Get Mystery Box with random crypto!

✞ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ✞ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታምርህ ተሰምቷል ዝቋላን ካላየሁ ምድረ ከብድን ይ | ዘ_መርቆሬዎስ

✞ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ✞

ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታምርህ ተሰምቷል
ዝቋላን ካላየሁ ምድረ ከብድን ይላል
በክርስቲያኖች ልብ ተጋድሎህ አበራ
ዝጊቲም አየንህ ድንቅ ስትሰራ

ለነፍሳችን እረፍት ሰላምን ሰባኪ
የሰማዩን ሚስጢር ለትውልድ ተራኪ
ምክርህንም ሰምተን አገኘን ማምለጫ
ጌታን ስታሳየን ጠቁመህ አቅጣጫ

/አዝ=====

ሕይወትህ ይደንቃል ላነበበው ሁሉ
ጦርና ጋሻ ነው የእግዚአብሔር ቃሉ
ለዓለም ተሰቅለህ ዓለምን ሰቅለሃል
በምድር ላይ ሆነህ ሰማይን ኖረሃል

/አዝ=====

በመክሊትህ ያተረፍክ እምነትህ የጸና
ጌታን ያከበርከው ኖረህ በትህትና
የዓለም አሸን ክታብ በፊትህ ተንቆ
ዲያብሎስ ተገዛ ከእግርህ በታች ወድቆ

/አዝ=====

ብዙ ምስክሮች በዙሪያችን አሉ
በተጋድሎ ጸንተው ክብር የተቀበሉ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዝቋላ የኖረው
የዓለሙን ቤዛ አክብሮ አከበረ
#ዘ-መርቆሬዎስ ወጣት ማህበር

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥ @Merkorawos ✥
✥ @Merkorawos ✥
✥  #ዘ_መርቆሬዎስ ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥