Get Mystery Box with random crypto!

የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆ | Metti high school ™

የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል።

የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች ማስተካከል ያለባቸውን መረጃዎች እንዲያስተካክሉ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ትላንት ተጠናቋል።

መቼ ተማሪዎች ተመድበው ትምህርት እንደሚጀምሩ ግን እስካሁን አይታወቅም።

በውጤት እና መቁረጫ ነጥብ ላይ ከተነሳው ቅሬታ ባለፈ ወደዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይገቡ ሌላው ቀርቶ የት እንደሚማሩ ሳያውቁ ለወራት ለመቀመጥ ተገደዋል፤ ይህም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

መንግስት እየተነሱ ላሉ ቅሬታዎች ያለውን ምላሽ በፍጥነት እንዲሰጥና ሌሎች ውጤት የመጣላቸውና ወደ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀል ያለባቸውን ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ትምህርት እንዲያስገባ ከወላጆችና ተማሪዎች እየተጠየቀ ይገኛል።

ይህ ዓመት ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት የቀረው ሲሆን እስካሁን ተማሪዎች አልተመደቡም፤ ዩኒቨሲቲዎችም መቼ ጥሪ እንደሚያደርጉ አይታወቅም።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተነሳ ጊዜ አንስቶ በኃላም በሰሜን ኢትዮጵያ የተነሳው ጦርነት የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከባድ ሆኖ ቀጥሏል።

በትግራይ ተማሪዎች የ2012ና የ2013 ፈተናን አልወሰዱም የ2014 ስለመውሰዳቸውም አጠራጣሪ ነው።

በሀገር ደረጃም የትምህርት መርሃግብሩ ቀድሞ ወደነበረበት ሊመለስ አልቻለም። ይህ ትውልዱ ላይ ትልቅ ተፅእኖ የሚያሳድር በመሆኑ መፍትሄ ያሻዋል።

@mettihighschool
@mettihighschool