Get Mystery Box with random crypto!

#MoE በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግ | Metti high school ™

#MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ምንጭ.-ቲክቫ ሀቪ

@mettihighschool
@mettihighschool