ ኸይረል ጀዛ

♢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000388115444

♢ አዋሸ ባንክ 01425412116600

♢ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000085221616

♢ ኦሮሚያ ኢንተርናሺናል 1493281700001

የአካውንት ሰም ፦ ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር

ለማንኛውጥ ጥያቄና አሰተያየት ለማድረስ

+251949941451
+251936443838
+251965070705


ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር