Get Mystery Box with random crypto!

Motivational Speech & Truth

የቴሌግራም ቻናል አርማ motivational6 — Motivational Speech & Truth M
የቴሌግራም ቻናል አርማ motivational6 — Motivational Speech & Truth
የሰርጥ አድራሻ: @motivational6
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.31K
የሰርጥ መግለጫ

💎እኳን ወደቻናላችን በደህና መጡ
🌐ይህ ቻናል አናቃቄ ንግግሮችን ፣ ምስሎችን፣ቪዲዬወችን እና ጥቅሶችን
በአማርኛ እና በእግሊዘኛ ያቀርባል፡፡
🌐በተጨማሪም፦የተመረጡ ወቅታዊ እና አገብጋቢ የሆኑ እዉነታወችን በመምረጥ ያቀርባል
🔵 እረሶ ተጠቅመው ለወዳጅዎም Invite ማድረግዎን እንዳይረሱ!
👥 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ያሳዉቁን
👇👇
@Motiv2team
@motivational6

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-20 12:20:11 ለውብ ቀን

ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል!
ዴል ካርኒጌ

ፈገግታችን የስሜታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ በሰዎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖም አንዘንጋ፡፡
ብሩህ ፈገግታ፣ እወድሃለሁ፣ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል የሚሉትን ቃላት ይወክላል፡፡
እያሻሸነው ፍቅራችንን የምናሳየው ውሻችን ሳይቀር ከሩቅ ሲመለከተን ጭራውን እያወዛወዘ
የሚሆነውን የሚያሳጣው ለምን ይመስላችኋል?
የህፃን ፈገግታም ከልብ የመነጨ ስለሆን መሰል ተፅዕኖ አለው።
አዎ! በካርኒጌ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ ድርጊት ከቃላት የበለጠ ይናገራል።
---------------------------------------------

ሳቅና ፈገግታ ሰደቃ ነው ብለው
ነግረውኝ ሼሆቼ ስንቱን ቀን ሰደኩት
በውብ ሳቅ ሸኝቼ!!!

መልካም እለተ ሰኞ ተመኘሁ
@motivational6
4.1K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 15:13:53
የሚያመሰግን ሰው ትልቅ ሰው ነው::

ማመስገን ጥሩ ነገሮች እንዲበዙ ያደርጋል::
3.5K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:28:28
ወጥነት ( consistency)

ብርድ ነው ብለን እንቅልፍን አንመርጥም።ሠው አይኖርም ብለን ከመንገዳችን ወደኅላ አንልም።

ሁሌም ለአላማችን እንተጋለን። ለውጥ ሂደት ነው። ቀናት ፣ ወራት ፣ አመታትን ይፈልጋል። በዚህ ረጅም መንገድ ለመጓዝ የወጥነትን ባህሪ ( consistency) ማዳበር ይገባናል። በህይወታቸው የፈለጉትን ያገኙ ሠዎች ትልቁ ባህሪያቸው ወጥነት ነው። የትኛውም ሁኔታ ከሀሳባቸው እንዲያስቆማቸው አይፈቅዱም።

በየትኛውም የህይወት ክፍላችን ላይ ( በስራ ፣ በግንኙነት ፣ በመንፈሳዊነት ወዘተ) ወጥነትን ይኑረን። ያሰብነውን ውጤት እስክናገኝ ድረስ በመንገዱ ላይ እንቆይ። ወጥ እንሁን።
4.2K viewsedited  17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 18:19:38 አይምሯችን መሬት ነው፤ የተዘራበትን ማብቀል ነው ስራው።
መልካም ነገር ከነገርነው፣ መልካም ነገር ካየ የህይወት መንገዳችን ያማረና ደስተኛ እንሆናለን።

ለሆዳችን እኮ በጣም ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በፍፁም የቆሸሸ ምግብ አንበላም።
ታዲያ የነገ መድረሻችንን ለሚወስነው አይምሯችን ምንድነው የምንመግበው? መጥፎ ዜና ነው ወይስ መንፈሳዊ ሀሳብ? ስለ ሰው አሉባልታ ነው የምናስበው ወይስ ስለ ነገ መድረሻችን? ምርጫው የኛ ነው!

@motivational6
4.1K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 13:52:33 እንደ ፈጣሪ ያለ ማንም የለም! ለሱ ታመን፤ እሱ ካከበረህ ማንም ቢንቅህ ቢሰድብህ እንዳትደነግጥ! እንዳትከፋ! የምትኖርበት ቤት ያለ ግድግዳና ምሰሶ ይደረመሳል፤ ሰማይ ግን ምሰሶ የለውም፣ ግድግዳ የለውም ብቻውን ነው የቆመው! እሱን ብቻ ፍራ! ማንም አያቆምህም!

እምነት የሞላው ህይወት ተመኘውላችሁ

መልካም ሰንበት
4.6K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 18:50:17 Good night world

take time for reading a page before sleeping
4.3K viewsedited  15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 21:03:23 <<ዓለም ደስተኛ፣ ጤናማ እና የበለጠገ እንዲሆን ከፈለክ፣



ለዓለም አንድ ደስተኛ፣ጤናማ እና የበለጠገ ሰዉ - አንተን በማበርከት ጀምር>>


@motivational6
4.2K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 09:45:17 ብእሩ ያለው በእጅህ ነው!
በእጅህ ባለው ብእር ስትፈልግ የደስታና የሀሴት የምስጋና ቃላት ስትፈልግ የሀዘንና የሰቆቃ ቃላትን ልትጽፍበት ትችላለህ።
በያዝከው ብእር የነገን ማንነትህን ልትጽፍበትም ትችላለህ። የነገው ማንነትህ በብሩህ ተስፋ፣ በደስታና በስኬት የተሞላ ወይም በችግርና ባለመሳካት የሚገለጽ ሊሆን ይችላል።
ይሄ ሁሉ ግን የሚወሰነው በእጅህ ላይ ባለው ብእር ነው። አይገርምም ያ በወረቀት ያሰፈርነው መልካምም ይሁን መጥፎ ወደድንም ጠላንም በእውኑ አለም ይገለጣል (ህይወታችን ላይ ይፈፀማል )
ስለዚህ የምትጽፉትን በጥንቃቄ ምረጡ!
እንደ እኔ ከሆነ ምስጋና, ስኬትን ፃፉበት በምስጋና የተሞላ ህይወት ይኖራችኃል!

ሰናይ ቀን ይሁንልን!ብእሩ ያለው በእጅህ ነው!
በእጅህ ባለው ብእር ስትፈልግ የደስታና የሀሴት የምስጋና ቃላት ስትፈልግ የሀዘንና የሰቆቃ ቃላትን ልትጽፍበት ትችላለህ።
በያዝከው ብእር የነገን ማንነትህን ልትጽፍበትም ትችላለህ። የነገው ማንነትህ በብሩህ ተስፋ፣ በደስታና በስኬት የተሞላ ወይም በችግርና ባለመሳካት የሚገለጽ ሊሆን ይችላል።
ይሄ ሁሉ ግን የሚወሰነው በእጅህ ላይ ባለው ብእር ነው። አይገርምም ያ በወረቀት ያሰፈርነው መልካምም ይሁን መጥፎ ወደድንም ጠላንም በእውኑ አለም ይገለጣል (ህይወታችን ላይ ይፈፀማል )
ስለዚህ የምትጽፉትን በጥንቃቄ ምረጡ!
እንደ እኔ ከሆነ ምስጋና, ስኬትን ፃፉበት በምስጋና የተሞላ ህይወት ይኖራችኃል!

ሰናይ ቀን ይሁንልን!
4.3K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:12:59 ሙሉ ሰውነትህ ቢወፍር የተለመደ ነው፤ አንድ እጅህ ተነጥሎ ቢወፍር ግን እንግዳ ነገር ነው።
አየህ መዝናናትና ፈታ ማለት ላይ ምርጥ ሆነህ ነገር ግን ስራህ ላይ፣ መንፈሳዊ ህይወት ላይ፣ የቤተሰብ ወይ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፈዘዝክ ይሄን ምሳሌ አስታውስ።
ወዳጄ የሁሉንም ነገር ሚዛን ማስጠበቅ አለብህ።

የተባረከ እለተ ሰንበት ተመኘን
@motivational6
4.0K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 18:38:40 ራስህን ለመለወጥ ብትሞክርም ባትሞክርም ጊዜው እንደሆነ መሄዱ አይቀርም፤
ታዲያ ራስህ ላይ ሰርተህ የዛሬ አመት ቢመጣ አይሻልም?
ህይወትን በዘፈቀደ ሳይሆን በእቅድ ለመኖር ምርጫው ያንተ ነው!


መልካም ምሽት
@motivational6
4.4K viewsedited  15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ