Get Mystery Box with random crypto!

#የማውገዝ_ድንኳን_እድምተኞች ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬ ነገር የተረጋጋ ሲመስል ሰከን ብ | Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

#የማውገዝ_ድንኳን_እድምተኞች
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ነገር የተረጋጋ ሲመስል ሰከን ብለን ካወራናት መቼም እንደዚህ ድንኳን እድምተኞች አሳፋሪም፣ አሳዛኝም፣ ኮሚክም ነገር የለም። ደግሞም ድንኳኗ ብዙ ተራ ማጀቢያዎችና አጃቢዎች ይታደሙባታል።
"ለምን አታወግዝም?"
"ሰው ሲሞት አታዝንም ወይ?" ይሉሀል። አስተዛዛኝ መሆናቸው ነው። መፍትሄ ማንገባቸው ነው። የመጀመሪያው ድንቁርና ከዚህ ይጀምራል። እንኳን በግፍና በግፈኞች ለተገደለው ወገኔ ለየትኛው የሰው ልጅ ሞት መቅረብ የሌለበት ቆሻሻ ጥያቄ። የቀሽሞች መደበቂያ ናት። ገዳይና አስገዳይ፣ ደንቆሮና አዋቂ ተቀላቅለው የሚፈሱባት ትቦ።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ #ክላሽ ተደግፈው ተኳሽ የሚያወግዙ ድንዙዞችም ይበዙበታል። ዋናው ጉዳይ ግን ሌላ ነው።
ማን የፈጠረውን ችግር ነው የምናወግዘው
ማውገዝ እንዴት ያለውን መፍትሄ ሊያመጣ ነው
ለመፍትሄው ማን ይስራልን ዝርዝሩና ጥያቄው ብዙ ነው።
ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ የምንሳተፍበት እንጂ በማውገዝ ድንኳን ውስጥ የምንወሸቅበት አይደለም። መጀመሬ ነው። ከመሰሉኝ መፍትሄዎች ጋር እመላለሳለሁኝ። ጥያቄውንና መፍትሄውን ጀምሩት። በማውገዝ ድንኳን ውስጥ አንወሸቅ! ንግዱንም እንጠየፈው። በወገናችን ሰላም ከመስራት ለሰላማችን እንስራ።