Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርን _ከክርስቶስ ትይትናን ከማርያም ያልተማረ አገልጋይ አይሆንም ምሳሌይውረድከአትሮንስላይ | የማህበር መዝሙር 🙏🙏🙏

ፍቅርን _ከክርስቶስ ትይትናን ከማርያም
ያልተማረ አገልጋይ
አይሆንም ምሳሌይውረድከአትሮንስላይ

#አዝ

ስለሚያሳድዱት እሱ ካልፀለየ
በምንስ --ተለየ
የሚናገረውን በተግባር ካልኖረ
ምኑን አስተማረ

#አዝ

የሚያምነውን -ጌታ በሕይወት ካልገለጠ መቼ ተመረጠ
እየተበደለ ካላለ ይቅርታ
አያውቀውም_ጌታ

#አዝ
ልብ ሳይሰበረ ወንጌሉን ቢዘራ
አንዳች አያፈራ
ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ካላለ ብርቱ ነው ድካሙ ከንቱ ነው
#አዝ

ክፉን ተጠይፎ ካልቆመ ለእውነት
ስብከቱ ነው ሀሰት
ብርሃንን ሰብኮ በጨለማ ካለ
ራሱን አታለለ

እርስ በርሷ መንግስት ከተከፋፈለች
መቼ ትፀናለች
አባቶች ታረቁ ብኩርናን ትታችሁ
አንድ ይሁን መንጋችሁ
#አዝ

በፀጋ ስጧታው እራሡን ከካበ የጌታ ባርያው ነኝ ብሎ ካላሠበ
አምላክን ፀንሳ ጌታን የወለደች
ለፍፁም ትይትና ማርያም ምሳሌ ነች (3)