Get Mystery Box with random crypto!

#በኡኡታ እንዳትጠፋ #በእልልታ አትለምልም ▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬ መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብም ስለምችል | Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

#በኡኡታ እንዳትጠፋ #በእልልታ አትለምልም
▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብም ስለምችል፣ ክላሽ ከያዘው ገዳይ በላይና በበለጠ ሀላፊነት የሚሻውን ብዕር የጨበጥኩ መሆኔን ጠንቅቄ አውቃለሁኝ። ከርሳም ብዕር እልፍ ገዳዮችን እንደምታፈራና እያፈራች እንደሆነም በአይኔ እያየሁ ነው። ጥንቃቄና ሰው መሆን ካልታከለበት ሁለታችንም ገዳይ እሳት ነው ጨብጠን የምንዞረው። ስለዚህ እልልታ አያሰክረኝም። ኡኡታም አያስበረግገኝም። ሀሳብ ገዳይ ከሰው ገዳይም እንደሚከፋ አውቃለሁና እኩል እጠየፋቸዋለሁኝ።

ወገኖቼ ልመርቃችሁ። አባቴ ያወረሰኝ ውድ ሀብት ነውና በሆዳችሁ አትውደቁ! ለላይክም ሆነ ለዩቲዩብ ዶላር አትንበርከኩ። ለወገን በሚቀርብ መፍትሔ የምትበረግጉ አውሬ አያድርጋችሁ። የሚፈጠፈጡብን ታላላቆቻችንም ልቦና ይስጣቸው። ታናናሾቻቸው የምናፍርባቸው ሳይሆን መከታ የምናደርጋቸው ይሁኑልን።
በተረፈ ለብሽሽቅ ጊዜ የለኝም። እኔን የሚያስጨንቀኝ "ወገኔ እንዳይሞት ምን ላዋጣ?" የሚለው እንጂ በየቀኑ ሰው እየሞተ ከንቱ እልልታ መለቃቀም አይደለም። በወገን ሞት ከመበሻሸቅ የከፋ ግፈኝነት የለም። ደናቁርት እንዲከስሙ ብርሀኑን አዋጡ። ደናቁርት ችግራችን ሳይገባቸው የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ አንጠብቅ። የሚበረግጉትን ትተን ለሰዎች በሰውኛ እንቀጥላለን።